Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, June 29, 2012

ስቴት ዲፓርትመንት እስረኞቹ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት ዜና:-ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የአቶ መለስ መንግስት ከመላው ዓለም ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተነሱበት ነው። የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነ አንዷለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት በተከሰሱ 24 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በ አቶ መለስ መንግስት ላይ ከ ዓለም ዙሪያ ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው።

በፍርድ ቤቱ ብይን ላይ ተቃውሞ ካሰሙት መካከል አንዱ፤ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ነው።የዩ.ኤስ ስቴት ዲፓርትመንት ፤ እስክንድር ነጋ እና ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የኢትዮጵያ ያ ፍርድ ቤት ያሳለፈው የጥፋተኝነት ብይን እጅግ እንደሚያሳስበው በመጥቀስ፤ ውሳኔው በኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ህግ ይዘት እንዲሁም፤ አገሪቱ ህገ-መንግስታዊ ዋስትና በሰጠቻቸው፤ በፕሬስ እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት አተገባበር ዙሪያ ከባድ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው ብሏል።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት ሲጠይቁ ዋሉ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በአንዋር መስጊድ ለጁማ ሶላት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸውን በጽናት እና በቁጭት አቅርበዋል። ድምጻችን ይሰማ፣ መጅሊስ አይወከለንም፣ ምርጫው በመስጊዳችን ይሁን፣ ህገ መንግስቱ ይከበርና የመሳሰሉትን መፈክሮች አሰምተዋል። መንግስት መጪው የመጂሊስ ምርጫ በቀበሌ እና በመስተዳድር ቦታዎች እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምርጫው በቀበሌ መሆኑ፣ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና ተማኞችን መልሶ ወደ መጅሊስ አመራር የሚመጣ ነው በማለት ይቃወማሉ። በዛሬው ተቃውሞ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሙስሊሙን ጥያቄ በመደገፍ የተቃውሞ ሰልፍ አደርገዋል።

Ethiopia: Conviction of government opponents a 'dark day' for freedom of expression

More Ethiopian government opponents have been convicted on trumped up terrorism and treason charges in what Amnesty International called "a dark day" for freedom of expression.

Iconic dissident journalist Eskinder Nega and leading members of the political opposition, Andualem Arage
and Nathnael Mekonnen, along with five other men, were found guilty on charges of ‘Terrorist Acts,’ ‘Encouragement of Terrorism,’ and ‘High Treason’ and several other charges.

45 Ethiopian immigrants found dead in forest

At least 45 illegal immigrants reportedly from Ethiopia have died and 72 others are in critical condition from lack of clean air in a container they were in, apparently on their way to Malawi via Tanzania. Reports said bodies of the deceased and those who were still alive were discovered yesterday morning by wananchi in Chitego forest.

The deputy Home Affairs Minister, Pereira Ame Silima confirmed the death of the foreigners after visiting the scene yesterday and being briefed by the Dodoma Regional Police Commander, Zelothe Stephen. The deputy minister said at least 45 Ethiopian nationals died, explaining that the majority were old, while the young survived, though they were very weak.
By William Davidson
Dissident Ethiopian writer Eskinder Nega was yesterday convicted of conspiring to commit acts of terror, sparking an outpouring of international condemnation.
 Christian Science Monitor (Addis Ababa) -The eloquent, long-standing critic of the Ethiopia Peoples’ Revolutionary Democratic Front’s rule – who has also been jailed at least seven times – was awarded the PEN American Center Freedom to Write prize last month. PEN called the verdict demonstrated a “shameful disdain for Ethiopia’s obligations to its citizens and to international law.”
 

 Judges at the Federal High Court found Mr. Eskinder – along with 23 other activists and writers – guilty of being involved in plotting a violent revolt. Supporters say his actual crime was voicing pro-democracy views and discussing the possibility of peaceful protests in the wake of the Arab Spring. Supporters include US Sen. Patrick Leahy (D) of Vermont, who wants at least $500,000 of existing American aid to Ethiopia’s military next year to be potentially withheld, depending on whether the Ethiopian government respects press freedom.

የጭኮ እና የይርጋለም ህንጻዎች መፈክሮች ተውበው ታዩ፣ መፈክሮችን ለማጥፋት ህንጻዎች እንዲፈርሱ ተደርጓል

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በጭኮና በይርጋለም ከተሞች ዛሬ ጠዋት የታየው ነገር በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ይላል ዘጋቢያችን።  ሰላም የራቀውና በሀዘን ድባብ ላይ የሚገኘው የከተማው ህዝብ ከቤቱ በጧት ሲወጣ የጠበቀው  እንደ ሰሞኑ ፍርሀትና ጭንቀት ሳይሆን ደስታና ተስፋ ነበር።  በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች  ሁሉም በሚባል ደረጃ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሌሊቱን በሙሉ  በደማቅ ቀለማት ሲሸለሙ አድረዋል። 

ህዝቡም በግድግዳዎቹ ላይ የተጻፉትን መፈክሮች ለማየት እየተደዋዋለ ወደ አደባባዩ ጎረፈ። የሚይዙት የጠፋቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና ፖሊሶች መፈክሮችን በውሀ ለማጥፋት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። ተስፋ በቆረጠ ስሜትም ጽሁፎችን ለማጥፋት የፊት ግድግዳዎች መፍረስ እንደገና መልሰውም በስሚንቶ መለሰን ነበረባቸው። ፖሊሶች የህንጻ መቦርቦሪያ ማሽኖች እየያዙ በየህንጻዎች ላይ በመውጣት ሲቦረቡሩ ፣ ሲለስኑ የከተማው ህዝብም በፖሊሶች ድርጊት ይዝናና ነበር።

ኢህአዴግ ነባር ታጋዮቹን ልዩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ህግ አወጣ

ኢሳት ዜና:-ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በነፍጥ ትግል የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረውና በአሁኑ ሰዓት ግን ኢህአዴግ በታገለበት መስመር በመሄድ በትጥቅ እና በሁለገብ ትግል ለውጥ ለማካሄድ የተደራጁ የተቃውሞ ኃይሎችን በአሸባሪነት የሚፈርጀው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ለቀድሞ ታጋዮቹ ላሳለፉት የትግል ዘመን ልዩ የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ደንብ አወጣ፡፡በዚሁ ደንብ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች ታጋይ የነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአዋሳ ከተማ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በትናንትናው እለት የክልሉ መስተዳደር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን በአዋሳ ባህል አዳራሽ ውስጥ በሰበሰቡት ወቅት ነው ውዝግቡ የተፈጠረው። አቶ ሽፈራው ” ሲዳማ ክልል እንዲሆን የጠየቃችሁት መቼውንም አይሳካም ቁርጡን እወቁት ” በማለት ሲናገሩ ተሰብሳቢው ተቃውሞውን ገልጧል።

በአዋሳ ተወልደው የኖሩ የሲዳማ ብሄረሰብ ተወላጅ ያልሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ” እኛን የሲዳማ ህዝብ አላጠቃንም፣ ሲዳማ እኛን አይጠላንም፣ እኛን እያስጠቃን ያለው አመራሩ የሚያወጣው ህግ ነው፣ እኛ ተከባብረን፣ ተዋልደን የምንኖር ህዝብ ነን” በማለት አስተያየት ሲሰጡ፣ ከሲዳማ ተወላጆች በስተቀር የሌላ አካባቢ ተወላጆች አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ አቶ ሽፈራው ሲናገሩ ነው፣ ውዝግቡ የተፈጠረው።

ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሲጓዙ የነበሩ 42 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞተው ተገኙ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የታንዛኒያ ያገር ውስጥ ምክትል ሚኒስትርን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፤ በከባድ መኪና  እንደ ዕቃ  ከሁዋላ ታሽገው ወደ ማላዊ ሲጓዙ ከነበሩት 120 ሰዎች መካከል 42 ቱ ሞተዋል።ሚኒስትሩ ፔሬሪያ ሲሊማ እንዳሉት ስደተኞቹ የመጡት ከኢትዮጵያ ሲሆን፤የሞቱትም  ከትራኩ  የሁዋላ ክፍል ተጨናንቀው በመታሸጋቸው ሳቢያ አየር አጥሯቸው ነው።

ታንዛኒያ እና ማላዊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራቸው  የሚፈጠርን ግጭት እና ድርቅን በመሸሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዝ ለሚፈልጉ ኢት ዮጵያውያን እና ሶማሊያውያን ስደተኞች ፤እንደመሸጋገሪያ እየሆኑ መምጣታቸውን ቢቢሲ አመልክቷል። በተመሣሳይ የዛሬ ሳምንት ከማላዊ ወደ ደቡብ አፍሪካ በጀልባ ሲጓዙ የነበሩ 47 ኢት ዮጵያውያን ስደተኞች  ማላዊ ሀይቅ ውስጥ ሰጥመው ማለቃቸው ይታወሳል።

ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ጽዋ በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ሲል አቶ አንዱአለም አራጌ ተናገረ

ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው አቶ አንዱአለም አራጌ ይህን የተናገረው ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍ ዛሬ በዋለው ችሎት ላይ ነው። የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ የተከታተለው ዘጋቢያችን  እንደገለጠው  የከፍተኛው  ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን ሁሉንም ተከሳሾች ጥፋተኞች ብሎአቸዋል።