Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, March 30, 2013

ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?

ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው።

ኢህአዴግ አድርባይ ሚዲያዎች አሉት። አድርባይ ባለሃብቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ የኔቢጤዎች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይና የማደናገሪያ ፕሮጀክቶች አሉት። ኢህአዴግ አድርባይ ድርጅቶች እንጂ ነጻ ድርጅቶች የሉትም። ኢህአዴግ አድርባይ ባለስልጣናት እንጂ ነጻ አመራሮች የሉትም። ሁሉም አድርባዮች ተጠሪነታቸው ለህወሃት ስለሆነ ተጠያቂውም ራሱ የኢህአዴግ ሾፌር ህወሃት እንጂ ሌሎች ሊሆኑ አይገባም። “ፈጣሪያቸው” የሚገመግማቸው፣ እነሱም አምነው የሚገመገሙት ታማኝ አድርባይ ስለሆኑ ብቻ ነው።

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም


ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል፡፡ ምንጭ፤ www.goolgule.com
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።

Friday, March 29, 2013

........እኔ የምለው ከክልል ወደ ክልል እየተንቀሳቀሱ ለመስራት እና ለመኖር ፓስ ፖርት እና ቪዛ ማስመታት ያስፈልገናል እንዴ? By ብሩክ ሲሳይ

እንደሚታወቀው ኢህአዴግ የሚባለው ገዢ ቡድን መንበረ ስልጣኑ ላይ ከወጣ ጀምሮ ብዙ አሳዛኝ ነገሮችን በህዝባችን እና በሀገራችን ላይ ሲፈፅም ቆይቷል አሁንም እየፈፀመ ይገኛል። ከነዚህ አሳዛኝ ነገሮች አንዱ እንደ አንድ ሀገር በአንድነት ለዘመናት ብዙ ርቀት የተጓዘን ህዝብ ወደ ኋላ በመመለስ የዘር እና ጎሳ ልዩነትን በሚያጎላ አካሄድ፤ ቋንቋን እና ዘርን መሰረት ያደረገ የከሸፈ የፌድራሊዝም አወቃቀር ስርዓት በመከተል እንደ ሀገር ብሄራዊ ስሜት እንዳይኖረን የክልል መንግስት የሚባል መዋቅር መፈጠሩ ነው። 

ሲመስለኝ ፌድራሊዝም በራሱ አስፈላጊ የሚሆነው እንደ ሀገር ተበታትነው በተለያየ አገዛዝ የነበሩ አካባቢወች ልዩነታቸውን በማቻቻል ወደ አንድነት መንግስት ለመምጣት ሲያስቡ እንደ መሸጋገሪያ ራስገዝ የሆነ የፌድራል ስርዓት ይመሰርታሉ፤ እነዚህን ራስ ገዝ ክልሎችም በበላይነት የሚመራና የሚቆጣጠር ከሁሉም አካባቢ የሚወከሉ አካላትን ያካተተ ማዕከላዊ መንግስት ይመሰረታል። ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ትናንሽ የተለያዩ መንግስታት የነበሩት የአሜሪካ ግዛቶች የፈጠሯት የዛሬዋ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ነች። 

የዘገየው አብዮት (ተመስገን ደሳለኝ)

‹‹አረብ ስፕሪንግ››ን ተከትሎ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፖለቲካ ተንታኞች በዘርፈ ብዙ ቅሬታ በተሞላችው ኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነገር መከሰቱ አይቀሬ እንደሆነ ደግመው ደጋግመው መተንተናቸው ይታወሳል፡፡ ለድምዳሜያቸው ገፊ ምክንያት አድርገው ከወሰዷቸው ችግሮች ውስጥ ስርዓቱ ለሁለት አስርታት በስልጣን ላይ መቆየቱ፣ አስከፊ ድህነት መስፈኑ፣ የስራ አጥ ቁጥር ማሻቀቡ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ክብር አልባ መሆናቸው፣ የፍትህ እጦት… ተጠቃሽ ናቸው፡፡ 

ቁጥራቸው የበዛ ምሁራኖች እነዚህ ችግሮች በጊዜ መፍትሄ ካላገኙ አብዮት ወደ ሚያቀጣጥል ‹‹ካምሱር››ነት ለመቀየራቸው የተለያዩ ሀገራትን ታሪክ ጭምር ጠቅሰው በርካታ ፅሁፎችን አስነብበዋል፡፡ የሆነ ሆኖ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ህዝቦች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን መነቃቃት ለማደብዘዝ ስርዓቱ ራሱን ለተጋነነ ወጪ መዳረጉ ይነገራል፡፡ በተለይም የደህንነት ተቋሙን፣ መከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊትን ለማጠናከር የሀገር ሃብት ባክኗል፡፡

Monday, March 25, 2013

የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው

ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡