Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, April 17, 2012

ኢህአዴግን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ እየተዘጋጀ መሆኑን መኢአድ አስታወቀ

 ፍኖተ ነፃነት ዜና ቁ.38

የኢህአዴግ ባለሥልጣናት በአስቸኳይ ካድርጊታቸው ካልታቀቡ በዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍ/ ቤት ለመክሰስ እየተዘጋጀ መሆኑን መኢአድ አስታወቀ፡ ፡ የመኢአድ አመራሮች ይህንን ያስታወቁት ባለፈው ሐሙስ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ ፓርቲውን ወክለው መግለጫ የሰጡት የፓርቲው ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ወንድምአገኝ ደነቀው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ ወ/ሪት መሶበወርቅ ቅጣውና የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ም/ኃላፊ አቶ ጌታቸው አበበ ናቸው፡፡ አመራሮቹ እንዳሉት “እየተፈፀመ ያለው ጥቃት በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ፣ ከሀብት ንብረት ማፈናቀልና ከመኖሪያ ቀዬ ማሳደድ እንዲቆም እየጠየቅን ይህ ሊሆን ካልቻለ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት በዓለም አቀፍ ፍ/ቤት በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ ከዓለም አቀፍ የሕግ ባለሞያዎች ጋር እየመከሩ መሆናቸውን” አስታወቋል፡፡

መኢአድ መጋቢት 4 ቀን 2004 ዓ.ም በወጣዉ መግለጫ እንደገለፀዉ “የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የህዝብን ጉዳይ ወደ ኃላ በመተው እውነታውን ደብቆ ኢህአዴግ በሚታወቅበት በተራ ዶክመንተሪ ፊልም ፕሮፓጋንዳ ዝግጅት ላይ መጠመዳቸው በእጅጉ አሳዝኖናል” በሚል ርዕስ ባለ አራት ገጽ መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግለጫው በመግቢያው ላይ እንደተገለፀው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ )በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን በጉራፋርዳ ወረዳ ውስጥ በነዋሪዎች ላይ በመንግስት አካላት እየተፈጸመ ያለውን በአንድ ዘር ላይ ያነጣጠረ ከሀብት ንብረት ማፈናቀልና ከመኖሪያ ቀዬ ማሰደድ እንዲቆም ለሚመለከተው ሁሉ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ የፌደራል መንግስትን ጨምሮ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በሙሉ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ በተለያዩ መግለጫዎችና ደብዳቤዎች በተደጋጋሚም ጠይቋል፡፡ 

በክልሉ አሁንም ሰዎች ይሰደዳሉ ፤ይፈናቀላሉ ፤ ከመኖሪያ ቀያቸውና ከእርሻ ቦታቸው እንዲነሱ ይገደዳሉ፤ ይደበደባሉ፤ ይታሰራሉ በጉማሬ ጎማ ይገረፋሉ ፤ በሀሰት ክስ ይከሰሳሉ፤ በቅርቡም እየሩሳሌም በሚባለው አካባቢ በወረዳው የፖሊስ አዛዥ በሳጅን ምስክር ድብደባ በጭብቅላቱ ላይ በደረሰ ከባድ ጉዳት ምክንያት እራሱን በመሳቱ ከመኪና ላይ ወድቆ ህይወቱ ያለፈው የአቶ አባብለው ማሞ አሟሟትም የዚሁ ማስረጃ ነው፡፡ ሌሎች ሁለት ወጣቶችም በጦር ተወግተው በታፋቸውና በሽንጣቸው ላይ በደረሰ ጉዳት ለከፍተኛ ስቃይ ተደርገዋል፡፡ አሁንም የህዝቡ ንብረት በካድሬዎች ይዘረፋል፤ ስድስት ወፍጮ ቤቶች ተነቃቅለው ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል እቃዎቹም ተዘርፈዋል፡፡ 23 ቤቶች ተቃጥለዋል ይላል፡፡ መግለጫው በገጽ ሁለት ላይ ሲዘረዝር ከአካባቢው ላይ ህዝቡ በመሰደዱ ምክንያት ማሪያም ሰፈር የሚገኘውን የማሪያም ቤተክርስቲያን ጽላት(ታቦት) ወደ ወረዳው ቤተክህነት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተወስዷል፡፡ ህጻናትና ሴቶች ለከፋ እንግልትና ስቃይ ፤እንዲሁም ለህክምና እጦትና ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል፡፡

ሆኖም ግን መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ለመፍትሄ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ለርካሽ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል ችግሩ እንዳልተፈጸመ ለማድረግና ለማስተባበል እንዲሁም ሁኔታውን ፈጽሞ ለማዳፈን ከፍተኛ ዘመቻ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡ መጋቢት 02/2004 ዓ.ም. የደቡብ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በጉራፋርዳ ወረዳ ውስጥ ‹‹ የተፈናቀለ ሰው የለም ፤ ሰዎችን ለመመለስም የተያዘ ዕቅድ የለም ›› በማለት በሚዲያ የተናገሩት ርካሽ ፕሮፓጋንዳ አሳዛኝና አሳፋሪ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ፀሀይ የሞቀውን እውነታ ለመሸፈን ሲሉ ምንም አይነት ከቀዬው የተፈናቀለም ሆነ ከክልሉ እንዲወጣ የተደረገ ሰው እንደሌለ በማስመሰል ፤በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ኢ-ሰብአዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ እንዲሁም የዜጎችን ክብር ያዋረደ ድርጊት መካዳቸው እውነትን የመግደል አባዜ የተጠናወታቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ዛሬም ከሃያ ዓመት በኃላ ለለውጥ፤ ለግልጸኝነትና ለተጠያቂነት ያልተዘጋጁ መሆናቸውን አመላካች ነው፡፡

የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሚያስተዳድሩት ክልል ውስጥ በዜጎች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የበላይ መመሪያ ሰጭ እንደ መሆናቸው ከማንም በላይ ጉዳዩ በቀጥታ እንደሚመለከታቸው የማይታበል ሀቅ ነው፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ደብረ ብርሀንና ሌሎች አካባቢዎች የተሰደደው ህዝብ ቁጥር ከሁለት ሺህ (2000) በላይ በሆነበትና ፤አሁንም ድረስ ከክልሉ እየታሰሩና እየተደበደቡ እንዲወጡ እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ምንም እንዳልተፈጸመ ለመሸፋፈን መሞከር እራስን ማታለል ካልሆነ በቀር ከኢትዮጵያ ህዝብ የተሰወረ አይደለም፡፡ እነዚህ ከሰሜኑ የአማራ ክልል አካባቢ በተለያየ ጊዜ እና የስራ ሁኔታ ምክንያት ወደ ደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን እየወረዱ ረጅም ዓመት ያስቆጠሩ፤ በህጋዊ መንገድ ከመንግስት መሬት ተረክበው ሀብት ንብረት ያፈሩ፤ ቤተሰብ የመሰረቱ ፤ግብር ከፋይ ዜጎች ሆነው ሳለ የክልሉ ባለስልጣናት ቁጥራቸውን ወደ ሰላሳ አሳንሶ ‹‹ደን ሲያወድሙና ሲያቃጥሉ የነበሩ ህገወጦች ናቸው ›› ማለቱ በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡ እነዚህ ዜጎች ግን መንግስት እንደሚለው ሳይሆን ህጋዊ ሆነው ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድና ግብር የከፈሉበት ማስረጃ በእጃቸው ይገኛል፡፡

 ከዛም ባለፈ በ1996 ዓ.ም. ወረዳቸውን በልማት ከዞኑ በአንደኝነት ያሸለሙ አምራች ዜጎች ናቸው፡፡ መንገድ የሰሩ፤ ትምህርት ቤት እና ቀበሌዎችን የገነቡ፤ ቤተክርስቲያናትን ያነጹ እና ጥሩ ማህበራዊ መስተጋብርን የፈጠሩ ዜጎች ናቸው፡፡›› በማለት አቋሙን ገልፃóል፡፡ በማያያዝም መግለጫው ሲብራራ በቅርቡ ጉዳዩን ለማጣራት ከአዲስ አበባ ወደ ቤንቺ ማጂ ዞን ጉራፋርዳ ወረዳ የተንቀሳቀሰ አጣሪ ቡድን መኖሩ ይታወቃል፡፡ይህ አጣሪ ቡድን የኢህአዴግ ብአዴን አመራሮች ሲሆኑ ከደህዴን ደግሞ የደቡብ ክልል ቤንቺ ማጂ ዞን እና የወረዳ ኃላፊዎች እንደተካተቱ ለማወቅ ተችሏል፡ ፡ ህዝቡን ሲያስሩና ሲደበድቡ ፤ ሀብት ንብረቱን አዲሶቹ “ቀሺ ገብሩዎች” በሻማ ምሽት ታወሱ ኢህአዴግን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ እየተዘጋጀ መሆኑን መኢአድ አስታወቀ ሲያዘርፉና ሲያፈናቅሉ የነበሩና አሁንም ድረስ ቀንደኞቹ የችግሩ ፈጣሪ አድራጊዎች የዞን፤ የወረዳና የቀበሌ ባለስልጣናት፤ እንዲሁም ሰው ደብድበው በመግደላቸው ምክንያት በግድያ ወንጀል መጠየቅ የሚገባቸው ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ከሄደው ቡድን ጋር የችግሩ አጣሪ ቡድብ አባላት ሆነዉ እንዲሰሩ መደረጉ የመንግስትን ለመፍትሄ ዝግጁ አለመሆን አመላካች ነው፡፡ ሲል ከሷል፡፡

መግለጫው ሰለአጣሪ ቡድኑም የማጣራት ሂደት ሲዘረዝር፡- የጥቃት ሰለባ የሆነውን ህዝብ ማነጋገር ሲገባው እስከ አሁን ድረስ አላናገረም ፤ሊያናግሯቸው ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ በተቃራኒው የዞንና የወረዳ ኃላፊዎች እንደሚመቻቸው አድርገው ያዘጋጇቸውን ግለሰቦች እንደ አርሶ አደር አድርጎ በማቅረብ በአካባቢው ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልተፈጠረና ሰላም እንደሆነ፤ ማንም ላይ በፖሊስና በታጣቂዎች ድብደባም ሆነ ሌላ ጥቃት እንዳልተፈጸመ በመግለጽ ፤ ከአካባቢውም አንድም የተፈናቀለ አርሶ አደር እንደሌለ ፤እንዲሁም ደግሞ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚል ኃይልም እንዳልመጣባቸው እንዲናገሩ ተደርጓል፡፡ አጣሪዎቹም ህዝቡን የማይወክሉትን፤ ነገር ግን ህዝቡን ወክለው ምስክርነት እንዲሰጡ የተደረጉትን እነዚህን የኢህአዴግ ታማኞች በቪዲዮ ሲቀርጹ ውለዋል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች የወረዳው የገጠር ልማት ሰራተኞችና የቀበሌ ካቢኔ አባላት መሆናቸው በግልጽ እየታወቀ የተሳሳተ መረጃ እዲሰጡ መደረጉ ኢህአዴግ እየሰራ ላለው ፀሀይ የሞቀውን ጉዳይ ለመካድና ለማፈንና እንዲሁም ለውሸት ዶክመንተሪ ፊልም ፕሮፓጋንዳው ግብአት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

 መንግስት እውነት ችግሩን ለመፍታት ቢፈልግ ኖሮ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው ህዝብ በሜዳ ተበትኖ ባለበትና አዲስ አበባን ጨምሮ ፤ከወለጋ እስከ ደብረ ብርሀን በፈሰሰበት ሁኔታ ተጎጂውን ህዝብ ባገለለ መልኩ ማጣራቱን ለማስኬድ ባልፈለገ ነበር፡፡ ቤንቺ ማጂ ድረስ መሄድ ሳያስፈልገዉ አዋሬ ያሉትን ተፈናቃዮች ማየቱ ብቻ በቂ ነዉ፡፡ የኢህአዴግን ባህሪ ለሚያውቅ ሁሉ ጉዳዩ ወዴት እያመራ እንደሆነ መገመት አይከብደውም፡፡ በክልሉ ያለው የችግሩ ገፈት ቀማሽ ህዝብ ግን ከተደበቀበት እየወጣ ‹‹ እነዚህ ሰዎች የኢህአዴግ ሰዎች ናቸው ፤ የሚሰጡት ማስረጃም ህዝቡን የሚወክል አይደለም እኛ ችግር ደርሶብናል አዳምጡን ለማጣራት ከፈለጋችሁ ተጎጂው ህዝብ አካባቢ ውረዱና አናግሩን፣ የመንግስት ካድሬዎች ያቃጠሉትንም ቤት፤ ያወደሙትን ንብረት ተመልከቱ፤ የህዝቡንም ማሳ እዩ ፤ በሜዳ የቀረውንም ከብት ተመልከቱ ፤ሰው አልባ የሆኑ መኖሪያ ቤቶችንም እዩ ›› ቢልም የሚሰማው አጥቷል፡፡ እንዳውም አጣሪው ቡድን ይገኝበታል ወደተባለበት ቦታ የተንቀሳቀሰውን ህዝብ የዩና የቁጥሩ መጨመር ያሰጋቸው የአካባቢው ካድሬዎች ህዝቡ በታጣቂና በፖሊስ ኃይል እንዲበተን አድርገዋል፡፡

አጣሪ ቡድኑ የተጎዳውንና የተሰደደውን ህዝብ የመኖሪያ አካባቢ በመተውና ሌላ አካባቢ ላይ በመሄድ በመኖሪያ ቤቱ የሚገኝንና ያልተፈናቀለን ህዝብ ሲቀርጽ ውሏል፡፡ ምንም አይነት ችግር እንዳልተፈጠረም በሚዲያ አስነግረዋል፡፡ ይህም ለተራ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ሲባል የህዝብን ጩኸት የማፈን ድርጊትም ፈጽመዋል፡፡ አጣሪ ቡድኑ ደን ሲቃጠልና፤ የደረቀ ዛፍ እየፈለገ ሲቀርጽ ሰንብቷል፡፡ይህም የአካባቢው ባለስልጣናት ህዝቡን ከሚያስፈራሩበትና በብዙዎች ላይ ክስም ከመሰረቱበት አንዱ ተግባር ነው ፡፡ ‹‹ ዛፍ አድርቃችኃል፤ደን አቃጥላችኃል ›› ብለን እንከሳችኃለን የሚለው ዛቻቸው እውነት ሆኖ በርካታ ዜጎች በዚህ ክስ ተከሰው ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ኢህአዴግም ለሌላ ዙር የውሸት ዶክመንታሪ ፊልም (ድራማ) እየተዘጋጀበት ይገኛል፡፡ ብሎአል፡፡መግለጫው በመጨረሻው ሲያጠቃልል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ‹‹ይህን አይነቱን የአጣሪ ቡድኑን ድርጊት በህዝብ ላይ የተፈጸመ አስከፊ ግፍና በደልን ለመሸፋፈን የሚደረግ ርካሽ ተግባር በመሆኑ አጥብቆ ያወግዛል ፡፡ የሚመለከተውና ያገባኛል የሚል አካል ሁሉ ድርጊቱን እንዲያወግዝም ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

መንግስት ለችግሩ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ሁኔታውን ለመሸፋፈንና ለማዳፈን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አቁሞ በአስቸኳይ ለነዚህ ዜጎች መፍትሄ እንዲስጥ አሁንም በድጋሜ ጥሪ እናደርጋለን፡፡ ሰው የገደሉ፤ በአካል ላይ ጥቃት የፈጸሙ፤ በተለያየ ህገወጥ ተግባር ላይ በመሰማራት በህዝቡ ላይ ወንጀል የፈጸሙ የመንግስት ባለስላጣናት በህግ እንዲጠየቁ መኢአድ ይጠይቃል፡፡›› ሲል ይደመድማል፡፡በመጨረሻም አመራሮቹ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡“የደቡብ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሰሞኑን የተፈናቀሉ የሉም፡፡ ወደ ክልላቸው መሄድ የፈለጉ 800 ሰዎች በክብር ተሸኝተዋል ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment