Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, July 21, 2012

ፍትህ ጋዜጣን ማገድ የአገሪቱ ሁኔታ ወደ አደገኛ ሁኔታ መሄዱን የሚያመላክት ነው ሲል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ተናገረ

ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም, የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ነው። 

መንግሥታዊው ብርሃንና ሠላም ማተሚያ ቤት ሃሙስ ምሽት ሳንሱር አድርጎ አላትምም ብሎ ያቋረጠውን የፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 5 ቁጥር 197 ፣ ከፌዴራል ጸረ ሽብር ግብረይል፣ ዐቃቤ- ሕግ፣ የደህንነት ኃይሎች እና ከፍትህ ሚንስትር ተወካዮች ጋር ከተነጋገረና ይዘቱን ካስገመገመ በኋላ ትላንት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በደህንነት ኃይሎች ቅርብ ክትትል ሥር ሆኖ ጋዜጣው እንዲታተም ቢፈቅድም ፣ በዛሬው ማለዳ ለሥርጭት እንዳይውል አድርጓል።

በመርካቶና አካባቢዋ ግጭት ተነሳ

ኢሳት ዜና:-
ሐምሌ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብና በኢህአዴግ መካከል የተፈጠረው የመብት ጥያቄ ውዝግብ ተካሮ  በፖሊሶች ላይ ድንጋይ የወረወሩ ሲሆን የኢህአዴግ መንግሥት የፌዴራል ፖሊስ ልዩ ኮማንዶ የጥይትና አስለቃሽ ጭስ ምላሸ የሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡

በርካታ ሰዎች የመፈንከት፣ የመደብደብ እና በትልልቅ ኦራል ካሚዮን እየተጫኑ ለጊዜው ወዳልታወቀ ሥፍራ መወሰዳቸውን ዘጋቢያችን ተመልክቷል፡፡ በግጭቱ ላይ በመርካቶ አንዋር መስኪድ ዙሪያ፣ አዲስ ከተማ፣ ጨው በረንዳ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ የሚገኙ ክርስቲያኖች በአመጹ ውስጥ በመሳተፈቸው ወደ አጠቃላይ የዜጎች የመብት ጥያቄ ያመራ ሲሆን 7፡00 ሰዓት ላይ የጀመረው አመጽ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ለጊዜው የበረደ ይመስላል፡፡

Wednesday, July 18, 2012

የሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ታሰሩ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ የ አቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ገንዘብ ይዘው ሲወጡ ተይዘው መታሰራቸውን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘገበ።

ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሃቢባ መሐመድ መሐሙድ ፤በወረዳ 17 ወርቁ ሕንፃ አጠገብ ከሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሃይማኖት አታሼ ቢሮ ግምቱ ከሃምሳ እስከ መቶ ሺ ብር የሚገመት የታሰረ ገንዘብ እና በዓረብኛ የተፃፉ መፅሐፍት ይዘው ሲወጡ በፌዴራል ፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

የአቶ መለስ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ላለፉት 2 ሳምንታት የኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቦ የቆየው የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ የመከላከያ፣ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት እንዲከታተሉ ታዘዙ::

 የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ የአመራር አባልን በመጥቀስ እንደዘገበው  የፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት አባላት የአቶ መለስን የጤና ሁኔታ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ወይም በዋና ዋና የክፍለሀገር ከተሞች ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን በፍጥነትና በቅልጥፍና መቆጣጠር የሚያስችል ” የአንድ ለአምስት” የጥቃት አመካከት ስልት ተግባራዊ እንዲሆንና ፖሊሶችም በዚሁ መሰረት ልምምድ እንዲጀምሩ ትእዛዝ ተላልፎአል።

Tuesday, July 17, 2012

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባት እና የፖለቲካው አሰላለፍ

ቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ መግባት እና የፖለቲካው አሰላለፍ

ህመማቸው ፀንቶ ቤልጂየም ሀገር በመታከም ላይ ይገኙ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ትላንትና ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል። ሕይወታቸው እንዳለፈ ሲነገር የነበረው አቶ መለስ ወደ ቤተመንግስታቸው የተመለሱት ‹‹ከህመማቸው አገግመው›› ይሁን ወይም ‹‹ከዚህ በኋላ በህክምናው አትድንም ተብለው በተስፋ መቁረጥ›› ይሁን እስከ አሁን ለማረጋገጥ አልቻልኩም። የተረጋገጠው በህይወት መግባታቸው ብቻ ነው፡፡

የአቶ መለስን መታመም ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ አራት ሀይሎች ‹‹በሸዋ ፖለቲካ›› ጥበብ ግብግብ ገጥመዋል። በእርግጥ አንደኛው ሀይል (ቡድን አንድ) የበላይ የመሆን ዕድሉን እያሰፋ ነው። 

በዳባት ከተማ አንድ ነዋሪ የቀበሌውን ባለስልጣን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ሰዎችን ገደለ

ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ ቀበሌ 03 ነዋሪ የነበረ አንድ ግለሰብ የቀበሌው ሊቀመንበር የሚያደርስበትን ጫና ለመቋቋም ባለመቻሉ ሊቀመንበሩን፣ ባለቤቱን እና ሌላ አንድ የሊቀመንበሩ አጋር የሆነ ሰው ገድሎ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ክፉኛ አቁስሎአል።

በፍትህ እጦት የተማረረው ግለሰብ ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ እጁን ለመንግስት የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ በሁዋላ እንደፈለጋችሁ አድርጉኝ የልቤን አድርሻለሁ በማለት መናገሩን ዘጋቢዎቻችን ገልጠዋል።

ግለሰቡ ከሊቀመንበሩ ጋር ያለውን ውዝግብ በድርድር ለመፍታት ጥረት ያደርግ ነበር ተብሎአል።

 Source: ኢሳት ዜና:-

የአውሮፓ ህበረት በእነ አቶ አንዱለአም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወገዘ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ህብረቱ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ መሪዎችን አወዛጋቢ በሆነው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ ሰበብ አድርጎ ማሰሩ በአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሳይቀር እንዲተች አድርጎታል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ካተሪና አሽተን የፍርድ ሂደቱን አዲስ አበባ በሚገኙ ዲፕሎማቶች አማካኝነት ሲከታተሉት መቆየታቸውን ያወሳው የህብረቱ መግለጫ፣ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ ራሱዋን ከሽብረተኝነት የመከላከል መብት ቢኖራትም ፣  የጸረ ሽብረተኝነት ህጉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ሳይቀር እንደ ሽብር መመልከቱ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል።

ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳው አረፈ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ጀርመን ድምጽ ራዲዮ የአዲስ አበባ ወኪል የሆነው ጋዜጠኛ ታደሰ እንግዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ተወዳጁ  ጋዜጠኛ ይህን ዓለም የተሰናበተው፤ ትላንት ማምሻውን በደረሰበት   ድንገተኛ  የመኪና አደጋ ነው።

ደቼ ቨለ እንደዘገበው ፤ጋዜጠኛ ታደሰ አደጋው የደረሰበት፤ ከአዋሳ የኒቨርሲቲ ዘንድሮ ትምህርቱን ባጠናቀቀ በወንድሙ ምረቃ ፕሮግራም ላይ ተካፍሎ ወደአዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳለ ነው።በአደጋው ከታደሰ በተጨማሪ ለምርቃቱ ወደ አዋሳ ሄዶ የነበረ ሌላ ወንድሙም የሞተ ሲሆን፤ ከአዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀው ደግሞ ክፉኛ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት ህክምና እየተከታተለ ይገኛል።

Sunday, July 15, 2012

ሕዝብ ተገፋ! ተጠያቂነት ጠፋ!

በየስብሰባው፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በዓመታዊ ሪፖርት፣ ወዘተ በተደጋጋሚ የምንሰማው ይህ ተከናወነ፣ ይህ ተሠራ፣ ይህ ተሳካ፣ አንዳንድ መጠነኛ እንቅፋት ቢያጋጥምም አበረታች ነበር፣ ወዘተ የሚል ነው፡፡

የተሳካና የተፈጸመ ነገር የለም አንልም፡፡ አለ፡፡ ነገር ግን ተደናቅፎ ስለቀረው፣ ሳይሳካ ቀርቶ ገንዘብ ስላከሰረው፣ ሲጠበቅ ስለነበረውና ሥራ ላይ ሳይውል ስለቀረው ልማትም ሆነ ሌላ ጉዳይ አንሰማም፡፡ በተለይ በተለይ ለተሰጣቸው ሥራ ኃላፊነት ወስደው ሳይፈጽሙ በመቅረታቸው፣ አገርና ሕዝብ እንዲጐዳ ያደረጉ መሥርያ ቤቶችና ግለሰቦች ተጠያቂ ሲሆኑ አይነገረንም፡፡

የኢህአዴግ ጥንካሬ ምን ያክል ነው?

እንቁላል በጫፍና ጫፉ በመዳፍ መሃል አይሰበርም
ሙላቱ አርጋው ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ ሲነዱ በርጋታ ነው፤ የኢትዮጵያን ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ስነ ልቦና ላለፉት 40 ዓመታት ስራዬ ብለው አንብበዋል፤ ባለፉት 21 ዓመታት የኢህአዴግን አስተዳደር እግር በግር ተከታትለዋል፤ “ኢህአዴግ ከተቃዋሚዎች አንጻር እጅግ ጠንካራ ነው፤ ጥንካሬው ግን በትክክለኛው መሰረት ላይ አይደለም’’ ይላሉ፡፡

 “ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ ስነዳ ቀጥ ያለው መንገድ የደህንነት ስሜት ይሰጠኛል፤ ጠንካራ የሚመስለው ግን ግዝፈቱ ወደ አንድ አቅጣጫ ያደላ የሚመስለው ኢህአዴግ ግን ያሳስበኛል፡፡” ይላሉ::

የመለስ ህመም፣ ታክቲክ እና መፃኢ እጣ ፈንታ

By ተመስገን ደሳለኝ
ሰሞኑን አዲስ አበባ በወሬ መጋኛ ተመታለች። ወሬው በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በተለይም በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንደ ጉድ እየተራገበ ነው- የ57 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በጠና መታመም። ህመማቸውንም ተከትሎ ቤልጂየም ለህክምና መሄዳቸው እና ከፍተኛ ሊባል የሚችል ክብደት የመቀነሳቸውም ወሬ እንዲሁ የመጋኛ ያህል ነው።

በእርግጥ የጉብዝናውን ወራት የዱር ፍሬ እየበላ በረሃ የታገለ ቀርቶ በቤተመንግስት ያደገ ‹‹ልዑል››ም ቢሆን የዚህን ያህል አመት በስልጣን መቆየቱ (ሌላ ምክንያት እንኳ ባይኖር) በጤናው ላይ አንዳች ጉዳት ማስከተሉ አይቀሬ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ችግርም ይህ ነው። ሌላ አይደለም። በበርካታ አምባገነን መሪዎች ላይ የታየ ማለቴ ነው፡፡

ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ እራሱን ከሳተ ቦኋላ በቻርተር አውሮፕላን ወደ ቤልጂዬም ብራስልስ መወሰዱ ታወቀ

አገራችን ኢትዮጵያንና ህዝቧን በመጥላት ተወዳዳሪ የሌለው መለስ ዜናዊ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለከፈበት የካንሰር በሽታ ምክንያት አእምሮውን ከሳተ ቦኋላ ለአፋጣኝ የህክምና እርዳታ በቻርተር አውሮፕላን ወደ ቤልጂዬም ብራስልስ መወሰዱን የብራስልስ ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ።

እንደ ምንጮቻችን መረጃ ሞት አፋፍ ላይ ያለውን መለስ ዜናዊን የጫነው አውሮፕላን ከአዲስ አበባ የወጣው ረቡዕ ሌሊት ሲሆን ብራስልስ ሆስፒታል የገባው በማግስቱ ሃሙስ ጠዋት እንደሆነና አውሮፕላን ማረፊያ ሲጠባበቀው የነበረው አምቦላንስ ወዲያውኑ ተቀብሎት ዘወትር ወደሚታከምበት የሴንት ሉክ ሆስፒታል አድርሶታል።