- ‹‹ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም››
ከትናንት በስቲያ ስብሰባውን ረግጠው እንደወጡ ዘ-ሐበሻ የዘገበችላቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለዐቃቤ መንበሩ ማቅረባቸውን ምንጮቻችን ገለጹ። የዘ-ሐበሻ ምንንጮች እንደሚሉት ዋና ጸሐፊው ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑት ከጥር 6 እስከ ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ጉባኤ እንደተጠናቀቀ ነው ያሉት የዜና ምንጮቻችን “ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም” በሚል የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ማቅረባቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል። እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ከሆነ ለሕሊናቸው ያደሩ እውነተኛ አባቶች የአቡነ ሕዝቄልን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችሉ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል።ውድ የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ይህ ዘገባ ከደረሰን በኋላ ሐራ ተዋሕዶ የተሰኘው ድረ ገጽ በአቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ዙሪያ የሚከተለውን ሰፊ ዘገባ አቅርቧል። እንደወረደ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።


