Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, June 9, 2012

የጣት አሻራ መረጃን ለደህንነት ተግባር ለመጠቀም ታቅዷል

ኢሳት ዜና:-
የኢትዮጽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥርን በጣት አሻራ ለማስደገፍ ባለፉት ሶስት ዓመታት እየሰበሰበ ያለውን በፎቶግራፍ የተደገፈ የአሻራ መረጃ ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለአገሪቱ ደህንነት ተቋም ሥራ ለማዋል ዕቅድ መኖሩን አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለጹ፡፡

ባለሥልጣኑ በሐምሌ ወር 2001 ዓ.ም የጣት አሻራ መሰብሰብ ሲጀምር ታሳቢ አድርጎ የነበረው የታክስ ሥርዓቱን ዘመናዊ በማድረግ ንግድ ውስጥ የሚገባውንና ያለውን በሙሉ መመዝገብና ግብር ከፋይ ማድረግ እንዲሁም በአንድ ሰው ስም ጭምር ተደጋጋሚ የንግድ ፈቃድ እያወጡ ግብር የሚሰውሩ አንዳንድ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ነበር፡፡በዚሁ መሰረት ሥራው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካለፈው ወር ድረስ የ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች የጣት አሻራ ከየመ/ቤቱ፣ከየቀበሌና ክፍለከተማዎች ተሰብስቦ፤ አብዛኛዎቹ ለ10 ዓመታት የሚቆይ የግብር ከፋይ መታወቂያ ደብተር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

ምንጫችን እንደሚሉት ይህንኑ መታወቂያ እንደብሔራዊ መታወቂያ ጭምር እንዲያገለግል በመወሰኑ በአሁኑ ሰዓት መታወቂያውን የያዙ ሰዎች እንደቀበሌ መታወቂያ በሰፊው የሚጠቀሙበት ሆኗል፡፡ በሌላ በኩል የሁሉም ዜጋ አሻራና ፎቶ ቀስበቀስ በዳታ ስለሚያዝ ወደፊት መረጃውን ለደህንነት ጉዳይም ለመጠቀም ዝግጅቱ መኖሩን ጠቁሟል፡፡ሆኖም ይህ ጉዳይ ለዜጎች ግልጽ አለመደረጉንም አመልክቷል፡፡

ባለስልጣኑ እስካሁን ከሰበሰበው አሻራ ውስጥ ወደ 2ሺ ተኩል ያህሉ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጽያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆኑ ታውቋል፡፡ ገዢው ፓርቲ እያንዳንዱን ዜጋ ለመቆጣጠር የሚያመች አሰራር መዘርጋቱንም ምንጫችን ጠቁመዋል። የጣት አሸራ ተግባራዊ እንደሆነ በርካታ ነጋዴዎች ተቃውሞ ማንሳታቸው ይታወቃል።

Friday, June 8, 2012

በዋልድባ ገዳም አካባቢ ማይጋባ በሚባል ቦታ ላይ በፌደራል ፖሊስና እና በአርሶ አደሩ መካከል በተነሳ ግጭት 15 ሰዎች ተገደሉ


ኢሳት ዜና:- ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
 የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ግጭቱ የተነሳው ግንቦት25 ሲሆን፣ የፖሊስ አባላቱ የአካባቢው አርሶአደሮች ቤቶቻቸውን እንዲያፈርሱ ሲጠይቁ አርሶአደሮች ለማፍረስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በተነሳ ግጭት ነው ፖሊሶችና አርሶአደሮች የተገደሉት።

በተመሳሳይ ዜና ደግሞ በዋልድባ አካባቢ በምትገኘዋ የዛሬማ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በትናንትናው እለት በርካታ መኪኖችን አግተው ውለዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ከወታቶች ጋር በፈጠሩት ግጭት በርካታ ወጣቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ60 በላይ ወጣቶች መታሰራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።

በሌላ በኩል ደግሞ የኢህአዴግ በዋልድባ ጉዳት ከአባላቱ ጋር ሳይቀር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል። ግንባሩ ያስታጠቃቸው ሚሊሺያዎች ሳይቀሩ በዋልድባ ገዳም ላይ የሚፈጸመውን በደል በመቃወማቸው፣ ግንባሩ ታጣቂ ሚሊሻዎች ትጥቅ እንዲፈቱ አዟል።  በጫራዱቃ  ቀበሌ  8 ታጣቂ ሚሊሺያዎች ብቻ ትጥቅ ሲፈቱ ሌሎች አንፈታም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።

 ከዋልድባ ጋር በተያያዘ በአካባቢው ያለው ውጥረት እንዳለ ነው። ሰኔ 21 በሚከበረው የቅድስት ማርያም በአል ላይ ግጭት ሊፈጠር ይችላል በሚል የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ከፍተኛ ቅኝት እያደረጉ ነው።

Netizen Report: Telecoms Edition


In countries whose governments disrespect free speech and privacy, the introduction of new telecommunications (telecoms) infrastructure generally creates a new layer of censorship and  surveillance. 

One of the latest examples is Ethiopia. Last week Ethio Telecom, the sole telecommunication service provider in Ethiopia, announced a plan to relaunch its 3G wireless network to improve the quality and speed of Internet connections. However Tor, a project which supports anonymous online communication, recently found that Ethio Telecom has deployed or begun testing Deep Packet Inspection (DPI) of all Internet traffic, and has also blocked Tor. The Tor team has since developed a workaround for users in Ethiopia.

This latest move to deepen censorship and surveillance comes on the heels of last month's ratification of the Ethiopian Telecom Service Infringement Law, which is meant to impede Internet telephony such as Voice over Internet Protocol (VoIP) calls and faxes. As the use of computer-to-telephone call services is expanding in Addis Ababa, legislators have argued that the trend not only threatens the profits of Ethio Telecom, but also poses a threat to national security. The law also  includes anti-terrorism and anti-defamation provisions, which bloggers fear will dampen free expression in Ethiopia's thriving blogging culture.  
Censorship
On the eve of the 23rd anniversary of the Tiananmen Square massacre, the Chinese government escalated its crackdown on discussion of the tragedy. Sina Weibo, the popular Chinese microblogging platform, banned the account of Japanese public TV channel NHK for posting for a message on Weibo about the Tiananmen anniversary. A large number of Hong Kong Facebook accounts were deactivated soon after they posted political messages about a candlelight vigil commemorating the massacre. [Note: The Netizen Report has learned that a Facebook executive told several activists that the reason for the deactivation was caused by a global technical problem which has now been fixed - and had nothing to do with local political events or actions. However, to our knowledge Facebook has made no public statement explaining what happened.]

Last week, Sina Weibo also introduced new rules to control its users. According to the rules, Sina will establish content requirements for Weibo posts and “community committees” to judge on cases violating these requirements. The system will operate on a points system, which will adjudicate the actions Sina will take to punish violations.

Last week, a netizen in China's northwestern province of Xinjiang was detained for 15 days for spreading the news of a youth’s death in a detention facility. To alert Chinese users of censorship, Google has announced that it will incorporate new tools into its search engine that indicate when sensitive search terms are typed in. Malaysia has amended its Evidence Act, shifting the burden of proof to website owners to prove their innocence and making them responsible for abusive or politically incorrect comments.

Malawi’s government removed an amendment to its penal code that would have banned all news content “not in the public interest,” bowing to pressure from the same press freedom advocates that prevented the amendment from being implemented after it was passed in 2010. The South African City Press was forced by the African National Congress to remove an image of a controversial portrait of President Jacob Zuma on its website.

Wikipedia Co-Founder Larry Sanger called for better awareness that some Wikipedia entries include adult content and advocates the creation of a pornography filter. Thuggery Bahraini human rights activist Nabeel Rajab, charged with inciting illegal rallies online, was released on bail last week, then arrested again this week. Fox News reports that agents at Israel's international airport have been requiring some people of Palestinian descent to open up their emails for search before being allowed into the country.

National policy
The Dutch parliament voted against the Anti-Counterfeiting Trade Agreement (ACTA), placing it back at the top of the agenda for the European Union (EU) parliament to determine whether 20 European signatory nations will be able to institute the treaty. Three EU committees also voted not to recommend adoption of the treaty, and the next vote by the EU’s Committee on International Trade on June 21 could determine the outcome of the final vote in July.

By the end of 2012, the European Commission will draft proposals to institute net neutrality, following a report that indicates between 20 and 50 percent of Europeans have their online access restricted by their Internet Service Providers (ISP). China’s CNNIC altered its policy and again will allow individuals to register domain names. The organization has not allowed individuals to register domain names since 2009.

Internet governance
Panelists and members of the United States (US) House of Representatives Energy and Commerce Subcommittee on Communications and Technology expressed opposition to expanding the United Nations’ control over the Internet. Such a move would hold profound and hazardous implications for the future of the Internet, said Vint Cerf, the computer scientist known as “the father of the Internet” for his work in the 1970s with the US Defense Department.

Digital freedom non-profit organisation Access is close to collecting 20,000 signatures on a petition for the International Telecommunications Union (ITU) requesting it not expand its control over the Internet. Technology researchers Jerry Brito and Eli Dourado have launched a new website, WCITleaks.org, a platform for the publication of leaked documents related to the ITU and its upcoming World Conference on International Communications to be held in Dubai in December 2012, at which proposals related to extending the ITU's authority over the Internet will be discussed.

The non-profit Internet Corporation for Assigned Names and Numbers (ICANN) has collected approximately 2,000 applications for new generic top-level domain names and will reveal the winners on June 13, with an appeal and dispute period to follow until August 12.

Internet activism
The Knight Foundation awarded a grant to a Miami-area high school project to connect online with undocumented immigrant students and let them know about their opportunities for higher education. Members of hacktivist groups Anonymous and Telecomix differ on their approach to helping protesters in nations such as Syria, yet the Swedish-based group Telecomix claims to have more of a defined political strategy.

Wikileaks Founder Julian Assange, who has been under house arrest in the United Kingdom for rape allegations, lost his case in a British court about whether he could be extradited to Sweden to face the charges. He will have to decide whether to request an appeal. Despite slow activity on the website because of recent legal and political troubles, the whistleblowing culture it helped galvanize continues.

Following Reddit’s 12-hour blackout in 2011 to protest the Stop Online Piracy Act (SOPA), Reddit’s founder Alexis Ohanian has partnered with the advocacy group Fight for the Future to form the Internet Defense League to bring attention to other efforts to expand Internet governance. They call the effort “a bat signal for the Internet” for other websites to cooperate with to advocate against legislation such as the Cyber Intelligence Sharing and Protection Act (CISPA) and to “make sure the Internet never loses- ever.”

Inspired by the electoral success of the digital liberty-focused Pirate Party in the recent German elections, some French citizens are seeking to establish their own version of the party ahead of parliamentary elections.

Privacy
According to the “When the government comes knocking, who has your back?” report surveyed by the Electronic Frontier Foundation, an independent ISP in California, Sonic.net, is the Internet company which provides the best protection over customers’ privacy against governments’ requests for user data. The European Commission is referring Germany to the European Court of Justice because the country has failed to implement a EU rule demanding the Internet and phone companies to keep records of users’ emails and phone calls.

Facebook has opened up a vote on users’ proposed changes to its “Statement of Rights and Responsibilities” and the social network's “Data Use Policy.” The vote started June 1 and will end at 9 am PDT on June 8. In order for the changes to be binding, over 30% of the Facebook user base must participate in the voting.

Cybersecurity
An article in the New York Times reveals that the US government and Israel coordinated an effort to undermine the Iranian nuclear program through the Stuxnet virus. Meanwhile, Iran announced that computers in the country have been attacked by a more harmful form of malware than Stuxnet, called “Flame.” The Flame virus is designed for cyber espionage rather than cyber warfare. The UAE and Saudi Arabia have also reported that they have detected the same virus in their computers. Simurgh, an important software used by the Iranian and Syrian Internet users to circumvent censorship has a malicious version, which plants backdoors in victims’ computers.  

Publications and studies
Written by Rebecca MacKinnon
 
Source link:  http://advocacy.globalvoicesonline.org/2012/06/07/netizenreport-telecom/

ለልማት የሄዱ ዲያስፖራዎች ፦”የመንግስት ያለህ!”እያሉ ነው

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
 “የመንግስትን የልማት ጥሪ አምነን ወደ አገራችን  ከገባን በሁዋላ  በሙስና እየተንገላታንና እየተሰቃየን ነው” ሲሉ  ለሪል ስቴት ግንባታ   ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑ  ዲያስፖራዎች  እሮሮ እያሰሙ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ  ዲያስፖራው ወደ አገሩ ገብቶ በኢንቨስትመንት አስንዲሳተፍ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያቀርቡ ሰምተን ነው ለዓመታት በምቾት ስንኖርባት አሜሪካ ለልማት ወደ አገራችን ያቀናነው ይላሉ-የ ጂ. ኤም.ኤ.ኤስ ሪል ስቴት አክስዮን ማህበር አባላት።

ከዚያም በአምስት ኪሎ ከድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት  የሚገኙትንና ንግድ ሥራ ሲያካሂዱባቸው የቆዩትን የቀበሌ ቤቶች በሪል ስቴት ለማልማት መደራጀታቸውን የሚናገሩት እነዚሁ የቀድሞ የዲያስፖራ አባላት፤ ለዚህም አስፈላጊ የሆኑትን መስፈርቶች በማሟላት ፕሮፖዛላቸውን  ለአዲስ አበባ ሊዝ ቦታዎች አፈፃፀም ጽህፈት ቤት ማስገባታቸውን ጠቁመዋል።

ጽህፈት ቤቱም ፦”ቦታው ለግንባታ የሚውል ከሆነ መስፈርቱን ስላሟላችሁ ቅድሚያ የሚሰጣችሁ እናንተ ናችሁ፤ ጥቂት ታገሱ” እያለ ሲያጉላላቸው መቆየቱን የጠቀሱት የአክስዮን አባላቱ፤”እኛ በህጋዊ መስመር ውሳኔውን እየጠበቅን ሳለ፤ ህግን በጣሰ አሠራር ለራዲካል አካዳሚ ባለቤት ለአቶ ገብረ ሥላሴ በየነ ተሰጥቷል ተባልን ብለዋል።

አቶ ገብረሥላሴ ያመለከቱት ከነሱ በሁዋላ እጅግ ዘግይተው እንደሆነ እና  ቦታውን ሊያገኙ የሚችሉበት ምንም ዓይነት የህግ  አግባብ እንደሌለ  ያስረዱት የአክስዮን ማህበሩ አባላት፤ “ቦታው ለነሱ አይገባም ከተባለ ግልጽ ጨረታ ሊወጣበት እንጂ በአቋራጭና በሙስና  ለማይገባው ሰው ሊሰጥ እንደማይገባ ተናግረዋል። -“አቶ ገብረ ሥላሴ  የተሰጣቸውንስ ትምህርት ቤት  መቼ በሥርዓት ተጠቀሙበት?”ሲሉም አክለዋል።

እንደ አክስዮን ማህበሩ አባላት ገለፃ አቶ ገብረሥላሴ  ከህግ አግባብ ውጪ ከፍ ያለ ጥቅም እያገኙ ያሉ ግለሰብ ናቸው።በባለቤትነት በሚመሩት በራዲካል አካዳሚ ግቢ ውስጥ የነበሩ ሁለት የቀበሌ ቤቶችን በህገ ወጥ መንገድ አፍርሰው ለራሳቸው እየተገለገሉባቸው ቢሆንም፤እስካሁን የጠየቃቸው አንድም ባለስልጣን የለም።

የአቶ ገብረስላሴ ራዲካክ አካዳሚ ከጀማሪ እስከ 12 ኛ ክፍል 300 ታዳጊ ወጣት ተማሪዎችን ያቀፈ ቢሆንም፤ ከዚያው በተጓዳኝ በህገ ወጥ መንገድ  ቢራ እንደሚያከፋፍል ተጠቁሟል። “ታዳጊ ወጣቶች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ውስጥ ቢራ ማከፋፈል ህጉ ይፈቅዳልን?” ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎቹ በአግራሞት ጠይቀዋል።

ከዚህብ ባሻገር በ አካዳሚው ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ከ300 የማይበልጡ ቢሆንም፤  ለሊዝ ቦርዱ የቀረበው መረጃ ከ 2000 እስከ 3000 የሚገመቱ ተማሪዎች እንደሚማሩ ተደርጎ ነው። “ይህ አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ እኛ በህጋዊነት የጠየቅነው ቦታ በአቋራጭ ለእርሳቸው መሰጠቱ እጅግ አሳዛኝ ነው ያሉት እኚሁ የቀድሞ ዲያስፖራዎች፤ በህገ-ወጥ አሰራር እና በሙስና ትስስር መብታችን ተነጥቋል ሲሉ ምሬት እያሰሙ ይገኛሉ።

ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ግንቦት 13 ቀን 2004 ዓ.ም ከወረዳ 6 ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በሚል የራስጌ አድራሻ ባለበት ወረቀት ላይ የተፃፈና- ቁጥር የሌለው፤ የግርጌ ማህተሙ ትክክለኛነትም አጠራጣሪ የሆነ  ደብዳቤ ከሦስት ቀን በፊት ከአንድ ግለሰብ  እንደተመለከቱ የሪል ስቴት አባላቱ ተናግረዋል። “ደብዳቤው ለኛ ለባለ አድራሻዎቹ ለምን በቀጥታ እንዳልተፃፈልን አልገባንም ያሉት” እኚሁ የቀድሞ ዲያስፖራ አባላት፤ የደብዳቤው ይዘት በአስር ቀናት ውስጥ ቦታውን እንድትለቁ” የሚል ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አመልክተዋል።

በሁኔታው እጅግ ያዘኑት የሪል ስቴት አባላቱ፦“በዚች አገር በህገወጥ አሰራርና በሙስና የሚፈፀመውን ተግባር ተመልክቶ የሚመለከተው አካል እርምጃ እንዲወስድልን አቤቱታችንን አሰሙልን” ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል አቤት ብለዋል።

የሪል ስቴት አክሲዮን ማህበር አባላቱ አክለውም፦“በአሜሪካን አገር የምንኖር ነበርን፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ዲያስፖራው ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲያለማ ጥሪ ሲያቀርቡ ሰማን፡፡ እኛም የጠ/ሚኒስትሩን ቃል አምነን  አገራችንን ለማልማትና ራሳችንን ለመጥቀም በሚል ገንዘባችንን ከሰከስን ። በመጨረሻም እንዲሁ ቀረን”ብለዋል።

“ከውጪ ከመምጣታችን በፊት፦ እንዴት ኢህአዴግን አምናችሁ ትሄዳላችሁ? ምኑን አምናችሁ ገንዘባችሁን ታፈሳላችሁ? በሚል  ከዲያስፖራው ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞን ነበር” ያሉት እነኚሁ የቀድሞ የዲያስፖራ አባላት፤ እኛ ግን ሄደን ማረጋገጥ አለብን ብለን መጣን። መጥተን የገጠመን ግን እጅግ አሳዛኝ ነው”ብለዋል።

አያይዘውም፦” የበታች ኃላፊዎች በሙስናና በህገወጥ አሠራር የተሳሰሩና የተመሳጠሩ ናቸው፡፡ አንዱ የሠራውን ጥፋት ሌላው ሊያርመው አይፈልግም፡፡ በየሄድንበት የመስተዳድር መዋቅር የሚደርስብን ማመናጨቅና ግልምጫ ያሳዝናል። አቤቱታችንንም መስማት አይፈልጉም፡፡ በህገወጥ መንገድ በተቀነባበረ የሐሰት ሰነድ መብታችን  ለሌላ አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ የጠየቅነውን ቦታ በህጋዊ መንገድ ለመውሰድ  ስንሞክር ፤በባለሥልጣን ለማስፈራራት ይሞከራል” በማለት  የሙስናውን መክፋትና ውስብስብ መሆን በዝርዝር አስረድተዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የ አቶ ገብረሥላሴ በየነን አስተያዬት ለማካተት የተደረገው ጥረት አልተሳካም። “በአገር ቤት በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የተመቻቸ ሁኔታ አለ” የሚለውን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮፓጋንዳ በመስማት በተለያዩ ጊዜያት ጥሪታቸውን አሟጠው ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑ የዲያስፖራ አባላት፤ በውስብስብ ቢሮክራሲና በሙስና ባዶ እጃቸውን ቀርተው ለጸጸት እየተዳረጉ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።
______________________________________________________________________

Thursday, June 7, 2012

አቶ መለስ ዜናዊ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ብራሰልስ ገቡ

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
አቶ መለስ ዛሬ በቤልጂየም ዋና ከተማ ብራሰል የተገኙት በህክምና ቀጠሮዋቸው መሰረት ነው። በአእምሮ እጢ በሽታ እንደተጠቁ የሚነገርላቸው አቶ መለስ፣  ብራሰልስ የገቡት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑትን አቶ ብርሀነ ገብረክርስቶስን አስከትለው መሆኑን ከኢምባሲ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደር ብርሀነ ከአቶ መለስ ጋር የመምጣታቸው ምክንያት ቀደም ሲል ለ10 አመታት ብራሰልስ በነበሩበት ወቅት የአቶ መለስን ህክምና ያመቻቹ ስለነበር ቀረቤታ አላቸው በሚል ነው። አቶ ብርሀነ ገብረክርስቶስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኢታ ሆነው ሲመደቡ፣ ዶ/ር ካሱ ኢላላ በእግራቸው እንዲተኩ የተደረጉት ለአቶ መለስ ባላቸው ታማኝነትና ህክምና ለመከታተል በሚመላለሱበት ወቅት ሚስጢር እንደሚጠብቁ ታምኖባቸው ነው።

አምባሳደር ብርሀኔ አምባሳደር ሆነው ብራሰልስ በነበሩበት ወቅት ይኖሩበት የነበረውን ቤት 360 ሺ ዩሮ በማውጣት በፈረንሳይ አገር በታወቁ የቤት ውስጥ ዲዛይነሮች አስውበው እንደነበረ ምንጮች ተናግረዋል። የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ ምንጮች ጠቁመዋል። አቶ መለስ ለመደበኛ ምርመራ በየሶስቱ ወሩ ብራሰልስ የግል ወይም ቻርተርድ አውሮፕላን ተከራይተው የሚመላለሱ ሲሆን ፣ የኢምባሲ ሰራተኞች እንኳ ስለ ጉዞአቸው ምንም አይነት መረጃ እንዳይኖራቸው ይደረጋል።

 ሆኖም ግን በኢምባሲው ውስጥ የሚሰሩ የተወሰኑ የአንድ ብሄር ተወላጆች አቶ መለስ ወደ ብራሰልስ ከማቅናታቸው በፊት  መረጃው አስቀድሞ እንደሚሰጣቸው የኢምባሲው ምንጮች ገልጠዋል። ከሁለት አመት በፊት የአቶ መለስን ብራሰልስ ለህክምና መመላለስ የግንቦት7 ራዲዮ በመዘገቡ ምክንያት አንድ የፊሊፒናዊ ዜግኔት ያላት የአምባሳደር ብርሀኔ ምግብ አዘጋጅና አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ሚስጢር አሳልፋችሁ ሰጥታችሁዋል በሚል ተወንጅለው ከስራ መባረራቸው ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል።

አቶ መለስ ዛሬ ጠዋት ብራሰልስ ከገቡ በሁዋላ ሀኪማቸው ጋር እስከተገናኙበት ከሰአት በሁዋላ ድረስ ቀደም ሲል አምባሳደር ብርሀኔ ባሳደሱት ቤትና አሁን ካሱ ኢላላ በሚኖሩበት የአምባሳደሩ መኖሪያ ተኝተው እንደዋሉ ምንጮች ገልጠዋል። የአቶ መለስ በፍጥነት ወደ ብራሰልስ መምጣታቸውም ከሰሞኑተቃውሞ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ምንጮች ጠቁመዋል።

አቶ መለስ  ከጤናቸው ጋር በተያያዘ ከሶስት አመታት በሁዋላ ስልጣናቸውን ሊለቁ ይችላሉ የሚሉ ዘገባዎች እየቀረቡ ቢሆንም፣ ኢህአዴግ  አቶ መለስ በስልጣናቸው እንዲቀጥሉ ማስታወቂያ ማስነገር መጀመሩ የኢህአዴግን አባላት ሳይቀር ግራ እያጋባ ነው።

አቶ መለስ  በአእምሮ እጢ በእንግሊዝኛው አጠራር ብሬን ቲሞር በሽታ እንደሚሰቃዩ ይታወቅ እንጅ የበሽታው የአሳሳቢነት ደረጃ ምን ያክል እንደሆነ ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። አቶ መለስ ከአምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ ቀጥሎ ወዳጅ አድርገው የሚያቀርቡት ዶ/ር ካሱ ኢላላን እንደሆነ ይነገራል።
አቶ በረከት ስምኦንም በአእምሮ በሽታ እንደሚሰቃዩ ፣ ከምርጫ 97 በሁዋላ በደቡብ አፍሪካ ተገኝተው ህክምና ሲከታተሉ እንደነበር ይታወቃል። በቅርቡ ሼህ ሙሀመድ አላሙዲን አቶ በረከት በደቡብ አፍሪካ ህክምና ሲከታተሉ ወጪያቸውን እንደሸፈኑላቸው መናገራቸው ይታወሳል።

Wednesday, June 6, 2012

የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚተላለፈውን ስርጭት ለማቋረጥ ዝግጁ መሆኑን መግለጡ ታወቀ

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት የኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄውን ያቀረበው ለአረብሳት ነው።   መንግስት በመጀመሪያ በአረብ ሳት ሲተላለፍ የነበረውን  ኢሳትን ፣ ቀጥሎም የኤርትራን ቴሌቪዥን ለማፈን ሙከራ ማድረጉን ተከትሎ፣ ከአረብ ሳት ባለስልጣናት ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር።

 የአረብ ሳት ባለስልጣናትም የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ሲያስጠነቅቁት ቆይተዋል። ይሁን እንጅ መንግስት ከዚህ ድርጊቱ ሊቆጠብ ባለመቻሉ የአረብሳት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን እና የኤርትራን የአረብሳት ስርጭቶች እንዲቋረጡ አድርገዋል። ውዝግቡን በንግግር ለመፍታት ጥረት ያደረጉት የአረብሳት ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ መንግስት ያገኙት መልስ አሳዝኖአቸው እንደነበር ታውቋል።

 የኢትዮጵያ መንግስት ኢሳትን የመሳሰሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ዝግጅቶች በአረብ ሳት በሚተላላፈው የኤርትራ ቴሌቪዥን ላይ የማይቀርቡ ከሆነ ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ የሚተላለፈውን ስርጭት ለማቋረጥ ዝግጁ ነኝ የሚል ቅድመ ሁኔታ ለኩባንያው ቢያቀርብም የኤርትራ መንግስት ግን የኢትዮጵያን ቅድመ ሁኔታ አልተቀበለውም። የኤርትራ መንግስት  ” የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ኤርትራ የሚልከውን ስርጭት ከፈለገ ከአንድ ሰአት ወደ 24 ሰአት ማሳደግ እንደሚችል እና በስርጭቱ ምንም እንደማይከፋ፣ በጣቢያው ላይ የሚተላላፉ ዝግጅቶችን የሚወስነው ግን ራሱ መሆኑን በመግለጥ የኢትዮጵያን መንግስት መደራደሪያ ውድቅ አድርጓል።

በኢትዮጵያ መንግስት አቋም የተበሳጩት የአረብ ሳት ባለስልጣናት ለ4 ወራት ያክል በራቸውን በመዝጋት የኢትዮጵያን መንግስት ባለስልጣናት ለመቀበል አሻፈረን ብለው ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ከአራት ወራት ልመና በሁዋላ  ለአረብ ሳት ባለስልጣናት ከአሁን በሁዋላ አፈና እንዳማያካሂዱ የጽሁፍ ማረጋጋጫ በመስጠታቸው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  ወደ አየር እንዲመለስ ተፈቅዶለታል።

አንድ የአረብ ሳት ባለስልጣን ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ከተገናኙ በሁዋላ በባለስልጣኖቹ ድርጊት ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሁኔታ ማዘናቸውን መናገራቸውን ምንጮች አስታውቀዋል። የኤርትራ ቴሌቪዥን የኢሳትን ስርጭት ከኢንተርኔት ላይ በመውሰድ አልፎ አልፎ እንደሚያሰራጭ ይታወቃል።

አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግስት ፕሬሱን ለማፈን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ አውግዘዋል። የመለስ መንግስት ግን ሳተላይት ስርጭቶችን ከማፈን አልፎ በአገር ውስጥ የሚታተሙ አነስተኛ ስርጭት ያላቸውን ጋዜጦች ሳይቀር ለመቆጣጠር አዲስ የማተሚያ የንግድ ውል ማውጣቱ ይታወቃል።

 በኢንተርኔር የሚሰራጩትን መረጃዎች ለማፈንም አዲስ የቴሌ ህግ በማርቀቅ ላይ ይገኛል። 99 ነጥብ 6 በመቶ የሆነ የህዝብ አመኔታ አግኝቼ ተመርጫለሁ የሚለው የመለስ መንግስት  ፣ ነጻ ሀሳብን ከሚያፍኑ የአለም አገሮች መካከል በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳል።

በደብረ ይድራስ ቅ/ጊዮርጊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን የተሰማራው ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ይዞ ቤተ መቅደስ ገባ

·        በአስለቃሽ ጢሱ ጸሎተ ቅዳሴው ታጉሏል፤ ሕፃናት፣ ምእመናንና አገልጋዮች ታፍነዋል::
·        ለውዝግቡ መፍትሔ ያፈላልጋል የተባለ ጥምር ኮሚቴ ተቋቁሟል::
·        ከ70 - 80 የሚደርሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን እንደታሰሩ ናቸው::
·        ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ሊቀ ጳጳሱን በስልክ አነጋግረዋል::
By Dejeselam news
(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 29/2004 ዓ.ም፤ ጁን 6/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከይዞታ ማስከበር ጋራ በተያያዘ ትናንት፣ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በአጥቢያው ምእመናን መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ በግጭቱ የአንድ ፖሊስ ሕይወት አልፏል፤ ስድስት ፖሊሶችና በርካታ ምእመናንም ተጎድተዋል፤ ብዙዎቹን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላትንና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ በቁጥር ከ70 - 80 የሚሆኑ የአጥቢያው ወጣት እና አዛውንት ምእመናን ከየመንደሩ በፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሰበሰቡ መታሰራቸው ነው የተነገረው፡፡

ግጭቱ እየቀጠለ በነበረበት ኹኔታ ለጸሎተ ቅዳሴ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለመበተን በሚል ፖሊስ ወደ ቤተ መቅደሱ ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተመልክቷል፤ በዚህም በመካሄድ ላይ የነበረው ጸሎተ ቅዳሴ ታጉሏል፤ ለቍርባን የተዘጋጁ ሕፃናት፣ ሌሎች ምእመናንና አገልጋዮችም በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የሕን ቤተ ክርስቲያኑ በሮችና መስኰቶች መንሥኤው ለጊዜው ባልታወቀ ኹኔታ የተበሳሱና የተሰባበሩ ሲሆን የደብሩ አስተዳደር ቢሮዎች፣ የጥምቀተ ክርስትና ቤትና ሌሎችም በሮች “የተደበቁ ሰዎችን ለማሰስ” በሚል መዝጊያዎቻቸው እየተሰበረ ፍተሻ እንደተካሄደባቸው ተገልጧል፡፡

ከንቲባ ኩማ ደመቅሳና ‹የፓትርያሪኩ ልዩ ሀገረ ስብከት› በሚል ከሚታወቀው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የረዳት ሊቀ ጵጵስና ሓላፊነታቸው እየለቀቁ ያሉት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በጉዳዩ ላይ በስልክ መነጋገራቸው ተሰምቷል፤ በግጭቱ አንድ ፖሊስ መሞቱንና ሌሎች ስድስት አባላት መቁሰላቸውን የተናገሩት ከንቲባ ኩማ የታሰሩት ምእመናን እንዲፈቱ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ እንዳልተቀበሉ ተሰምቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት የደብሩ የክብረ በዓል (ንግሥ) እና መስቀል ደመራ ፍራ የነበረውን ይዞታ የቀበሌ 06 ጽ/ቤት (የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ) ለመከለል የጀመረው ሂደት እንዲቆም ተደርጎ ውዝግቡን የሚያጣራ ኮሚቴ መቋቋሙ ተነግሯል፡፡ ኮሚቴው ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ፣ ከአጥቢያው ምእመናን፣ ከክፍለ ከተማው አስተዳደርና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የተውጣጡ አባላት የሚገኙበት ነው፡፡ ግጭቱ ትናንት ጠዋት ከመቀስቀሱ ቀደም ብሎ የአጥቢያው አስተዳደር፣ አገልጋዮችና ምእመናን በፖሊስ ታጅቦ የመጣውን ግብረ ኀይል በባንዲራው እያሉ ሲማፀኑ ነበር፤ እነርሱ ራሳቸው ይዞታቸውን ለማስከበር በተደጋጋሚ ሲያመለክቱበት የቆዩበትና አሁንም ከፓትርያኩ ጋራ እየተነጋገሩበት በመኾኑ ግብረ ኀይሉ ወደ ርምጃ ከመግባቱ አስቀድሞ ሁለት ቀናት እንዲሰጣቸው ሲጠይቁም እንደ ነበር ተዘግቧል፡፡ 

ምእመናኑ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ለሚያቀርቡት ተማኖ ቦታ ያልሰጠው ግብረ ኀይሉ ግን አጥሩን ወደ ማፈራረስና ችካል ወደ መቸከል ተግባር በመግባቱ ምእመናኑ ርምጃውን ድንጋይ በመወርወር ሲከላከሉ የአድማ ብተና ፖሊስ ደግሞ በቆመጥና በአስለቃሽ ጭስ ምእመናኑን ለመበተን መሰማራቱ ተገልጧል፤ ጥይትም ተተኩሷል፡፡ የችካል ምልክቱ የሚያርፍበት ቦታ ከዐውደ ምሕረቱ ያለው ርቀት ከኀምሳ ሜትር እንደማይበልጥ የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ የደብሩ አስተዳደር በዚህ ይዞታው ላይ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታና በሌሎችም ትልሞች የራሱን የራስ አገዝ ልማት ዕቅዶች ለማካሄድ ሲንቀሳቀስ እንደ ነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙ በርካታ አድባራትና ገዳማት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዳገኙ ተዘግቧል፡፡ በአንዳንዶቹም÷ ለአብነት ያህል በኮተቤ ደብረ ልዑል ቅዱስ ገብርኤል÷ የቤተ ክርስቲያን ይዞታ ለግለሰብ ጥቅመኞችና ለፕሮቴስንታቶች በመሰጠቱ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የየካ ክፍለ ከተማ ችግር ከመፈጠሩ በፊት በጉዳዩ እንዲያስብበት ያቀረበው ጥያቄ ይገኝበታል፡፡ 

በደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንም የትናንቱ ችግር በተዘገበው ደረጃ እንዲባባስ ያደረገው አሁን እስከ ዐውደ ምሕረቱ የዘለቀው የይዞታ ነጠቃ ብቻ ሳይሆን የቀበሌው ጽ/ቤት ቀደም ብሎ የደብሩ ካህናት መኖሪያ ቤት ተሠርቶበት የነበረውን ቦታ በመውሰድ ኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ጽ/ቤት ሲሠራበት በዝምታ በመታለፉ መሆኑን አስተየየታቸውን ለዜና ሰዎች የሰጡ የሰበካው ምእመናን ገልጸዋል፡፡ 

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ (ከፍተኛ 24 ቀበሌ 14 59 ቁጥር ማዞርያ) አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ አካባቢ የሚገኘው የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከ23 ዓመት በፊት፣ በ1981 ዓ.ም የተመሠረተ ደብር ነው፡፡ይድራስ የዱድያኖስ ጭፍሮች የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስን ዐፅም አቃጥለውና ፈጭተው የበተኑበት ተራራ ስም እንደ ኾነ ይታወቃል፡፡

Source link:  http://www.dejeselam.org/2012/06/blog-post_4568.html#more

Tuesday, June 5, 2012

በሰሜን ጎንደር ፍጥጫው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሳት ዜና:-
ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር ህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ፣ ሊፈነዳ መቃረቡን ዘጋቢዎች ከስፍራው ገልጠዋል።

የአካባቢው ህዝብ ስንቁን እየያዘ ወደጋዳሙ በመትመም ላይ ሲሆን፣ መንግስትም በደባርቅና አካባቢው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሰራዊቱን በትኖአል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው፣ በህዝቡና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ በመጨመሩ ምናልባትም ሰኔ 21 ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጠዋል። የአገር ሽማግሌዎች፣ ቀሳውስቱና ታዋቂ ሰዎች ችግሩን ለመፍታት በዛሬማ ወንዝ አካባቢ ውይይት እያደረጉ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ መፍትሄ ላይ ሊደርሱ አልቻሉም። 

የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን ችግሩ በውይይት የሚፈታ አይሆንም። መንግስት ድርጊቱን እስካላቆመ ደረስ ተቃውሞው ይቀጥላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ 5 ካህናት በደባርቅ መታሰራቸው ታውቋል። በቅርቡ ስለሺ ጥጋቤነህ የተባለ የደባርቅ ነዋሪ መታሰሩ ይታወሳል።

ግንቦት 20ን ለማክበር 120 ሚሊዮን ብር መውጣቱ ተጠቆመ

By finote Netsanet news, second years, no. 45
ኢህአዴግ 21ኛውን የግንቦት 20 በዓል ለማክበር ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ ምንጮቹ እንደሚሉት ኢህአዴግ በዓሉን ለማክበር ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቷል፡፡ ምንጮቻችን አክለውም “በዓሉ በየአባል ድርጅቶቹና በየመሠረታዊ ድርጅቶች እንዲከበር ተደርጓል፡፡

በዝግጅት ላይም የጋባዥና ተጋባዥ ኮሚቴ ተዋቅሮ በጀት ተመድቦ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በዓሉ በገንዘብ ብዛትና ለጥቅም ሲባል በተሰበሰቡ ሰዎች እንጂ በዓሉን በእምነት አላከበሩም፡፡” ብለዋል፡፡ 

አያይዘውም በተለይ የኦሮሚያ የግንቦት 20 በዓል የተከበረው በከፍተኛ የገንዘብ ወጪ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ እነዚህ ታማኝ የዜና ምንጮች እንደሚሉት “ሰዎችን ጋብዞ ላመጣ አንድ ሺ ብር፣ ለፎረም አባል 600 ብር፣ ለቀበሌ ቀስቃሽ 300 ብር፣ ለሰልፈተኛ መቶ ብር እየተከፈለ የተሰበሰበ ነው፡፡

 ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚውል ለኦሮሚያ ብቻ 30 ሚሊዮን ብር መመደቡን” ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት “ግንቦት 20 እንዲከበር ከፍተኛ ገንዘብ ቢወጣበትም ተሰብሳቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥርዓት እየሆነ በመጣው ሙስና፣ የመልካም  አስተዳደር እጦትና ኦሮሚያ ከሞግዚት አስተዳደር አለመውጣት ቅሬታ ሲያሰሙ ተደምጧል፡፡ እንዲያውም ለሥራ ነው እንጂ ኦሮሚያ መኖሬ፣ የከፋኝ ዕለት እማ ትግራይ ነው አገሬ” የሚል ግጥም ሲነገር መደመጡን በሥፍራው የነበሩት ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

 በሌላ በኩል ግንቦት 20 በዓል ማለዳ ላይ በመስቀል አደባባይ ለማክበር የተደረገው ጥረት ለመሳካቱን ሪፖርተራችን ዘግቧል፡፡ በዕለቱ እስከ ሦስት ሰዓት ድረስ በመስቀል አደባባይ የነበረው ህዝብ ከ300 ሰው የማይበልጥ ሲሆን እነሱም “አቶ መለስ ይመጣሉ ውጡ ተብለን መተን በፀሐይ ያስደበድቡናል” በማለት ተበሳጭተው ተበትነዋል ሲል ዘግቧል፡፡ መንግስት ለቦንድ ግዢ የሰራተኞችን አቅም ያላገናዘበ የግዳጅ ሽያጭ እያደረገ ባለበት ወቅት ስልጣን የያዘበትን ቀን ለማክበር ለአንድ ቀን ይህን የሚያክል ወጪ ማውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በቤንች ማጂ ዞን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ

                   - ግጭቱ አሁንም አልበረደም
 By Finote Netsanet news no. second year, no.45
በቤንች ማጂ ዞን ሜኒኑ፣ ጉልዲያ፣ ሜኒትሻሻ፣ ቤሮ፣ እሹርማ እና በኮይ ወረዳዎች ለወራት የቀጠለው ግጭት ዳግም ማገርሸቱን የአካባቢው ምንጮች ጠቆሙ፡፡ 

በተለይ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት በጥምረት በሚቆጣጠሯቸው ኮይ እና ቤሮ ሻሻ አካባቢዎች ከፍተኛ የፀጥታ ችግር እንዳለ የሚናገሩት ምንጮቻችን ግጭቱ ያገረሸው ግንቦት 12 ቀን 2004 ዓ.ም በአካባቢው ቢራ እና ለስላሳ የሚያከፋፍሉ አቶ አብርሃም የተባሉ ግለሰብ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱት ታጣቃዎች መገደላቸውን ተከትሎ እንደሆነ ዘግበዋል፡፡

ፍኖተ ነፃነት ያነጋገረቻቸው አንድ የዞኑ ባለስልጣን በአካባቢው አሳሳቢ የሆነ የፀጥታ ችግር እንዳለ አምነው፣ ችግሩ ከአራት ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ተናግረዋል፡፡ እኚሁ የዞኑ ባለስልጣን ጨምረው እንደ ገደለፁት ካለፉት አራት ወራት ወዲህ መኪናዎች ወደ ተለያዩ የወረዳ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ በመንግስት ታጣቂዎች እንደሚታጀቡ አብራርተዋል፡፡ ባለሥልጣኑ እንደሚሉት የዞኑ የፀጥታ ችግር ከቁጥጥር ውጪ በመውጣቱ በአካባቢው የሚገኙት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት አካላት እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ባደረጉት ማጣራት እንደሞከሩት የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት ከመጠን ያለፈ ኃይል ተጠቅመው አካባቢውን ለማረጋጋት ሞክረዋል፡፡ ምንጮቻችን በዚህ የኃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ ከተባባሰባቸው አካባቢዎች ሸሽተው የወጡ ነዋሪዎች ለምንጮቻችን እንደገለፁት በየቀኑ ከአስር እስከ አስራ አምስት ሰዎች በግጭቱ ይገደላሉ፡፡ በአካባቢው የሚወጣውን የወርቅ መአድን ለመቆጣጠር የሚፈልጉ ከ15 በላይ የሚሆኑ ታጣቂ ሀይሎች በዞኑ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ከአካባቢው ያሰባስብናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ 

በተያያዘ ዜና በአካባቢው ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ ከሚዛን ከተማ ወጪ ባሉት የዞኑ አካባቢዎች የስልክ ግንኙነት መቋረጡ ታውቋል፡፡ ከግንቦት 18 ጀምሮ የተቋረጠው የስልክ ግንኙነት በአካባቢው ያለውን ግጭት አደገኛነት የሚጠቁም መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ፍኖተ ነፃነት ስለ ግጭቱ መንግስት የሚያቀው መረጃ እንዳለ የተጠየቁት የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል የደረሳቸው መረጃ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ፍኖተ ነፃነት የክልሉ ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ ሀሰንን ለማግኘት ያደረገችው ጥረት ስልካቸው ባለመስራቱ ምክንያት አልተሳካም፡፡

በጐንደር ፖሊስ የሟቾችን አስክሬን በመኪና መሬት ለመሬት አስጐተተ

 By Finote Netsanet news
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ጐንደር ዞን ታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ በተኩስ ልውውጥ የተገደሉ ሁለት ሰዎች አስከሬን በመኪና ላይ ታስረው ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት መጐተቱን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ 

የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት “አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው አያሌው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጐተት ውሏል”
ብለዋል፡፡ ምንጮች እንደሚሉት “አቶ ዳኛቸው አያሌው ከአንድ ግለሰብ ጋር በመጋጨቱ አካባቢውን ለቆ ሄዷል፡፡ ከመንግስት ጋር ፀብ አልነበረውም፡፡ ከዚያም ታጣቂዎች ሸፍተዋል በማለት ይገኛሉ የተባለበትን አካባቢ በመክበብ ተኩስ ከፈቱ፡፡ ሟቹም የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ሞቱ፡፡ መቀጠልም አስክሬናቸውን በመኪና ላይ አስረው በከተማ ውስጥ ከ8-11 መሬት ለመሬት ከጐተታቸው በኋላ መሐል አራዳ ላይ ጣሏቸው፡፡ ህዝብ እንዲመለከታቸው አደረጉ፡፡ አስክሬኑን ሲመለከቱ የመንፈስ ጭንቀት ተፈጥሮባቸው የጮሁ ያለቀሱ ሰዎች በፖሊስ ቆመጥ ተደብድበዋል” ይላሉ፡፡

በማያያዝም ሲናገሩ “የአቶ ዳኛቸው አያሌው አባት፣ እናትና አያትም በሥፍራው ነበሩ፡፡ አስከሬኑን ወስደው ለመቅበር ቢጠይቁ ተከልክለዋል፡፡ በ11 ሰዓት ላይ እግራቸው ላይ ገመድ አስረው ከፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ዛፍ ላይ ሰቅለው ዘቅዝቀው አሳደሯቸው፡፡ በማግስቱ እንዲቀበሩ ሲወሰን ቤተሰብና የአካባቢው ህብረተሰብ ቤተክርስቲያን ለመቅበር ቢጠየቅ የአካባቢው ኃላፊዎችና ፖሊሶች ቤተክርስቲያን አይቀበሩም ብለው ከልክለው ሌላ ቦታ እንዲቀበሩ አድርገዋል፡፡” በማለት
በቅሬታ ይገልፃሉ፡፡

ምንጮች በመጨረሻም ሲናገሩ “የአካባቢው ህብረተሰብ እጅግ አዝኗል፡፡ በተለይ ከግድያው በኋላ ፖሊሶች በአስከሬኖቹ ላይ የፈፀሙት ድርጊት ከባህልና ወግ ያፈነገጠ ከሰብአዊ አስተሳሰብ የወጣ በመሆኑ እናዝናለን፡፡ ማንም ሰው በሠራው ወንጀል በሞትም ሊቀጣ ይችላል፡፡ አስክሬን ግን ክብር አለው፡ ፡ የቀብር ቦታም መከልከል ህገወጥ ተግባር ነው፡ ፡ አስክሬን ዘቅዝቆ ሰቅሎ ማሳደርስ ምን ማለት ነው? ይህንን ድርጊት የፈፀሙም ያስፈፀሙም በህግ ሊጠየቁ  ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሳንጃ ከተማ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልካቸውን ስለማይነሳ ዜናውን ለጊዜው ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡

በተያያዘ ዜና በዚሁ በሰሜን ጐንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብረሃ ጅራ ከተማ ዙሪያ “ለረጂም ዓመታት የቆየው የመሬት ግጭት አሁን በተባባሰ ሁኔታ ፍጥጫ መፍጠሩን” ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት “አካባቢው ከሱዳን ጋር ድንበር ነው፡፡ መንግስት የአካባቢውን መሬት ለሱዳኖች ማስረከብ ይፈልጋል፡፡ 

የአካባቢውን ህብረተሰብ ድንበሩን ለማስከበር ከሱዳኖች መሬቱን ሲከለከል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሱዳን ወግኖ የራሱን ዜጋ ይወጋል፡፡ በአካባቢው ያለው የመከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ለሱዳን ቆሞ ኢትዮጵያኖች ምንም ዓይነት የመከላከል ሥራ እንዳይሰሩ እያደረገ ነው፡፡” በማለት በአግርሞት ይገልጹታል፡፡

ምንጮች በመቀጠልም ሲገልጹ “ሰሞኑን መንግስት በተጨማሪ ለውጪ ዜጐችና ለባለሀብቶች ለመስጠት እቅድ ይዟል፡፡ ለእያንዳንዱ ገበሬ አንድ ሄክታር መሬት ብቻ ለመስጠት በማቀድ መሬት እያሸጋሸገ ነው፡፡ አንዱ ለፍቶ ያለሰለሰውን እርሻ ለሌላው ይመድባል፡፡ ገበሬው ግን አንዱ የአንዱን እርሻ ላለማረስ ቃል ተገባብቷል፡፡ የአካቢው ኃላፊዎች ግን እንዲያርስ እያስገደዱት ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት ከሁለት ቀን በፊት ለሊት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ፖሊስ ጣቢያውንናቀበሌ መስተዳደሩን ጽ/ቤት አቃጥለውታል፡፡ በዚህ የተነሳ የአካባቢውን ህብረተሰብ እየሰበሰቡ እያሰሩና እየደበደቡ ናቸው፡፡ የአካባቢውን ህዝብ ወደ መጥፎ  ድርጊት እየገፋፋት ነው፡፡ ህዝቡ በኩርፊያ ሥራቸውን በተጠንቀቅ ቆሞ እየተከታተለ ነው፡፡” ሲሉ ያብራራሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ “ፖሊስ ጣቢያውንና የቀበሌውን መስተዳድር ያቃጠሉት ምናልባትም ከመሬት ጋር በተያያዘ በሙስና የተነካኩ ግለሰቦች መረጃ ለማጥፋት የሠሩት ሥራ ነው፡፡” በማለት ጥርጣሬአቸውን ይገልፃሉ፡፡ ከመሬት ድልድሉ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን መሬት ከሌላ ቦታ ለመቱ ሰዎች እየተሰጠ በመሆኑ የአካባቢው ሊቀመንበርና ቅሬታ ሰሚ በጉዳዩ ባለመስማማት አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ሄደዋል” ይላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ መሬቱን የሚሸነሽኑት የመሬት አስተዳደሩና የወረዳው ፀጥታ ኃላፊውች ናቸው በማለት ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ግንቦት 20 ህዝቡ ከወጣ አይመለስም ተብሎ እንዳይከበር ሰሞኑን በደረሰን ዜና በዚሁ በሰሜን ጐንደር ተቃዋሚዎች
በህገወጥ መንገድ እየታሰሩ መሆናቸው ተጠቁሞአል፡፡

 ምንጮች እንደሚሉት “በምርጫ 2002 መኢአድን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተወዳዳሩ እየታሰሩ ናቸው፡፡ ከታሰሩት ውስጥ ታደለ ተፈራ የሰሜን ጐንደር የመኢአድ ም/ቤት ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ ስለሺ ጥጋቤ የጀናሞራ ወረዳ መኢአድ ኮሚቴ ሰብሳቢ መለስ አስሬ የጭልጋ ወረዳ መኢአድ ሰብሳቢ ሆነው ሲታገሉ የቆዩ ሲሆን ባለፈው ሐሙስና ዐርብ ምሽት በእያንዳንዱ ሰው ቤት ከአስር በላይ ፖሊሶች ተገኝተው ቤታቸውን እየበረበሩ አስረዋቸዋል፡፡” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ 

የእስረኞቹ ቤተሰቦች እንደሚሉት “ፖሊሶቹ የፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዳላሳዮቸውና ድርጊቱ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ በምሽት መከናወኑና እስረኞቹ የታሰሩበት ቦታ አለመታወቅ እንዳሳሰባቸው” ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡ እስረኞቹ ይገኙበታል ተብሎ የነበረው ደርጊ ፖሊስ ጣቢያና ጐንደር ፖሊስ ደውለን ለመጠየቅ ጥረት ብናደርግም ዜናውን ሚዛናዊ ማድረግ አልተቻለም፡፡

Monday, June 4, 2012

የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅፀደቀ

በኢንተርኔት ሰልክ መደወል እሰክ 8 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሰራት ያስቀጣል

ከኢኮኖሚያዊ ኪሣራ ባሻገር የአገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስጋት ሆኗል በተባለው የቴሌኮም ማጭበርበር ላይ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ያፀደቀው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያመለክተው፤ ከኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም አይነት የቴሌኮሚኒኬሽን መሣሪያ ማምረት፣ መገጣጠም፣ ከውጭ ሀገር ማስመጣት፣ መሸጥ እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 150ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡ 
 
በፀረሽብርተኝነት አዋጅ ከሚያስቀጣ ወንጀል ጋር የተያያዘ ሽብር የሚያስከትል መልዕክት ለማሰራጨት ወይም በወንጀል ህግ የሚያስቀጣ አስነዋሪ መልዕክቶችን ለማሰራጨት በማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያና ኔትወርክ መጠቀም እስከ ስምንት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 80 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡
 
ምክር ቤቱ ያፀደቀው አዲሱ አዋጅ፤ ኢንተርኔትን በመጠቀም የስልክ ጥሪ ወይም የፋክስ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውንም ሰው በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከ3 ዓመት እስከ ስምንት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በስልክ ጥሪዎቹ ሊያገኝ ይችላል ተብሎ የሚገመተውን ገቢ አምስት እጥፍ በሚሆን መቀጫ ይቀጣል፡፡ በኢንተርኔት ስልክ በመደወል ተግባር ላይ የተሳተፈ ወይንም የስልክ ግንኙነቱን ያደረገው ሰው ደግሞ እስከ 2 ዓመት በሚደርስ እስራትና እስከ ብር 20ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይወሰንበታል፡፡ ፍርድ ቤት በጥፋተኞቹ ላይ ቅጣት በሚወስንበት ወቅት ወንጀሉን ለመፈፀም በጥቅም ላይ የዋለ ማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያ በመንግስት እንዲወረስ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ 
 
በፀደቀው አዋጅ መሰረት፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎች የመጀመሪያ ደረጃ የመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲሆን የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሉ ለመፈፀሙ ወይም ሊፈፀም ለመሆኑ ፖሊስ ካመነ በድብቅ የሚደረግ የብርበራ ማዘዣ ፈቃድ ከፍርድ ቤት አውጥቶ ለመበርበር እንዲችል ስልጣን ሰጥቷል፡፡
 
 በህገወጥ መንገድ ሲምካርድ፣ ክሬዲት ካርድ፣ የደንበኞች መለያ ቁጥር ወይም ዳታ  የሚሰራ ወይም የሚያባዛ ወይም በህገወጥ መንገድ የተባዙትን ሲም ካርዶች፣ የደንበኞች መለያ ቁጥሮች ወይም ዳታዎች የሚሸጥ ወይም በማናቸውም መንገድ የሚያሰራጭ ማንኛውም ሰው በወንጀሉ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ፤ እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና 150ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡
 
 የቴሌኮም የማጭበርበር ወንጀል የብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥልና ዜጐች በመንግስታቸው ላይ አመኔታ እንዲያጡ የሚያደርግ ከባድ ወንጀል መሆኑን የጠቀሰው አዋጁ ፤ወንጀሉ ለተለያዩ የሽብር ሃይሎች መጠቀሚያ መሆኑን፤ አሠራሩ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ እንዲሆን በማድረግ ተደራራቢ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት እጅግ ሥር የሰደደ አደጋ እንደሆነ ገልጿል፡፡
 
አለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን የአገር ውስጥ በማስመሰል (ኮልባክ) ወንጀል በየዓመቱ በበርካታ ሚሊዮን የሚገመት የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ እንድታጣ እያደረጋት መሆኑን የጠቆመው አዋጁ፤   በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑትን እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲሁም በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች እስከ 2 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ይደነግጋል፡፡

 ህገወጥ የቴሌኮም መሣሪያዎችን በሲስተሙ ላይ በመግጠም ድርጅቱ በአንድ የስልክ ጥሪ ማግኘት ከሚገባው ገቢ 83 በመቶ ያስቀራል በተባለውና ህገወጥ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ከውጭ በማስገባት ከአገሪቱ የቴሌ ሲስተም ሳይገናኝ ራሱን የቻለ የቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ለመፍጠር ያስችላሉ የተባሉት ወንጀሎች በአዋጁ በአደገኝነታቸው ከተለዩ ወንጀሎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

Source: Esat news

Ethiopia: Food for Famine and Thought!

The New Alliance for Food Security and Nutrition
At the recent 2012 G8 Food Security Summit in Washington, D.C., Abebe Gellaw, a young Washington-based Ethiopian journalist, stood up in the gallery and thunderously proclaimed to dictator Meles Zenawi, “… Food is nothing without  freedom…” Is he right? When President Obama invited the leaders of Ghana, Tanzania, Benin and Zenawi to the Summit  on May 18, few expected any meaningful outcomes.

A White House statement on the Summit declared: “The New Alliance for Food Security and Nutrition is a shared commitment to achieve sustained and inclusive agricultural growth and raise 50 million people out of poverty over the next 10 years by aligning the commitments of Africa’s leadership to drive effective country plans and policies for food security; the commitments of private sector partners to increase investments where the conditions are right; and the commitments of the G-8 to expand Africa’s potential for rapid and sustainable agricultural growth.” To implement the “New Alliance” and spark a Green Revolution in Africa, dozens of global food companies, including multinational giants Cargill, Dupont, Monsanto, Kraft, Unilever, Syngenta AG, have signed a “Private Sector Declaration of Support for African Agricultural Development”.


The vast majority of Ethiopians eke out a living as smallholder farmers. According to a 2010 USAID report, eight of every ten Ethiopians live in rural areas with average land holdings of 0.93 hectare. A 2011 report by the Oakland Institute   (OI) stated that Zenawi’s regime has “transferred at least 3,619,509 ha of land to investors, although the actual number may be higher.” These “lease” transfers (for 99 years) are handed out to companies from India, China, Saudi Arabia and 36 other countries for pennies per hectare. The OI further  reported that “displacement from farmland is widespread, and the vast majority of locals receive no compensation.” The displaced farmers who have lost their ancestral lands to “leases” are mostly indigenous minority peoples.

In 2011, Africa imported $50 billion worth of food from the U.S. and Europe. Food prices in Africa are 200-300 percent higher than global prices, which means higher profit margins for multinationals that produce and distribute food. With a steady growth in global population, the prospect of transforming Africa into vast commercialized farms is mouthwatering for global agribusinesses. The “New Alliance for Food Security” will accelerate at warp speed the “transfer” of hundreds of millions of hectares of arable African land to Cargill, Dupont, Monsanto, Kraft, Unilever, Syngenta AG and the dozens of other signatory multinationals. Working jointly with Africa’s corrupt dictators, these multinationals will “liberate” the land from Africans just like the 19th Century scramble for Africa; but will they liberate Africa from the scourge of hunger, famine, starvation and poverty? 

A Brief Lesson in African History
In 1894,  fourteen European and other countries including the U.S. (the “G-14” of the era) held a land grab conference in Berlin to "save" the Dark Continent. The publicity cover for the conference was the liberation of Africa from the slave trade and the need to undertake a civilizing mission. To that end, the Berlin Conference passed hollow resolutions. But the real agenda was to carve up Africa between the European powers peacefully and without the need for internecine imperialistic wars. The Scramble for Africa gave Britain a nice slice of Africa stretching from Cape-to-Cairo. France gobbled up much of western Africa. King Leopold II of Belgium took personal possession of the Congo. Portugal grabbed Mozambique and Angola. Italy snagged Somalia and laid claim to parts of Ethiopia.  

Ironically, the G-8’s “New Alliance” smacks of the old Scramble for Africa. The G-8 wants to liberate Africa from hunger, famine and starvation by facilitating the handover of millions of hectares of Africa's best land to global multinationals in Ethiopia, Mozambique, Uganda, Zambia, Malawi, Mali, Senegal, Tanzania, Sudan, Nigeria and  Ghana, among others. Is history repeating itself in Africa? Only the people of Madagascar have been able to successfully fight back and rescue their country from the clutches of the international land grabbers by dumping their president.

Ethiopian Hunger Games
When it comes to famine and starvation in Ethiopia, the standard response by the ruling regime and its international donors is to deny, evade and sugarcoat the whole thing in clever euphemisms (calling it “severe malnutrition, “food insecurity”, etc.; see my commentary, African Hunger Games at Camp David ), blame droughts and natural forces and endlessly supply food handouts. Bad governance, dictatorships  and corruption are rarely blamed for the predictable and recurrent famines and starvation in Ethiopia. 

Last week, the UN World Food Programme (WFP) in Ethiopia announced that “3.2 million people are food insecure in Ethiopia” and that it needs an additional US$183 million to provide emergency assistance. At the same time, Mitiku Kassa, Zenawi’s official responsible for agriculture, blamed the “food insecurity” on drought: “Irregularity in rainfall seasons resulting in problems of such a kind is not a new thing to us. We faced it last year and a year before that and we are managing it so far… The country has enough resources and mechanisms in place to deal with it this time, though.” The  mechanism in place is beggary proficiently practiced as a high  art form by Zenawi’s regime over the past two decades. A little over a month ago, the U.S. pledged to provide nearly $200 million in additional humanitarian aid to Ethiopia and the Horn of Africa. In 2011, the U.S. provided more than $1.1 billion in humanitarian aid. Ethiopia received more than US$3 billion in 2008, making that country the largest recipient of development aid in Africa.  

To say that Ethiopia will continue to face chronic “food insecurity” is like predicting the sun will rise tomorrow. “Food insecurity” (a/k/a famine) in Ethiopia is expected to reach biblical proportions by 2050.  In 2011, the U.S. Census Bureau made the catastrophic prediction that Ethiopia's population by 2050 will more than triple to 278 million. That did not stop Zenawi from declaring a crushing victory on famine in 2011: “We have devised a plan which will enable us to produce surplus and be able to feed ourselves by 2015 without the need for food aid.” 

Zenawi's plan to “produce surplus” is to stretch out cupped palms for handouts of crumbs left over from exports by Karuturi Global, Saudi Star, Cargill, Monsanto… and the rest. It is manifest that with the “New Alliance”, the U.S. and the other G8 countries have willfully blinded themselves to the moral hazard of endlessly aiding famine victims in Africa and unashamedly accepted the moral bankruptcy of endlessly aiding African dictators. It is axiomatic for them that providing endless handouts to impoverished and famished Africans is their divinely ordained “burden”, to borrow a word from the poet Rudyard Kipling who romanticized British colonialism. But they are now playing a far more sophisticated and deadly “hunger game” in Africa. 

They want to use multinational food conglomerates to “save” Africa from starvation by 1) subsidizing  these giant agribusinesses to dump their agricultural surpluses in famine-stricken African countries, and 2) by greasing the hands of Africa’s corrupt dictators so that these multinationals could “lease” hundreds of millions of acres of Africa’s most arable land to cultivate export crops that command high prices on the global commodities markets, without contributing much to the domestic African market to alleviate endemic hunger. The “New Alliance” is a brilliant strategy that will sustain the decades long vicious cycle of dependence and food aid addiction in Africa while displacing and severely undercutting the productive capacity of  the African smallholder farmers to deal with famine on their own. 

Keeping Them Honest!
It is noteworthy that few in the mainstream U.S. or international media paid any attention to the proceedings of the “New Alliance” food Summit. Even the international humanitarian organizations thought it was a publicity stunt. Oxfam was dismissive: “The New Alliance is neither new nor a true alliance. The rhetoric invokes small-scale producers, particularly women, but the plan must do more to bring them to the table.”  ActionAid was instructive: “While the New Alliance touts the role of the private sector, as President Obama said, this must include even the smallest African cooperatives. The real innovators in African agriculture are women smallholder farmers.  Any private sector partnership to improve food security must place them and African civil society at the center.” 


What needs special attention is the basic approach to “food security” that was discussed and not discussed at the summit. Rajiv Khan, the USAID Administrator and moderator of the food security Summit directing his remarks to Zenawi said:

… So many people have associated a mental image of hunger with Ethiopia and at the same time because of actions in the public sector maintaining strong public investment in agriculture you were able to protect millions of Ethiopians during the recent drought from needing food aid and food assistance.  Could you speak to, even as we are launching a new food alliance, to engage the private sector, could you speak to some of the comments you have shared with us privately how important it is we live to our commitments to invest in public investment, in public institutions?
Zenawi responded:
Ultimately, agricultural  transformation in Africa is going to be a partnership between the smallholder farmer and the private sector. But the most important actor here is the smallholder farmer that 70 percent of [interruption by Abebe Gellaw calling Zenawi “a dictator…” ] 70 percent of the population in Africa is smallholder farmers, so without transforming their livelihoods there is no future for agriculture in Africa. So at this stage the role of the private sector can only be to supplement the small scale farmer. There is the issue of rural roads, water supply systems, irrigation infrastructure. All of these require public investment; and yes, we need more of it. But we also need public investment. 

We in Africa are doing all we can, as I said, most of our countries are moving towards 10 percent of their budgets invested in agriculture; but we need partnerships. This morning the President [Obama] was talking about the L’Aquila Initiative  with $22 billion of money promised. We want the money promised delivered as the President was saying. We need that for public investment in infrastructure. We also need the developed countries to do something about trade because when you subsidize your farmers, our farmers who cannot be subsidized by our poor governments cannot compete. In the European Union, for example, every cow earns about $2 per day. Now that is more than the average African farmer gets and so if the subsidies were to be dealt with, we could have a better way of trading out of poverty.

Khan’s assertion that Zenawi by “maintaining strong public investment in agriculture [was] able to protect millions of Ethiopians during the recent drought from needing food aid and food assistance” is simply a statement made in reckless disregard for the truth, and arguably borders on a patent falsehood.  The fact of the matter is that USAID is clueless about its agricultural programs in Ethiopia,   according to the audit report of the Office of the Inspector General of USAID (March 2010, at p. 1):

The audit was unable to determine whether the results reported in USAID/Ethiopia’s Performance Plan and Report were valid because agricultural program staff could neither explain how the results were derived nor provide support for those results. Indeed, when the audit team attempted to validate the reported results by tracing from the summary amounts to the supporting detail, it was unable to do so at either the mission or its implementing partners… In the absence of a complete and current performance management plan, USAID/Ethiopia is lacking an important tool for monitoring and managing the implementation of its agricultural program.

In cases where USAID has been served with credible allegations of misuse of humanitarian and development aid for political purposes, it has turned a blind eye, deaf ears and muted lips. In 2009, the U.S. State Department, under which the USAID operates as the agency primarily responsible for administering civilian foreign aid, promised to investigate allegations that “$850 million in food and anti-poverty aid from the U.S. is being distributed on the basis of political favoritism by the current prime minister’s party.” No report has been issued. Khan and Zenawi can talk about “public investment” and the “smallholder farmer” until the cows come home, but the fact of the matter is that neither Ethiopia nor the rest of Africa can achieve food sufficiency by tethering predatory multinational corporations with corrupt African dictators in a new “alliance  for food security” and and strapping them around the necks of Africa’s smallholder farmers. 

A joint venture between jackals and hyenas will never benefit the gazelles.There are some simple questions that need to be asked about Ethiopia’s hunger games: Could Ethiopia reasonably expect to achieve food security when its citizens are prohibited by law from owning agricultural (for that matter all) land? Does it make sense to hand out the country’s most arable land to “foreign investors” to produce food for export and ensure food security in other countries when Ethiopians are dying from starvation?  Could Ethiopia reasonably expect to be saved from famine, starvation or “chronic food insecurity” by Karuturi, Saudi Star, Cargill, Dupont and the rest of the vampiric leeches? Does the smallholder Ethiopian farmer scratching out a living on 0.93 hectare stand a snowball’s chance in hell against Karuturi, Saudi Star, Cargill, Dupont…? Is the ultimate destiny of the smallholder African farmer to be a consumer of food produced by global agricultural multinationals instead of being a local producer and harvester of his/her own food?

Zenawi has adamantly opposed private ownership of land, which by all expert accounts is the single most important factor in ensuring food security in any nation. In 2000,  Zenawi said (and has repeatedly taken similar positions since): 
I have not heard of any truly convincing reason as to why we should privatize land ownership at this stage. I have not heard of any economic rationale for doing so. If there were to be an overwhelming economic rationale to do it and ultimately that would be the best way of securing the interests of our peasant farmer and therefore politically that would be our agenda… But at the same time we do not have any illusions as to what land ownership can do to the peasant farmer over the long-term. We do not believe that the long-term future and destiny of our peasant farmers is to be stuck in the mud, so to speak. We feel that ultimately there has to be industrialization, ultimately these people have to find to get employment outside agriculture.” 

In 2012, Zenawi pontificates about the need to “transform the livelihoods Africa’s smallholder farmers” through “public investment” and predicts “there is no future for agriculture in Africa.” He just does not get it!  There can be no smallholder farmer when there is no land to have and to hold. The smallholder Ethiopian farmer that Zenawi talks about is no better than the sharecropper or the tenant farmer. When the smallholder farmer is arbitrarily evicted from his land because he refuses to support Zenawi’s regime, denied fertilizer because he voted for the opposition or is put on the blacklist and watched day and night by hordes of  informants because he wants to remain politically independent, he is no longer a smallholder farmer. He becomes a landless, hopeless, helpless, restless, hapless, rootless, voiceless and powerless panhandler of international food aid. Without the small holder farmer, not only is there not a future for agriculture in Africa, there is no future for Africa itself! 

USAID, Ethiopia’s largest donor, in its 2010 report (perhaps unread by Khan), makes the simple point that effective agricultural development and long-term food security requires “100% ownership and buy-in by the Ethiopian people”. But instead of a “buy in”, Zenawi has pursued a relentless and ruthless policy of kick out, resulting in the displacement and confiscation of ancestral lands from countless small holder farmers. Now, Zenawi rubs his hands with glee to swipe his cut of the $22 billion promised in the L’Aquila Initiative. That is all he cares about!

Food  is Nothing Without Freedom!
Ethiopia’s four-decade old dependence on humanitarian food aid will continue and worsen. The Universal Declaration of Human Rights and the Convention on the Rights of the Child provide that it is the natural right of all people to have access to food. But under Zenawi, Ethiopians face a double whammy: A insatiable hunger for food and an unquenchable thirst for freedom, democracy and human rights. Ethiopians suffer from hunger and thirst because they are victims of a ruthless dictatorship!   

In 2007, speaking at the World Food Day, President Horst Köhler of Germany made the following extraordinarily insightful statement:
Hunger is not an inescapable destiny, but can be eliminated by wise policies. This requires first and foremost that the governments of the developing countries make food security for their populace a priority goal…. Democratic participation by the people is the best guarantee that governments will genuinely understand people's basic needs and will take these into account.  As the Indian Nobel Laureate Amartya Sen has so aptly said, in countries where there are no elections and there is no opposition, governments do not need to worry about political fallout from their failure to eradicate poverty…. Good governance and a functioning executive are absolutely  crucial for an economic policy that is geared to the needs of the people and will help to eradicate poverty… 

Who can seriously expect a smallholder to invest his savings in his farm and machinery if he fears he may be  thrown off the land at any time?... Excessive long-term help from outside can stifle the recipients' initiative and frequently even results in aid-dependency. … Hunger is above all the result of political mistakes - in the developing countries as in the industrialized nations.  To conquer hunger in our globalized world we need an honest, reliable and partnership-based development policy that spans the entire planet...

Perhaps President Obama could begin a new alliance for food security based on honesty and a genuine commitment to fundamental democratic principles that could help alter permanently Africa’s destiny as the beggar continent. The real solution to famine in Ethiopia lies in nourishing the emaciated Ethiopian body politic with clean elections, accountability, transparency, open political space and robust human rights protections. In 2009, he lamented, “There is no reason why Africa cannot be self-sufficient when it comes to food. I have family members who live in villages -- they themselves are not going hungry -- but live in villages where hunger is real.” President Obama should remind Zenawi and the rest of the African gang of dictators that though man does not live by bread alone, a hungry man in the village is an angry man!

Source:  http://www.ethiomedia.com/2012_report/3871.html

አማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ያዘዙትና በሙስና የተወነጀሉት ሽፈራው ሽጉጤ ካናዳ ይመጣሉ (አኢጋን)

Source: ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)
ተቃውሞ ፍራቻ ጉዞው በምስጢር አንዲያዝ መመሪያ ተላልፏል, በጉራፋርዳ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ትዕዛዝ የሰጡትና በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ በፓርቲያቸው የተበየነባቸው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የሚመሩት ቡድን ካናዳ ለስራ ጉብኝት እንደሚመጣ ተሰማ። 

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ሽፈራውን ተቃውሞ እንዳይገጥማቸው ጉብኝቱ በተለይ በውጪ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች እንዳይሰሙት በምስጢር እንዲያዝ መመሪያ ተሰጥቶ ነበር።

አቶ ሽፈራው ካላቸው የፖለቲካ ሥልጣን በተጨማሪ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት፣ የእርሻ ኮሌጁን ዲንና የተለያዩ ሹመኞችን አስከትለው በካናዳ በሚገኘው የሳስካችዋን ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት ለማድረግ ሰኔ 3ቀን 2004ዓም (ጁን 10 ቀን 2012) ካናዳ ይደርሳሉ፡፡ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከወራት በፊት በጉራፋርዳ ይኖሩ በነበሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ለተፈፀመው ግፍ መሪ ተዋናይ መሆናቸውን በስማቸው ተጽፎ የፈረሙበትን ደብዳቤ ዋቢ በማድረግ የጋራ ንቅናቄያችንን ጨምሮ በርካታ የአገርና የውጪ መገናኛዎች እንደመሰከሩባቸው ይታወሳል።

በተለይም የድርጊቱ ሰለባ የሆኑት እምባቸውን እያፈሰሱ የደረሰባቸውን በደል ሲገልፁ ያደመጡ ሁሉ በወቅቱ ድርጊቱን ከመቃወም ባለፈ “አማራው መደራጀት አለበት” እስከማለት አቋም እንዲይዙ የተገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። አቶ ሽፈራው “አንድም የተፈናቀለ ሰው የለም” በማለት ድርጊቱን ቢክዱም ከጉራ ፈርዳ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ሲቃ እየተናነቃቸው አገር አልባ መደረጋቸውን፣ በደላቸውን የሚሰማ አካል እንዳጡና ሃብትና ንብረታቸው ተዘርፎ፣ ቤታቸው ተቃጥሎ እንደ ለማኝ ፌስታል አንጠልጥለው እንዲባረሩ የተደረጉበትን ሁኔታ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) እና የሪፖርተር ጋዜጣ በስፋት ዘግበውታል፡፡ 

በተለይ መጋቢት 23ቀን 2004ዓም በታተመው የሪፖርተር ጋዜጣ ተፈናቃዮቹ ሁኔታውን በሚከተለው መልኩ ገልጸው ነበር፡- “…ነፍሰ ጡር እናት ሌሊት ወልዳ ሲነጋ የሰዓታት ዕድሜ ካለው ልጇ ጋር ከነፍራሿ ደጅ ተጥላለች፤ ነፍሰ ጡሮች ተሰደዋል፤ የስምንት ወር ዕድሜ ካላቸው ጨቅላ ሕፃናት ጀምሮ በርካታ ሕፃናት ከሚያጠቡ እናቶቻቸው ጋር አብረው ታስረዋል፤ የሚላስ የሚቀመስ አጥተው በረሃብ ተጠብሰዋል፤ በነፍስ ወከፍ እስከ 3ሺህ እግር ቡና ዛፍ፣ አቡካዶ፣ ማንጐ፣ ፓፓያና ሙዝ የተከለ እንዲሁም በርካታ የንብ ቀፎ የሰቀለው፣ በከብትና በዶሮ እርባታ ላይ የተሰማራው ገበሬ ያመረተውንና ያፈራውን ሀብትና ንብረት ጥሎ ጨርቁን በፌስታል አንጠልጥሎ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

 ‘ምንም ይዛችሁ ስላልመጣችሁ ምንም ይዛችሁ አትሄዱም’ እየተባሉ ንብረታቸውን ሜዳ በትነው እንዲሄዱ ተደርገዋል፤ በታጣቂዎችና በፖሊስ ሃይል ተደብድበዋል…” “የሰሚ ያለህ” በማለት አቶ መለስ ዘንድ በመቅረብ ይኖሩበት ወደነበረው ጉራፋርዳ ወረዳ እንዲመለሱ ወይም ደግሞ ወደ አማራ ክልል ተመልሰው ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቷቸው በግብርና ሥራ የሚሰማሩበት ሁኔታ ይመቻችላቸው ዘንድ አቤቱታ ለማቅረብ ወደ አዲስ አበባ ከመጡት 600 ገደማ ከሚደርሱት ተፈናቃዮች መካከል አብዛኛዎቹ በፖሊሶች በኃይል እየተገፈተሩ በአራት የሕዝብ ማመላለሻና በአንድ ታክሲ ተጭነው ወደ ደብረ ብርሃን ተወስደዋል፡፡

ለዚህ ሁሉ ግፍና በደል ተጠያቂ የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሌላም በኩል ከየካቲት 5 አስከ የካቲት 11 ቀን 2004 በክልሉ ፓርቲ አማካይነት በተካሄደ የከፍተኛ አመራሮች ግምገማ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል እንዲጠየቁ የተበየነባቸው የህወሓት/ኢህአዴግ ሹመኛ ናቸው። የጋራ ንቅናቄያችን በክልሉ ያሉትን ምንጮች በመጥቀስ በወቅቱ እንደዘገበው በአቶ መለስና በተከታዮቻቸው ቋንቋ “ኪራይ ሰብሳቢና ሙሰኛ” የተባሉት አቶ ሽፈራው ለቀረበባቸው ክስ ሲመልሱ “እኔ ብቻዬን አይደለሁም። ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋር በጋራ ገንዘብ ወስደናል። የምንጠየቅ ከሆነ ሁለታችንም ህግ ፊት መቅረብ አለብን። ብሩን መመለስ ካለብንም ሁለታችንም መመለስ አለብን” ማለታቸው ይታወሳል።

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከግምገማው በኋላ አስር ይገጥማቸዋል፤ በዋናው የኢህአዴግ ግምገማ ላይ ይገመገማሉ፤ የሚል እምነት የነበራቸው የክልሉ ሹመኞች የግምገማው ውጤት በመገልበጡ ማዘናቸውን ተናግረው ነበር። ከማዘናቸውም በላይ ወደፊት እንዴት አብሮ መስራት እንደሚቻል ያሳሰባቸው ሹመኞች “አቶ ሽፈራው በከፍተኛ ሁኔታ የቡና ንግድ በተሰማራ ድርጅት ውስጥ የላቀ የአክሲዮን ባለ ድርሻ መሆናቸው እየታወቀ ዝም የተባሉት ወ/ሮ አዜብን ተንተርሰው ነው፤ ተነካክተዋል። ይህ ደግሞ አገራዊ በሽታ ነው” ሲሉ አቶ መለስ ታጋይዋን ሚስታቸውን ለመሸፈን ሲሉ የግምገማውን ውጤት መገልበጣቸው ቅሬታ መፍጠሩን አመልክተው ነበር።

በካናዳ ሳስካችዋን ዩኒቨርሲቲ ለስራ ጉብኝት የሚመጡት አቶ ሽፈራው ተግባራቸውን ስለሚያውቁት ጉብኝታቸውን ከተቃውሞ ለመከላከል ሲሉ ምስጢራዊ እንዳደረጉት የገለፁት የጋራ ንቅናቄያችን የደቡብ ምንጮች ምናልባትም የጉብኝታቸው ጉዳይ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አቋማቸውን ሊቀይሩ እንደሚችሉም ገምተዋል። አክለውም ሰሞኑን በታላቅ የዓለማችን መድረክ ላይ አቶ መለስ የገጠማቸው አስደንጋጭና ያልተደበቀ መብረቃዊ ተቃውሞ ከፍተኛ የመገናኛ ሽፋን በማግኘቱ የተነሳ አቶ ሽፈራውም ከተመሳሳይ ውግዘት ለመዳን ጉብኝታቸውን በዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች ብቻ እንዲከናወን ሊደርጉት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ በከተማዋ ለረጅም ዓመታት የኖሩ ሲሆን ትምህርታቸውን የተከታተሉበትና በተለያየ የተማሪ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ የነበሩበት የሳስካችዋን ዩኒቨርሲቲ፣ በቅርቡ 100ኛ ክብረ በዓሉን ሲያከብር “ተጽዕኖ ፈጣሪ” በማለት ከመረጣቸው 100 የቀድሞው ተማሪዎቹ መካከል አቶ ኦባንግ እንደሚገኙበት ከዩኒቨርሲቲው መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ሽፈራው ህጻናት ሳይቀሩ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ቀነ ገደብ ወስነው ደብዳቤ ትምህርት ገበታቸው ድረስ የላኩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ታዛዥ ቢሆኑም የሚያስተዳድሩት ሰፊ ኅብረተሰብ ድጋፉን እንዲያነሳ ቅስቀሳ እየተደረገባቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል እሳቸውን የሚተካው ሰው ህዝቡ እንዲቀበለው የውስጥ ለውስጥ ስራ እየተሰራ መሆኑን በክልሉ የጋራ ንቅናቄያችን ምንጮች አመልክተዋል።

Sunday, June 3, 2012

Wikileaks - Meles Zenawi gets money from Piracy

The world most Dictatorial Ethiopian regime leader Meles Zenawi enjoying money from Piracy.  As it has been heard from the above video, He get it so that he protects the pirates from harms. 

የሰሜን ጎንደር የመኢኣድ ምክር ቤት የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ታሰሩ

ኢሳት ዜና:-
በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታድሎ ተፈራ የታሰሩት ትናንት ሲሆን፣ ከ10 ያላነሱ ፖሊሶች ወደ ቤታቸው በመሄድ እና ከፍተኛ ፍተሻ በማካሄድ አፍነው ወስደውታል። የበለሳ ተወላጅ የሆነው አቶ ታደሎ ተፈራ  ጎንደር ከተማ ውስጥ ከአክስቱ ጋር ይኖር ነበር።

 አክስቱ  ወ/ሮ ዘርጊባቸው ሀይሉ ለኢሳት እንደገለጡት ግለሰቡን በርካታ ፖሊሶች ስራ ይሰራበት ከነበረው ደልጊ ከተማ ይዘው በመምጣት ቤቱን ፈትሸዋል:: በደባርቅ አቶ ስለሺ ጥጋቤነህ ፣ በጭልጋ ደግሞ አቶ መለሰ አስሬ  ከትናንት በስቲያ ታፍነው መወሰዳቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ግለሰቦቹ ታፍነው ስለተወሰዱበት ምክንያት እና የት እንዳሉ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ ዛሬ ከአቶ መለሰ ቤተሰቦች ባገኘነው መረጃ ግለሰቡ ቤታቸው ሲፈተሽ ምንም ነገር አልተገኘባቸውም። የጭልጋ ነዋሪዎች ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።  መንግስት በግለሰቦቹ መታሰር ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የለም።

አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ግለሰቦቹ የታሰሩት ከዋልድባ ገዳም እና ከራስ ዳሸን  ጋር በተያያዘ በአካባቢው ከሚታየው ውጥረት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። የደባርቅ ወረዳ ወጣቶች ከዋልድባ፣ ከራስ ደጀን እንዲሁም ከመልካም አስተዳዳርና ፍትህ እጦት ጋር በተያያዘ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጋር በተደጋጋሚ እንደሚላተሙ ይታወቃል።

 የደባርቅ መምህራን የደሞዝ ጭማሪ ይደረግልን በማለት ተቃውሞ ካሰሙ መምህራን መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው። በጭልጋ ወረዳም እንዲሁም መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በአፋር ክልል ያለው ችግር ተባብሶ መቀጠሉ ታወቀ

ኢሳት ዜና:-
የአፋር ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት በክልሉ ያለው ችግር መባባስ ህዝቡ ሰላማዊ ኑሮውን እንዳይገፋ አድርጎታል።  በዞን አንድ እና ዞን 3 በተባሉት አካባቢዎች መንግስት ነዋሪዎችን በጉልበት እያፈናቀለ መቀጠሉን  በዞን ሁለት ደግሞ የማእድን ዘረፋው የችግሩ ምንጭ መሆኑን  የአፋር ህዝብ ጋድሌ ሰራዊት ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ ለኢሳት ገልጠዋል::

ኮሎኔል ሙሀመድ እንዳሉት ለስኳር ፋብሪካ በሚል አካባቢው እንዲራቆት እየተደረገ በመሆኑ ህዝቡ ተቃውሞውን እያሰማ ነው:: የአፋር ክልል መንግስት ለህዝቡ ምንም ሊፈይድ እንዳልቻለ ኮሎኔሉ ይናገራሉ::

በዛሬው እለት ተፈጠረ ስለተባለው ግጭት ለማረጋጋጥ ወደ አካባቢው በተደጋጋሚ ብንደውልም የስልክ መስመር ለማግኘት አልተቻለም። መንግስትም በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።

የመሬት ቅርምት ወደ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ጋዜጣ ዘገበ

ኢሳት ዜና:-
በስዊዘርላንድ የሚታተም ታገስ አንዛይገር የተባለ ጋዜጣ  ፣ በመሬት እና ባካባቢው ከሚኖሩ ዜጎች ፍላጎት እና ስምምነት ውጭ የሚደረግ ማንኛውም ኢንቨስትመንት  በባለሃብቶች እና ባካባቢው በሚኖሩ ዜጎች መካከል በሚፈጠር  አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ግጭት ሊያመራ እና   በሃገሪቷ ውስጥም አለመረጋጋት ሊፈጥር እንደሚችል አስጠንቅቋል።

ጋዜጣው የአቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የእርሻ መሬት 10% ወይም 3.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለውጭ ባለሀብቶች እንደተሰጠ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ እና በሌሎች ደሀ አገሮች  የሚኖሩ አነስተኛ ገበሬዎች    ህይወታቸውን መሰረት ያደረጉበት መሬታቸው ለውጭ ባለሀብቶች በመቸብቸቡ እና ከቀዬአቸውም እየተፈናቀሉ መሆናቸው የወደፊት መጻኢ እድላቸው አደጋ የተጋረጠበት ነው ሲል አስፍሯል።

ታገስአንዛይገር በመቀጠል በአለም ዙሪያ በተለይ በታዳጊ ሀገሮችና ባላደጉ ሀገሮች ላይ እየተካሄደ ያለውን መሬት ነጠቃ በግንባር ቀደምትነት የምትመራው  ቻይና ናት ብሎአል።

ይህ መሬት ነጠቃም በዋናነት ያተኮረው ባላደጉ ሀገሮች ላይ እና ጠንካራ የመሰረተ ልማት አገልግሎት በሌለባቸው ረሀብና ድህነት በከፍተኛ ደረጃ በሚያጠቃቸው እንዲሁም መንግስት ለዜጎቹ መብት በማይጨነቅባቸው ሀገሮች ላይ እንደሆነ የጠቆመው ጋዜጣው፣ ባለሀብቶቹም በነዚህ ሀገሮች ላይ በከፍተኛ ደረጃ በማተኮር ገንዘባቸውን በማፍሰስ ላይ መሆናቸውን ከላንድ ማትሪክስ ጥናት ለመረዳት ተችሏል በማለት ገልጿል።

ጋዜጣው በአሁኑ ወቅት እየተስፋፋ ያለው የመሬት ቅርምት ካልተገታ በታዳጊ እና በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት ውስጥ በሚገኙ አነስተኛ ገበሬዎች የወደፊት ህይወት ላይ ከፍተኛ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አሳስቦአል።

ኢትዮጵያዊቷ በኩዌት ጎዳናዎች ራቁቷን ደም በደም ሆና ታየች

ኢሳት ዜና:-
ደሟን እያዘራች ራቁቷን በኩዌት ጎዳናዎች ላይ ስትሮጥ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት በፖሊስ ተይዛ -በሳይካትሪስት ምርመራና ህክምና እንዲደረግላት ወደ ሆስፒታል መግባቷን አረብ ታይምስ ዘገበ።

አረብ ታይምስ ፦ “አል ራይ” የተባለውን የአገሪቱን ሳምንታዊ ጋዜጣ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በጎዳና ላይ ሲጓዙ የነበሩ እግረኞች  አፍሪካዊ መልክ ያላት ሴት ራቁቷን ሆና ደም እየፈሰሳት በጎዳና ላይ ስትሮጥ ማየታቸውን ለኩዌት የአገር ውስጥ ሚኒስቴር የኦፕሬሽን ዲፓርትመንት ሪፖርት ያደርጋሉ።

መረጃው የደረሳቸው የኩዌት ደህንነቶችም ወዲያው በመሰማራት  በጎዳና ላይ እርቃኗን ሆና ደሟን የምታዘራውን ሴት ይይዟታል። በተደረገው ምርመራ ሴቲቱ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ስትሠራ የነበረች ኢትዮጵያዊት  ሆና መገኘቷን ይፋ ያደረጉት የደህንነት ምንጮች፤ ደም  ሲፈሳት የነበረውም የገዛ እጇን በስለት በማረዷ እንደሆነ   አመልክተዋል።

ለዚህ  የተዳረገችውም ወደ ኩዌት የወሰዳት ስፖንሰሯ ወደ አገሯ ይመልሳት ዘንድ ያቀረበችለትን ጥያቄ ሳይቀበላት በመቅረቱ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህም ሳቢያ ኢትዮጵያዊቷ እስከ መደባደብ ሳትደርስ እንዳልቀረች የጠቀሰው የኩዌት ፖሊስ፤ የተሟላ መግለጫ ለመስጠት የዶክተሮች ሪፖርት እየተጠበቀ መሆኑን  አስታውቋል።

በተለየ መልኩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኩዌት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  በአሠሪዎቻቸውና በስፖንሰሮቻቸው የተለያዩ በደሎች እየተፈፀሙባቸው እንደሚገኙ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።