Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, January 29, 2013

ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ ስብሀትና አማራ


ሉሉ ከበደ
ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን።
ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ።  

የቅ/ሲኖዶሱን ውሳኔ የተቃወሙት ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ አቀረቡ


  • ‹‹ማንንም አሿሿሚ አይደለሁም፤ የሥልጣን ጥመኞችን አላገለግልም››
    Ab Hizkiel
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ለዐቃቤ መንበሩ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ የወሰኑትና ከሐላፊነት የመልቀቂያ ደብዳቤ ያቀረቡት ከጥር 6 – 8 ቀን የቆየው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንደተጠናቀቀ መኾኑ ተገልጧል፡፡

“መናገር የማልፈልገው ብዙ ነገር አለ” ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል

የቅ/ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል 

የአጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ




(አንድ አድርገን ጥር 16 2005 ዓ.ም)፡- ቦታው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከጦር ኃይሎች ወደ ወይራ ሰፈር ሲሄዱ ከ2 ኪሎሜትር በኋላ ከአጉስታ ልብስ ስፌት ፋብሪካ አለፍ ብሎ ይገኛል፡፡ በ14/05/2005 ዓ.ም ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ምክንያቱ እስከ አሁን ያልታወቀ አሳት የአጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ አደጋ አድርሷል ፤ ቤተመቅደሱ የተዘጋው ከጠዋቱ 3 ሰዓት በፊት ቢሆንም እሳቱ ግን የተነሳው 7 ሰዓት አካባቢ መሆኑ ሰዎችን አነጋግሯል ፤ ከቤተክርስቲያኒቱ በጣሪያ በኩል ትንሽ ትንሽ ጭስ መውጣት ከታየ በኋላ ብዙም ጊዜ ሳይሰጥ ነዳጅ የተርከፈከፈበት እስኪመስል ድረስ ተንቦገቦገ ፤ በደቂቃዎች ውስጥ በርካታ ሰዎች ከአካባቢው በመሰባሰብ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት አደረጉ ፤ እሳቱን ለማጥፋት አካባቢው ላይ ባለው ነገር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም በወቅቱ እሳቱን ማጥፋት ግን አልተቻለም ፤ ይህ ጉዳይ ከአቅም በላይ መሆኑን በመገንዘብ ለአዲስ አበባ እሳት አደጋ መስሪያ ቤት ስልክ ተደውሎ የነበረ ቢሆንም እነርሱ እስኪመጡ ድረስ እሳቱ ከፍተኛ ጉዳይ አድርሶ ነበር ፤ በቦታው የደረሱበት ሰዓትም ብዙ ነገሩ ወደ አመድነት የተቀየረበት ጊዜ ነበር ፤ ሕዝቡን እጅጉን ያስገረመው በውስጡ የነበሩት የእመቤታችን ፤ የቅዱስ ኡራኤልና ፤ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሀንስ ታቦታት ምንም ያለመሆናቸው ጉዳይ ነበር ፤ ከዚህ በተጨማሪ ማገሩን የበላው እሳት አባቶች ቅዳሴ ላይ የሚይዙት የእንጨት የነሀስና የብር መስቀሎች እና የተለያዩ ቅዱሳት መጻህፍት ምንም እሳት ሳይነካቸው መገኝታቸው በምዕመኑን ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል ፡፡

አዲስ አበባ አጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስትያን ተቃጠለች


ዛሬ ጠዋት 2 ሰዓት ላይ የተነሳ ፎቶ

ሕወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ


ኢየሩሳሌም አርአያ
Tigray People Liberation Front Split
ዛሬ በመቀሌ ለአባላ ትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩ በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤ «ተቆርቋሪ ለሆናችሁ የትግራይ ተወላጆ በሙሉ፤ «ድርጅትህ ሕወሐት እስከ ዛሬ ታግላ እዚህ ደረጃ አድርሰሃለች። በተለይም የሁሉም ነገር አድራጊና ፈጣሪ የነበረው ባለ ራዕይው መሪህ በቅርብ ጊዜ አጥተኽል።