Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, August 23, 2012

ተወዳጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቃሊቲ እስር ቤት ተወሰደ!

የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ባለፈው ሳምንት ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበር ይታወቃል። በቀረበበትም እለት በርካታ አድናቂዎቹ እና የፍትህ ጋዜጣ አንባቢ ወዳጆች ፍርድ ቤቱን አጨናነቀውት የነበረ ቢሆንም ዳኛ አልተሟላም በሚል ሰበብ ለዛሬ ነሐሴ 16/2004 ዓ.ም  ተቀጥሮ ነበር።

በዛሬው እለት የተመስገንን ክስ የተመለከተው ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛው የተከሰሰበት ወንጀል ዋስትና አያሰጥም በሚል ወደ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት እንዲወሰድ እና በቀጣይ ነሀሴ 28/ 2004 ዓ.ም እንዲቀርብ ቀጠሮ ሰጥቷል።

አልሸባብ እና ግብፅ ሆይ፤ የሞቱት መለስ እንጂ ኢትዮጵያ እንዳልሆነች ኮስተር ብዬ እነግራችኋለሁ። ....... ከአቤ ቶክቻው

የጠቅላይ ሚኒስትሩን መሞት ቀድመው የተረዱት የግብፅ ባለስልጣናት “ከቀጣዩ መንግስት ጋር በአባይ ጉዳይ ላይ መግባባት ይኖረናል ብለን እናስባለን!” ሲሉ በደስታ መናገራቸውን ሰምተናል።

አሁን በቅርቡ ደግሞ አልሸባብ ሆዬ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት መደሰቱን ገልፆ ከዚህ በኋላ በእርግጠኝነት ኢትዮጵያ ትበታተናለች ሲል “ቅዠቱን” ጮቤ እየረገጠ ሲነግረን፤ መቼም ጆሮ አልሰማ አይልምና አድምጠናል። ይሄ ስለ ኢትዮጵያውያን ማንነት ጠንቅቆ ካለመረዳት የመጣ የግንዛቤ ችግር የፈጠረው ፈንጠዝያ ነው።

የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ሌሎች ጓዶቻቸው ለህዝብ ድጋፍ ማግኛ እየዋሉት ነው ተባለ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አዲሱ መንግስትና ነባር ታጋዮች ፣ በአቶ መለስ ሞት የህዝብ ድጋፍ ለማሳበሰብና የተዳከመውንና በቋፍ ላይ የሚገኘውን ፓርቲያቸውን ነፍስ ለማዘራት እየተሯሯጡ መሆኑን የኢህአዴግ ምንጮቻችን ገልጠዋል።

የአብአዴን ኢህአዴግ የአመራር አባል የሆነው ምንጫችን እንደገለጠው፣ ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ጭንቅት ውስጥ ይገኛል። በአንድ በኩል “የታጋይ መለስ የሽኝት ኮሚቴ” የሚል ኮሚቴ በሁሉም የአገሪቱ ወረዳዎች በማቋቋም ህዝቡ ለድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ፣ በሰልፉም ለኢህአዴግ ያለውን ታማኝነት እንዲገልጥ፣ በሌላ በኩል ደግሞ መላ የደህንነት አባላቱን በህዝቡ ውስጥ በመበተን የህዝቡን ስሜት ለማወቅ ስትራቴጂ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው።

የተለያዩ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ዙሪያ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው

ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ነባር ታጋይ የሆኑት አቶ አስገደ ገብረስላሴ ለአቶ መለስ ዜናዊ ወታደራዊ ትምህርት እንደሰጡዋቸው  ይናገራሉ::

የአቶ መለስ ዜናዊን የ21 አመታት አስተዳዳር እንዴት ይገመግሙታል ተብለው የተጠየቁት አቶ አስገደ ፣ በርካታ ችግሮች መታየታቸውን አልሸሸጉም::

ስለ አቶ መለስን ሞት የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አስተያየት

ኢሳት ዜና:-  ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
“በኢትዮጵያ የመሪነት ሥልጣን የሚይዘው ሰው የሚመራበትን ሁኔታ ራሱ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ የሚመራበትን ሁኔታ በፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ አስገብቶ መስጠት የሚመራውን ሰው መናቅ ነው ብዬ ነው የማስበው” ሲሉ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ተናገሩ።

በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ  በጠቅላይ ሚኒስትር  መለስ ሞት ሀዘን እንደተሰማቸው በመግለፅ፦” ፤”ከእንግዲህ በሞተ ሰው ላይ እንዲህ ነው- እንዲያ ነው ማለት አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሳይሞቱ ቢሆን ኖሮ ብዙ ነገር መማማር ይቻል ነበር፡፡ በሕይወት እያሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን፦ አምባገነን፣ ጨካኝ፣ ወዘተ በማለት ብዙ ኃይለ ቃል ተጠቅመን ገልጸናቸው ይሆናል፡፡ አሁን በሞተ ሰው ላይ ምንም ማለት አስፈላጊም አይደለም”ብለዋል።

Tuesday, August 21, 2012

የአቶ መለስ ዜናዊን ዜና እረፍት ተከትሎ በመላው አገሪቱ ውጥረት ነግሷል

በአዲስ አበባ በርካታ ሰዎች ከእየ አካባቢያቸው ተሰባስበው የሚሆነውን በኢትዮጵያ ሬዲዮና እና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚከታተሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ህዝቡን የማረጋጋት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ገድል በማወጅና እና በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በመንግስታዊ ድርጅቶች እና ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ መውለብለብ ጀምሯል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በየቦታው ፣ በሰፈሮች ውስጥ ሳይቀር ተበታትነው ይታያሉ።

ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ

ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ
እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ

የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በይፋ ከተነገረ በኃላ የመጀመሪያ በሆነው የመንግስት መግለጫ የቀብር አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን፣ከዛሬ ጀምሮ እስከቀብር ቀን የሚዘልቅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን መታወጁን፣የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ብሔራዊ ኮሚቴው የቀብሩን ቀንና ሥነሥርዓት በተመለከተ በቀጣይ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁመው ጠ/ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

አቶ በረከት ጠ/ሚኒስትሩ የት አገር እንደታከሙ፣የት አገር እንደሞቱ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አደረገ

 ዜና / News: የኢትዮጵያው ጠ/ሚ፤ አቶ መለስ ዜናዊ በተወለዱ በ57 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሁለት ወራት ከተሰወሩ በኋላ ነው ዛሬ፤ ማክሰኞ፤ ነሀሴ 15 ቀን መሞታቸው የተዘገበው።

ኢሳት ሀምሌ 23 ቀን፤ የአለምአቀፉን የቀውስ አጥኚ ቡድን (አይ.ሲ.ጂ) ውስጣዊ ምንጮችን ጠቅሶ የአቶ መለስን ሞት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ መለስን ሞት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት፤ በይፋ የአቶ መለስን ሞት ዘግበዋል። አልጀዚራን ጨምሮ፤ ሌሎች ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀንም ዜናውን እየዘገቡት ይገኛሉ።

የመለስ ዜናዊ አስከሬን በቦሌ የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጧል!! (udated news)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም መለየታቸው የ”አዋጁን በጆሮ” ዜና ኦገስት 21፣ 2012 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ገልጿል። ከጥቂት ቀናት በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን፤ ከውጭ አገር በግል አውሮፕላን እንዲገባ ተደርጎ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ነበር የቆየው። 

 ሆኖም በኢቲቪ የዜና እወጃ ላይ፤ “በትላንቱ ምሽት በድንገት ህይወታቸው አልፏል።” የሚል ውሸት በድጋሚ ተሰምቷል። የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን ወደ ሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ከመግባቱ በፊት፤ በዚያ የነበሩ ሌሎች አስከሬኖች በሙሉ እንዲወጡ አስቸኳይ ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር። ከዚያም አስከሬኑ በግል አውሮፕላን መጥቶ በከፍተኛ ጥበቃ ወደ ሬሳ ማቀዛቀዣ ክፍል ከተወሰደ በኋላ እስካሁን ድረስ በወታደር እየተጠበቀ ነው የሚገኘው። 

Monday, August 20, 2012

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ነሐሴ 14/2004 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአርሲ ሃገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑ የሲኖዶሱ ዋና ፀሃፊ ገለፁ።

የሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊና የከፋ፣ ሸካና ቤንች ማጂ ዞን አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የፓትርያርኩን ምርጫ አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የዋና ፓትርያርክ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው እንዲሰሩ ተወስኗል።

Sunday, August 19, 2012

አቦይ ስብሃት ነጋ ታገዱ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) የህወሃት መስራችና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩት ስብሃት ነጋ ከማንኛውም መንግስታዊ ስራ ታገዱ። ለኢ.ኤም.ኤፍ የደረሰው መረጃ እንደገለጸው ከሆነ፤ ስብሃት ነጋ የኢትዮጵያን መንግስትም ሆነ ኢህ አዴግን በመወከል ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጡ መመሪያ ተላልፎባቸዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ አቶ ስብሃት ነጋ ከአሜሪካ ድምጽ እና ከጀርመን ሬዲዮ ጋር አድርገውት የነበረው ቃለ ምልልስ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን፣ ከኢ.ዜ.አ፣ ከትግራይ ኦን ላይ እና ከአፍቃሬ ኢህአዴግ ድረ ገጾች ላይ እንዲነሳ ወይም እንዲሰረዝ ተደርጓል። አሁን ያለው ውጥረት የተፍጠረው በአቶ በረከት ስምኦን እና በአቶ ስብሃት ነጋ ቡድን መካከል መሆኑ ነው። 

በዳላስ ግድያ የፈጸመው አብይ ግርማ፤ በዴንቨር ፖሊስ ሲያዝ አስደንጋጭ መረጃዎች ተገኙበት

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዳላስ የደስታ ሬስቶራንት ባለቤት የሆኑትን አቶ ያየህይራድ እና የኒን በማታ ተከትሎ የገደላቸው ኢትዮጵያዊ ዴንቨር ከሚገኘው ዳግማዊት ግሸን ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ትምህርት ቤት የ2011 ኒሳን መኪናውን እንዳቆመ ነው በፖሊስ የተደረሰበት። አብይ ግርማ ይባላል። ከዚህ በፊት ዴንቨር ነዋሪ ነበር። አትላንታ ከተማም መምጣትን ያዘወትራል። 
 
ዳላስ ከተማ ውስጥ ደግሞ በሊሞዚን መኪና ሹፌርነት ይሰራል። ከዚህ በፊት ዳላስ በሚገኘው ደስታ ሬስቶራንት ውስጥ ከሰዎች ጋር ተጣልቶ ስለተፈነከተ፤ የጉዳት ካሳ በመጠየቅ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዷል። 

ኢቲቪ የኢድን ቀጥታ ዝግጅት ሳያልቅ አቋረጠ!

Abe Tokichaw: ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሶስት ቀን ጀመሮ የረመዳን ፆም ፍቺን አከባበር አስመልክቶ በዜና ዘገባው ላይ ረጅም ሰዓት ሰጥቶ ሲዘግብ ሰንብቷል። ከዛም አልፎ ተርፎ ገና ከሶስት ቀን አንስቶ በየዜናዎች መሀከል  በረጅሙ፤“እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ!” የሚል መልዕክት ሲያስተላልፍ ቆይቷል። ደግሞም የተለያዩ ሙስሊም የህብረተሰብ ክፍሎችን በዓሉን እንዴት “ሰላማዊ በሆነ መልኩ” እንደሚያከብሩት ሲጠይቅ እና ሲጨነቅ ሰንብቷል።
እኔን ጭንቅ ይበለኝ…!

የደህንነት ሹሙ አቶ አቶ ጌታቸው አሰፋ “የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ተከትሎ ጎንበስ ቀና ማለቱ ያስተዛዝባል” አሉ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኢሳት የብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት ምንጭ እንደገለጠው የደህንነት ዋና ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሰሞኑን ዋና ዋና የሚባሉ የኢሚግሬሽንና የውጭ መረጃ ሰራተኞችን እና በተለያዩ ተቋማት የተመደቡ የደህንነት አባላትን ሰብስበው በአቶ መለስ ዜናዊ የደህንነት ሁኔታ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል።

ከስብሰባው በፊት በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ለሚገኙት የደህንነት አባላትና የመንግስት ባለስልጣናት ” የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ተከትሎ ጎንበስ ቀና ማለቱ ያስተዛዝባል” በሚል ርእስ  ባለሁለት ገጽ ደብዳቤ ጽፈው አሰራጭተዋል።