Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, April 19, 2012

አማራ ማነው?

ባጠቃላይ ይህን አስመልክቶ ጥናት ማድረግ ከፈለጋችሁ መርድ ወ/አረጋይ፣ አስመሮም ለገሰ፣ አንቷን ዳባዲ ኤ.ትሪዩልዚ ያቀረቧቸውን የታሪክ ትንተናዎች ከነጋሶ ጊዳዶ፣ መሀመድ ሀሰንና ሌሎቹም ብሔረተኞች ከፃፏቸው ጋር ማወዳደርና የግላችሁን ማጠቃለያ መስጠት ትችላላችሁ። (በተጨማሪ በዚህ ፅሁፍ ተጠቃሽ የሆኑትን ምንጮችና ሌሎችንም ታሪካዊ ማስረጃዎች ማገናዘቡ ጠቃሚ ነው).
Oromo migration in the 6th century 


አማራን በተመለከተ ሁላችሁም እንደምታውቁት ሕወሀት ማዕከላዊ የፖለቲካ ስልጣን ሲጨብጥ ፀረ-አማራ አቋም ባደባባይ በማናፈስ የተቀሩትን ብሔሮች ከጎኑ በማሰለፍና አማራውን በማስመታት ለአገዛዙ ጠንካራ መሰረት ለመጣል ችሏል። በዚህ አንገፍጋፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል በተፈፀመበት ወቅት የሁኔታዎቹ አካሄድ ወደ እርስ በርስ ጦርነት አምርቶ ውጥንቅጥ ውሰጥ ላለመግባት መአሕድ ተቋቋመ። ይህ ክስተት በቴሌቭዥን በመለሰ ዜናዊ፣ በፕሮፌሰር መስፍንና በሌሎች መካከል የአማራ ብሔረሰብ አለ ወይም የለም የሚል እሰጣ ገባ አስከትሎ ነበር። ፕሮፌሰሩ “አማራ ብሔረሰብ ሳይሆን አማርኛ ተናጋሪ አለ” ብለው መደምደማቸውን ማንም አይረሳውም። ይህ አባባል በውቅቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ቆሽት አንድዷል። በዘር ላይ የተመረኮዘ አላማ ለሚያራምዱ ድርጅቶችና ብሔረተኛ ተራኪዎቻቸው ግን አባባሉ አስፈንጥዟቸዋል። ነገር ግን እነዚህ ቡድኖች ራሳቸው “መመሪያ” ብለው ያተሟቸውን ሰነዶች መለስ ብለው በክርክሩ ወቅት መመልከት ተስኗቸዋል።

              South-east Ethiopia c 1500
ኢትዮጵያን በተመለከተ የተለያየ አቀራረብና ትንታኔ አንዲሁም አቋሞችን ያነገቡ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የታሪክ መፅሀፎችና ጥናታዊ ፅሁፎች አሉ። የዚህ አጭር መጣጥፍ ዋነኛ ትኩረት የኦሮሞ ወረራና ተስፋፊ ብሔረተኛ ትንተናዎች ከታሪክ ማስረጃ አኳያ እንዴት ይገመገማሉ የሚለው ላይ ያተኩራል።

ፀሀፊው በግልፅ ማሳወቅ የሚፈልገው ማንኛውም የሰው ልጅ ታሪክ አዎንታዊ ጎን ያለውን ያህል አሉታዊ ገፅታዎቹም ምንም ሊደብቁት ቢሞክሩም ግዜውን ጠብቆ መውጣቱ የማይቀር መሆኑን ነው። የበርካታ ኦሮሞ (ገዳዎች) ወደ ተለያዩ ኢትዮጵያ ክፍሎች በተስፋፋበትና ወረራ ባከሄዱበት ጊዜና በኋላ ለብዙ ሺህ ዓመታት በራሳቸው ቋንቋ፣ ባህልና ልምድ ይመሩ የነበሩ ብሔሮች ከአቅማቸው በላይ በሆነ ሀይል ተውጠዋል፣ አናሳ ሆነዋል እንዲሁም ከነ ጭራሹ ጠፍተዋል። እስካሁን ባነበብኩትና ባየሁት ታሪካዊ ትንተና (99 በመቶ የኦሮሞ ብሔረተኛ አቋም ላይ የሚያዘነብሉ ተራኪዎች) ሁሉም በአደባባይ ጉዳዩን በማድበስበስና (ገዳ፣ ገባሮ፣ ጉድፈቻ) ወዘተ… በሚሉ አቀራረቦች በመጠቀም መስፋፋቱን ሰላማዊ ለማስመሰልና አሉታዊ ገጽታ ለመስጠት ከመጣር አለመቆጠባቸውንና ምናልባትም “የወጋ ቢረሳን” ብቻ የመረጡና “የተወጋ አይረሳ” የሚለውን ችላ እንደሚሉት ተገንዝብያለሁ። 

ለመንደርደሪያ እንዲያግዝ በሔረተኞቹ ከሚሉት ልጀምር “ኩሾች ኑቢያ፣ ናይሎ ሰሀራን፣ ኦሞቲክን ጨምሮ የኛ ናቸው፤ ሉሲ ከኛ ዘንድ ስለተገኘች የሰው ዘር መፍለቂያም ነን፤ እርሻ በዚህ ዓለም የተጀመረው በኦሮሚያ ነው ይላሉ”። አባባሉ ትረካቸውን ገና ከመጀመሪያው በታሪክ ተመራማሪዎች በኩል ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል። “ከቋንቋና አርኪዮሎጂ ጥናቶችና ምርመራዎች በቅርብ ግዜ በተገኙት መረጃዎች መሰረት እርሻ የተጀመረው የሰሀራ በረሀ ከመከሰቱ በርካታ ክ/ዘመናት በፊት በኢትዮጵያ፣ በመካከለኛው ሱዳንና በናይጀር ነው።” ሲል Africa Emerging Civilization In Sub Sahara Africa በተባለው የፅሁፍ ክምችት ላይ ተዘግቧል። በኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ ኦሮሞዎች በታሪክ የመጀመሪያ መኖሪያቸው እንደነበር የሚያረጋግጡና ዛሬ ኦሮሞዎች የሰፈሩባቸው አብዛኛዎቹ ግዛቶች ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሀይልና በወረራ የተነጠቁ ለመሆኑ በርካታ ምርምርና ጥናትን መሰረት ያደረጉ ፅሁፎች ሞልተዋል። 

የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት በዚህ አባባል አላማውን በሚገልፀው ደበተሩ አይስማማም፣ በተጨማሪ “ሐበሻዎች በዘመናዊ የአውሮፓ መሳሪያ በመደገፍ ማሸነፍ እስከቻሉበት 19ኛው መቶ ክ/ዘ መገባደጃ ድረስ ኦሮሞ ነፃ ነበር” በሚል አቀራረብ ትግል መጀመሩን ያበስራል። በታሪክ ከብት አርብቶ አደር የነበረውንና ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነስቶ ወደ አሁን የኦሮሞ ክልሎች ተስፋፍቶ በሌሎች ሕዝቦች መሬት ላይ ሊሰፍር እንደቻለ ያሉትን ተጨባጭ የታሪክ ሀቆችን በማዛባትና በውሸት የፈጠራ ወሬ ያልነበረና ያልተደረገ ታሪክን ከአቀንቃኞቹ ጋር በመሆን መፃፍን ገፍቶበታል። Oromo Migration & Their Impact በሚል ርዕስ የUS Library of Congress ባቀረበው ህትመት በ16ኛው መቶ ክ/ዘ አጋማሽ … ኦሮሞዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ጫፍ ሰፍረው የነበሩና በከብት አርቢነት ላይ ተመስርተው በተለያዩ ተፎካካሪ ቡድኖች የሚተዳደሩ ነበሩ። ይህም ለጦርነት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል … በ1550 እ.አ.አ አካባቢ አጥፊ ወረራዎችና መስፋፋቶችን (predatory expansion) በጎረቤቶቻቸው ላይ ፈፅመዋል …” ሲል ሀቀኛውን ታሪክ ገሀድ አድርጓል። ይህም የሚያመለክተው ከ460 ዓመት በፊት የተጀመረው ወራሪና ተስፋፊ አክራሪ ብሔረተኝነት በ21ኛው ክ/ዘ መልኩን ከ(ገዳ) ወዘተ… ወደ “መገንጠል” ጥያቄ ቀይሮ በመካሄድ ላይ መሆኑን ነው። 

በመሰረቱ ዛሬ ኦሮሞ ተስፋፍቶ የያዛቸው መሬቶች ከ16 ኛው መቶ ክ/ዘ አጋማሽ በፊት አንድም ኦሮሞ ኖሮበት የማያውቅባቸው ግዛቶች በታሪክ ሀብትነታቸው የእነ ሪያ ዳሞት፣ ማኦ፣ ኮሞ፣ መዠንገር፣ ሺናሻ፣ ከፋ፣ የም፣ አማራፈተጋር፣ አርጎባ፣ ደዋሮ፣ ባሊ፣ አዳል(ሀውዳል)፣ ሀረሪ፣ ጉራጌ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ጌዲዮ፣ ሀድያ፣ ጋፋት፣ ሸካና ሌሎች ናይሎ ሰሀራዊና ኦሞቲክ ሕዝቦች ሲወርድ ሲዋረድ በቋንቋቸው፣ በባህላቸውና ልምዳቸው ተከብረው የኖሩባቸው ለመሆኑ አመላካች ታሪካዊ ማስረጃዎችን ወደ ጎን በመግፋት ሀቁ ሁሌ ተደብቆና ተድበስብሶ ይኖራል በሚል የተሳሳተ አካሄድ ብሔረተኞቹ መምረጣቸው ዞሮ ወደፊት ለነርሱም ችግር መፍጠሩን አርቀው ያስተዋሉ አይመስልም። ባሁኑ ግዜ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ኦሮምኛ መጠሪያ ስላላቸው ቦታዎች Marco Vigano From Barara To the Indies በሚለው የአርኪዮሎጂ ጥናቱ “ሌላና ባዕድ የሆነው ባህልና ልምድ ባስከተለው ወረራ የአካባቢና ቦታዎች ስሞች ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተቀይረዋል …” በሚል ካቀረበው ማብራሪያ ጋር እንጂ ከብሔረተኞቹ ትረካ ጋር ማያያዙ ትክክል እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። 

ለምሳሌ በመልካ ቁንጥሬ ያሉትን የረጅም ዘመን ያላቸው የድንጋይ ትክሎችና ታሪካዊ ቅርሶች በማንኛውም ሳይንሳዊ ስሌት ጨርሶ ከኦሮሞ ጋር ግንኙነት የላቸውም። ቦታውን ከደዋሮና ምናልባትም ከጋፋት ወይም ጉራጌ ሕዝቦች አሰፋፈር ጋር ማያያዝ ይቻላል። ምክንያቱም በዛን ግዜ ኦሮሞ ኑዋሪነቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ጫፍ ኬንያ ድንበር ላይ ብቻ ነበር። ሌላው የዛጉዌና የክርሰትያን ኢትዮጵያ ስርአት በ12ኛው ክ/ዘ ማለትም ኦሮሞ ባካባቢው መታየት ከመጀመሩ 450 ዓመት በፊት ለመኖሩ በመልካ ቁንጥሬ የአዳዲ ማሪያም ውቅር (ፍልፍል) ድንጋይ ገዳም፣ በመተሀራ የተገኙት ጥንታዊ የፈላሻ ማምለኪያዎችን ወዘተ… መጥቀሱ በቂ ይመስለኛል። 

ሌላው በኦሮሞና ሶማሌ ብሔረተኛ ተራኪዎች መሀል ያለው የአዋሽ ወንዝ አካባቢ ጥንታዊ ታሪክ ጭቅጭቅ አንዱ ራሱን የቻለ ትንተና ስለሚጠይቅ በዚህ ፅሁፍ አይቀርብም። ነገር ግን ብሔረተኞች እንደሚያነበንቡት ሳይሆን ሁለቱን በተመለከተ H.S.Lewis the origin of the Gala and Somali በሚለው ጥናቱ “በተለምዶ ጋላ በአፍሪካ ቀንድ ከሱማሌ ቀድሞ (በፊት) ሰፍሮ ነበር የሚለው አገላለፅ አሁን ተቀባይነት የለውም።” ያለውንና በርካታ የታሪክ ምሁራን በዚህ ጉዳይ ያቀረቡትን ምርምር ወደፊት በሌላ ርዕስ እመለስበታለሁ። (በጥቅሱ የቀረበው የቃላት ምርጫ የ H.S.Lewis እንጂ የእኔ አይደለም)።

አሁን ለሰለባ ትኩረት የተደረገው የመስፋፈት ጥማት በፀረ- አማራ የፕሮፓጋንዳ ስራና አመቺ ሁኔታ ከተፈጠረ አማራውን በመጨፍጨፍ ግዛቱን መቀራመት ላይ ነው። እዚህ ላይ በርካታ ምሁራንን በማቀፉ የሚወሳለት የኦሮም ድርጅት ለምን (ሐበሻዎች) የሚለውን ቃል እንደተጠቀመ ባይገባኝም አረቦች የኢትዮጵያ ሕዝቦች የተደበላለቁ ወይም የተካለሱ መሆኑን መሰረት በማድረግ የአገሪቱን ነዋሪዎች ሊገልፁ የሞከሩበት መጠሪያ ስለመሆኑ ግን አጥተውት አይመስለኝም።

ሁላችንም የምንስማማበት ጉዳይ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ብሔር ብሔረሰቦች አለማጋነን ከሁሉም በደም የተዋሀደና የተዋለደ፣ በ16ኛው ክ/ዘ አጋማሽ ጀምሮ ከደቡብ የአገሪቱ ጫፍ ተነስቶ ዛሬ በያዛቸውና በተቆጣጠራቸው ገዥ ግዛት አኳያ በቀዳሚነት የተሳካ መስፋፋት ያደረገው ኦሮሞ ቅኝ- ገዢ ብሔረሰብ እንደሆነ ነው። ዋነኛው ኦነግንና ብሔረተኛ ተራኪዎቹን የሚያስደነግጠውና ዛሬ እነርሱ ተጠናክረውና ተደራጅተው “መገንጠል” ላይ ያተኮሩትን ያህል በተራው የዛሬዎቹን ምራብና ምስራቅ ወለጋ ከሚባሉት በኦሮሞ አስከፊ ወረራና መስፋፋት የተገፋውና የተጨፈጨፈው የበርታ፣ ማኦና ሌሎችም ብሔሮች አንድ ቀን አብረው ፀረ ኦሮሞ ትግል ያነሳሉ ብለው ማሰባቸው ነው። 

ይህ አንድ ምሳሌ ሲሆን የኦሞቲክ አባልና እየነቁ ታሪካቸውን በጥልቀት በማወቅ መንቀሳቀስ የጀመሩት ከፊቾና የም ብሔረሰቦች እስከዛሬ ድረስ ሰሚ አጥተውና ተበድለው እንጂ ጂማ በሙሉ የነርሱ እንደሆነና በኦሮሞ ሰለባ ታሪካዊ ግዛታቸውን ስለመነጠቃቸው ድምፃቸውን በአደባባይ ከማሰማት ከንጉሡ ጊዜ ጀምሮ ቦዝነው አያውቁም። መዠንግሮችና ሸካም ብሔረሰቦችም ዛሬ ኢሉባቦር በሚባለውም ቦታ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው። በባሌና ሀረር ደግሞ ሱማሌዎች ኦነግን የሚያስበረግግ የይገባኛል ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ከብሔረተኛ ኦሮሞዎች ጋር በየአጋጣሚው ግጭቶችን ከማድረግ ያልተቆጠቡና ወደፊትም ፍጥጫው ቀጣይነቱ ጥርጥር የለውም።

 በኦሮሞ ወረራ ዘመን ዳር ድንበራቸውን የተነጠቁት ዛሬ አናሳ የሆኑት ብሔሮች በፖለቲካ ንቃት እየጎለበቱ በሄዱ ቁጥርና የዘመኑ ስልጣኔ ተቋዳሽ አካል መሆን በመጀመራቸው ኦነግ በፃፈው የሀሰት ታሪክና ድርጅታዊ አቋም ተከታይ አክራሪ ብሔረተኞቹ ራሳቸው በከፈቱት በር ኦሞቲኮቹና ናይሎ ሳሀራዎች ሰተት ብለው በመግባት የነፃነት አቋም ያነገበ ትግል በመጀመር ኦሮሞዎቹን ወደ መጣችሁበት ተመለሱ ማለታቸው የማይቀረር የወደፊት የታሪክ ሀቅ ነው። ሌሎችም በየተራ ይነሳሉ። ለኦሮሞ ነፃ አውጪ ቡድንና ብሔረተኞችም ጉዱ እንደ ጭራ ከበስተኋላ የሚሆንባቸው ግዜ በህይወት ዘመናቸው በነበልባል እሳት እንደሚያቃጥላቸው ጥርጥር የለኝም። 

ለምሳሌ Alfredo Gonzales ና Victor Fernandez በቤኒሻንጉል ሕዝቦች ታሪክና ባህል ላይ ባቀረቡት ፅሁፍ “በ1988 (እ.አ.አ) በአሶሳ የተገንጣዩ ኦሮሞ ቡድን ታጣቂዎች በብዙ መቶ የሚቆጠሩ አማራዎችን ሲገሉ የበርታ ተወላጆችን ጥቁር ኦሮሞ ነን እንዲሉ ሲያስገድዱ በርታዎች እምቢ በማለታቸው በሁለቱ መካከል ግጭት ተፈጥሯል” ። ይህ ጉዳይ አሁን ስር እየሰደደ በመሄድ ላይ ሲሆን በቅርቡ በቤኒሻንጉልና ኦሮሞ ክልል ፖሊሶችና ሕዝባዊ ሰራዊት መካከል ተከስቶ የነበረውን ፀብ(ጠብ) ለማርገብ የፌደራል ጉዳይ ሚኒስትሩ ከቦታው ለማስታረቅ ሄዶ እንደነበር በዜና መነገሩ ተደምጧል (2004 ዓ/ም ጥቅምትና/ህዳር)።

እስቲ በተራ ከፍ ሲል የተቀመጠውን አባባል ከታሪክ አኳያ እንመርምር። ኩሽ ማነው ወይም እነማን ናቸው? በአመዛኙ ታሪክ የሚያስተምረው ጥቁር ቆዳ ያለው ሕዝብ በአፍሪካ የተባዛው ከክ/ዓለሙ በስተምራብ ተነስተው በተስፋፉ (ባንቱዎችና) ከሰሜን ምስራቅ ወደ ምስራቅ በደቡብ አቅጣጫ በተስፋፉት (ኩሾች) እንደሆነ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስ ስላለው ዊኪፒድያ ሲያትት “ኩሽ … የሀም መጀመሪያ ልጅና የኩሽ ሕዝቦች አባት እንደሆነ ይገመታል። እነርሱም ጠይም የቆዳ ቀለም ያለቸውና በጊዮን ወንዝ አካባቢ በጥንቱ ግምት በምድረ አረብያና አትዮጵያ የሚኖሩ ናቸው” ይላል። ይሄው የመረጃ ምንጭ “ኩሽ የሚለው መጠሪያ የመጣው ከምድረ ኩሽ ማለትም (ከዛሬዋ ሱዳንና ከደቡባዊ ግብፅ ከመጣ ጥንታዊ የጎሳ ቡድን) ሲሆን ሁኔታውን ሌሎች ምሁራን ከኢትዮጵያ አይሁዶች ወይም “ቤተ እስራኤሎች” ጋር እንደሚያያይዙት ይጠቁማል። 

በዚህ ጉዳይ የእስራኤላዊያን ዲያስፖራ ክፍል አንድና ሁለትን ለበለጠ መረጃ መመልከት ይረዳል። ባጭሩ ካገላበጥኳቸው መረጃዎች መረዳት የቻልኩት ኩሽ በዛሬዎቹ ሱዳን (ሰሜንና ሰሜን ምስራቅ)፣ በኢትየጵያ ሰሜናዊና ምእራባዊ (በጥቂቱ) ፣ በደቡባዊና ምስራቃዊ (በአመዛኙ)፣ በሶማሊያ፣ በጅቡቲ፣ በሩዋንዳ፣ በታንዛንያ እንዲሁም በአነሰተኛ ቁጥር በኬንያና ዩጋንዳ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ ብቻ ሲዳማ፣ ጌዲዮ(ኦ)፣ ኮንሶ፣ ከምባታ፣ ሀዲያ፣ ኢሳና ሌሎች በኦጋዴን ያሉ ጎሳዎች፣ አፋር፣ ኦሮሞ፣ ቤጃ አማራ ወዘተ. ይገኙበታል። 

አማራውን በተመለከተ ከሌሎቹ የሚለየው ሴማዊ ቋንቋ ተናጋሪ መሆኑና አንዳንድ ምሁራን ከአረቢያ በአዱሊስ በኩል ፈልሰው በመምጣት የሰሜኑን ሕዝቦች ከአክሱም ቀደም ብሎና ከዛም በኋላ በደም፣ በባህልና ቋንቋ ስለበረዙት ዛሬ በሀማሴን፣ አካለጉዛይ ሰራዬና በትግራይ ትግሪኛ ተናጋሪዎች ጋር ክርስትናን ተቀብሎ በመግፋቱ፤ በተጨማሪም በ13ኛው መቶ ክ/ዘ ለመጀመሪያ ስልጣን ላይ ሲመጣ እንደ ኢዛና ተከታዮች (ዘዕምነገደ ይሁዳ) ብሎ በማወጁ እንጂ ሀቀኛ የዘር ግንዱንና በአፍሪካ ቀንድ ከጥንት ጀምሮ ራሱን ችሎ ሰፊ ግዛት ላይ መኖሩን በተለያዩ ሰበቦች በመካድ የፈጠሩት የውሸት ትንተና መሆኑን ታሪካዊ ማስረጃን መሰረት አድርጌ በሌላ ገፅ እመለስበታለሁ።

የአባይ ሰሀራዊዎች (ናይሎ ሰሀራን) እነማን ናቸው? በዚህ ምድብ ያሉት ብሔሮችና ቋንቋዎች በጣም በርካታ ሲሆኑ የሚኖሩትም በምስራቃዊ ሰሃራ፣ በላይኛው የአባይ ተፋሰስ፣ አልፎ አልፎም በቻድና ናይጄሪያ ጭምር በሰፊ ቦታ ላይ ነው። በኢትዮጵያና ሱዳን እንዲሁም በኤርትራ ከሚገኙት መካከል በርታ፣ ማኦ፣ ጉሙዝ፣ ሻኬቾ፣ ኑዌር አኝዋክ፣ መዠንገር፣ ናራ፣ ኩናማ፣ ዲንቃ፣ ባሪ፣ ጎባቶ፣ ወዘተ. ሲጠቀሱ ታዋቂው የኬንያ ማሳይም የዚሁ ግንድ አካል ነው። በተለይም በሱዳን የጠረፍ አካባቢዎች ይበልጡኑ ከጥቁር አባይ ሸለቆ በስተደቡብ ወለጋንና ኢሊባቦርን አካቶ ከእናሪያ ይባል ከነበረው በቀር በመዠንገር፣ በበርታ፣ በማኦና ሌሎች ብሔሮች ለብዙ ሺህ ዓመታት ይኖሩ እንደነበር ታሪክ በማስረጃ ያመለክታል። በዚህ ነጥብ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ። 

በጎጃም ደግሞ በመተከል ጉሙዞች ድሮ ዳሞት ከሚባሉት የዛሬዎቹ ጎጃሞች ጋር ኩታ ገጠም ሆነው በጎንደር ቋራ ወረዳ ካሉት ቀበሌዎች ደግሞ ባንዱ ይኖራሉ። የኦሮሞ አነሳስ መቼና እንዴት ነበር? በዚህ ጉዳይ መላው የታሪክ ተመራማሪ የተቀራረበ አመለካከት ወስደዋል። በመጀመሪያ ኦሮሞዎች ሰፍረው የኖሩት በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ ጫፍ በኬንያ ድንበር ብቻ ሲሆን ከብት አርብቶ አደሮች እንደነበሩም ታውቋል። ለምሳሌም እንዲረዳ በቤትዝዌል (አፍሪካ ከ16ኛ-18ኛ ክ/ዘ) በተባለ መፅሀፍ ላይ ያለውንና ደቡብ ኢትዮጵያን አመላካች ካርታ ይመልከቱ።

በተለይም ከግራኝ አህመድ ወረራ በኋላ የአገሪቱ ክርስትና እንዲሁም ተቀናቃኛቸው እስልምና አስፋፊ ወገኖች በመዳከማቸው የተለያዩ የኦሮሞ ጎሳዎች በደቡብ፣ በመሀል፣ በምዕራብና ሰሜን ከፍተኛ ቦታዎች የ(ገዳ) ስርዓት በፈጠረላቸው የጦረኝነት ባህል ከአስራ ስድሰተኛው ክ/ዘ አገማሽ ጀምሮ በባሌ፣ በደዋሮ (ከዳውሮ ይለያል)፣ በፈተጋር፣ በሲዳማ (ሙሉ ለሙሉ ያልተሳካ)፣ በአማራ፣ በአዳልና አዋሽ(ኀዋስ) ፣ በአርጎባ፣ በደቡብ፣ በበርታ፣ በማኦ፣ በዳሞት፣ በመዠንገር፣ በኢሳ ሕዝቦች ላይ አስከፊ የሆነ ጭፍጨፋና ወረራ በማካሄድ ቋንቋቸውንና ልምዳቸውን በጉልበት አስፋፍተዋል።

 ከብሔረተኞቹ በኩል ለምሳሌ ሞሀመድ ሀሰንና ተሰማ ተአ(ጠአ) ይሄን አስመልክቶ አሮሞው በወረራቸው ሕዝቦች በኩል (ተሸናፊዎቹ) በደስታና በሰላም በኦሮሞ ባህልና ቋንቋ መዋጥን (assimilation) ተቀብለዋል ይሉናል። በወራሪና በተወረሪ፣ በገዳይና በተገዳይ፣ አገርንና ሀብትን በሚቀማና በተቀሚ፣ በአጥፊና በጠፊ መካከል መቼ ነበረ ይህ አይን ያወጣ ቅዠት በታሪክ ተመዝግቦ የተገኘው? ስለ (ገዳ) ብዙ ተብሏል። እውነትው ግን ገዳ ገባርነትን ከነቃሉ ጭምር በኢትዮጵያ ያስተዋወቀ በወራሪ ጦር የማዕከላዊ እዝ አመራር ሆኖ ለብሔረሰቡ የተሳካ መስፋፋት ሚና የተጫወተ ከቅኝ ገዢዎች ዋነኛ ስልት ጋር በሚወዳደር ደረጃ በሕዝቦች ላይ ሰለባና ጥፋት ያስከተለ ክስተት ነው። 

ምንም እንኳን በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ በዚህ ፅሁፍ የተጠቀሱት ብሔረተኛ የኦሮሞ ታሪክ ተራኪዎች ሳይቀሩ በትንተናዎቻቸው በማያሻማ ሁኔታ በተለያዩ አቅጣጫዎች የተደረጉትን ወረራዎች ለምሳሌ (የሀርሙፋ ገዳ፣ የሮበሌ ገዳ፣ ወዘተ…) በሚል ገለጻ ማቅረባቸው የስርአቱን (ገዳ) አሉታዊ ጎኖች ራሳቸው ሳያስቡት መስክረዋል። በናይሎ ሰሀራዊ በርታዎች፣ በማኦና መዠንገር ላይ የሜጫ (ገዳ) ኦሮሞ ባደረሱት ጭፍጨፋ የተረፉት ሸሽተው ካገራቸው ማለትም ዛሬ ወለጋና ኢሉባቦር ከተባሉት በመሰደድ ሱዳን ድንበር ስር ተወስነው በአናሳነት እሰካሁን ድረስ የመኖራቸውን ሀቅን ኦነግም ሆነ ፀሀፊ ብሔረተኞች ደብቆ መኖርን መርጠዋል። 

ትሪዩልዚ በዚህ ጉዳይ ኮፒቶፍን ጠቅሶ ሲፅፍ “በጦርነት የተሸነፉትን ሕዝቦች ወደ ኦሮሞነት ለመዋጥ የተወሰደው ዕርምጃ ፖለቲካዊ አቋምንና ወታደራዊ ሀይልን የተደገፈ እንጂ ሰላማዊ አልነበረም። በትክክል የተደረገው ተሸናፊዎቹን … ናይሎ ሰሀራዊያንን ደረጃ በደረጃ መተዳደሪያ ከሆነው መሬታቸው በሜጫ ሰፋሪዎች መፈንገል ነው። ባሁኑ ግዜ ይህንን የተወሳሰበና አስከፊ ክስተትን ገዳን ምን ያህል (ዲሞክራሲያዊ) ወይም (መደብ አልባ) ሰርዓት ነው በማለት ለመደባበቅ (ለመሸፈን) የሚደረገው ጥረት አይረዳም። ያለፈውን ታሪክ ለማጣራትና እውነቱን ለመገንዘብ ጉዳዩን እንደገና ማጥናት (መጎብኘት) እንጂ ፈጠራና ውሸት ላይ በተመረኮዘ ትረካ (mythologizing) ማድረግ አይገባም።” 

እኔ ግን ላስታውሳቸው እሻለሁ። ለምሳሌ ሕወሀት “ትግሪኛ ተናጋሪ ሁሉ ትግሬ ነው” ኦነግም “ኦሮምኛ ተናግሪ ሁሉ ኦሮም ነው” ሌሎቹም በተመሳሳይ ሁኔታ እንወክለዋለን ስለሚሉት ሕዝብ እንድዚህ በማለት አውጀዋል። የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ግን ስሜታዊነትን ወደ ጎን በማድረግ ሰውዬው (ፕሮፌሰሩ) ለምን በራሳቸው ታሪክ እንኮፍ ለመትከል እንደወሰኑ የሚከተለውን እንዲፅፍ አነሳስቶታል። ፕሮፌሰሩ በክርክሩ ላይ በበኩላቸው የነዚህን ሀይሎች ወንጌል በመጥቀስ ለማስተላለፍ የሞከሩት መልእክት በተዘዋዋሪ “አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አማራ ነው” ብለው ለማስቀመጥ የሞከሩት ልክ እንደ ተቀሩት ጎጠኞች “አማርኛ” የሚናገር ኢትዮጵያዊን ሁሉ አማራ ነው ወደሚል አቀራረብ ለማመልከት እንጂ “አማራ የሚባል ብሔረሰብ የለም” ለማለት ፈልገው የወሰዱት ግላዊ አቋማቸው አይመስለኝም። 

እዚህ ላይ አንባቢ የራሱ አመለካከት እንዳለው ይገባኛል። ተከራካሪዎቹን ለስማ አባባላቸው በግዜው ግልፅ ባይሆንም አመለካከታቸው ግን ፕሮፌሰሩን ጨምሮ በተመሳሳይ “አንድ ቋንቋ የሚናገር ሕዝብ ትግሪኛ ትግሬ፣ ኦሮምኛ ኦሮሞ፣ አማርኛ አማራ ነው ወዘተ…” የሚል ስለነበር “ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ” እንደሚባለው ተከራካሪዎቹ በሙሉ በብሔረተኝነት አመለካከታቸው አንዱ ካንዱ የሚተናነሱ ሆነው አላገኘኋቸውም። የአማራ ታሪካዊ አመጣጥ፣ የአማራ ሕዝብና ቋንቋ እንዲሁም መሰረታዊ ግዛቶቹ በጌምድርና ሰሜን ጎጃም፣ አንጎት(ያሁኑ ወሎ)ና ሸዋ መሆናቸው በተጨባጭ ታሪካዊ ጥናቶችና ማስረጃዎች ተረጋግጧል። 

ይህ ማለት ደግሞ አማራው በግዛቱ ሁሌ ቀዳሚውን ሚና ይጫወት እንዳልነበርም ግልፅ ነው። ለዚህም የዛጉዌ አገዛዝን የአገዎች፣ በሸዋ ምስራቅ ዳርቻ የኢፋት ሱልጣናዊ አሰተዳደርን በዋነኛ ምስሌነት መጥቀስ ይቻላል። በዚህ ጉዳይ ሪቻርድ ፓንክረስት The Ethiopian Borderlands በሚለው መፅሀፍ “እንደ አል ኡማሪ አገላለፅ ኢፋት ከኢትዮጵያ የእስልምና ተከታይ ጠ/ግዛቶች ትልቁ፣ ሀብታምና ኗሪዎቹም ሀበሽኛ ተናጋሪዎች ነበሩ ያለው ምናልባት አማርኛ ተናጋሪዎች መሆናቸውን ለመግለፅ አስቦ ያለው ነበር” በሚል አቀራረብ አስቀምጠውታል። ዛሬ በሸዋ ይፋቴዎች በአመዛኙ ክርሰትያኖች ቢሆኑም አነስ ቢሉም እስላሞችም አሉባቸው። ባህላቸውና ቋንቋቸው አል ኡማሪና ፓንክረሰት እንዳስቀመጡት አማርኛ ነበር፤ አሁንም ነው። 

አገዎች ግን በበኩላቸው ጥንታዊና የቅድሚያ መሰረታዊ አሰፋፈር በመላው ሰሜናዊ ኢትዮጵያ ያላቸውና በራሳቸው ቋንቋ ለብዙ ሺህ ዓመቶች በመጠቀም የኖሩ የበርካታ ታሪክ ባለቤቶች ናቸው። የአማራው ዝርያ ምንጭና አማራም የበህር ልጃቸው ለመሆኑ ጥርጥር የለውም። International Encyclopedia of Linguistics ላይ ዊሊያም ፍራውሊ እንደፃፉት “ያለምንም ጥርጥር (certainly) በጥቁር አባይ በስተሰሜንና በቤሽሎ ተፋሰስ አቅራቢያ በዛሬዎቹ በጌምድርና ወሎ አማራ የሚባል ጥንታዊ ግዛት ነበር …” ብለው ቋንቋን መሰረት ያደረገና ሌሎች ታሪካዊ ሀቆችን ተንትነው አስፍረዋል።

 ሮላንድ ኦሊቨር ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አጠናክሮ በሚከተለው አባባል ገልፆታል “በአማራ ድሮ ክርስትያኖች በ9ኛው ክ/ዘ ሲሰፍሩ በዘገቡት ማስረጃ አማራ ተብሎ የሚጠራ ከነርሱ የተለየ ጎሳና ቋንቋ የሚናገር ህዝብ በተከዜ ወንዝና በምስራቃዊ ሸለቆ ባሉት የአባይ ገባሮች መካከል ስለመኖሩና ይህም ተተኪ የሌለውና ጠቃሚ መረጃ (invaluable note) በአቡነ ተ/ሀይማኖት ገድልና ማስታወሻ ተጠብቆ እንደሚገኝና መረጃውም የአቡኑ የቅም ቅም አያቶች ከ18 ትውልድ በፊት ዳውንት በሚባል የአማራ አገር መስፈራቸውን ያመለክታል።” ይሄው የታሪክ ተመራማሪ አማራዎች በ9ኛው ክ/ዘ ከክርስትና ጋር መተዋወቅ ቢጀምሩም ለበርካታ ዘመናት በተለያዩ ነገሮች አማኒዎች (አማኞች) እንደነበሩ በሰፊው ዘግቧል። 

በአማራ የመጀመሪያው ገዳም የተመሰረተው በድሮው አንጎት (የዛሬው ወሎ) ሐይቅ ከ12 ክ/ዘ ወይም አንድ ሺህ አንድ መቶ ዓመት በፊት ከአክሱም ተሰደው በመጡ ሰዎች እንደሆነ ይነገራል። ከፍ ሲል የተጠቀሰው ተመራማሪ አያይዞም “በአንጎት የሐይቅ ደሴ ገዳም የምስረታ ታሪክ በዘጠነኛው ክ/ዘ እንደሆነና ባቅራቢያው የሚገኘው ቤተክርስትያን (ተ/ሀይማኖት) ከተሰራ 720 ዓመት በኋላ በሙስሊም ጦር (ግራኝ ወረራ) እ.አ.አ በ1532 መቃጠሉን የታሪክ ዘጋቢ ለነበረው አህመድ ኢብራሂም ተነግሮት ነበር” በሚል ሁኔታውን ለማብራራት ተጠቅሟል። (በዚህ ጥቅስ በቅንፍ የተቀመጡት በራሴ ለመረዳት እንዲያመች አካትቻለሁ)። 

ሆኖም በላስታ ያለውንና አስደናቂውን የአቡነ መርቆሪዮስ ውቅር ድንጋይ ገዳም ስንመላከት ከ አንድ ሺህ አራት መቶ ዓመት በፊት በአክሱሞች ዘመን መሰራቱ (ከዛጉዌ መግነን አስቀድሞ) ምናልባትም አማራ ውሰጥ ክርስትና የሮላንድ ኦሊቨርና ሌሎችም ጥናቶች ከሚሉት 300 ዓመት ቀድሞ ገብቷል ማለትም ይቻል ይሆናል የሚል አቀራረብም አለ። ዛሬ በሐይቅ የእስጢፋኖስን ገዳም ለሚጎበኝ በጥንት አማራው በዘንዶ አማኒ (አማኝ) እንደነበር አመላካች የሆኑና ለሚመለክለት ዘንዶ መስዋዕት ማቅረቢያ የአርኪዮሎጂ ቅሪት ቁሳ ቁሶች በክብር ተጠብቀው ስለሚገኙ መመልከት ይቻላል። በዚህ ነጥብ መካተት ያለበት ደግሞ ዳሞትና ጋፋት ከአማራ ጋር የነበራቸው የግዛት፣ የባህልና የቋንቋ ትስስር ነው። ባአሁኑ ወቅት ከአባይ ሸለቆ በስተደቡብ የሚገኘው ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ወለጋ በተባለው ሰሜናዊና ሰሜን ምዕራባዊ መሬቶች ጥንታዊ የዳሞት ሕዝብ ሰፍሮ የኖረባቸውና ያስተዳደራቸው ናቸው። 

በአቡነ ተ/ሀይማኖት ገድል ተፅፎ የሚገኘው ማስረጃ ደግሞ የዳሞት ድንበር እስከ ጀማ(ጃማ) ወንዝ የዘለቀና ዛሬ ምዕራብ ሸዋና ሰሜን ሸዋ ተብለው በኦሮሞ ውስጥ እንዲከካተቱ የተደረጉትን ግዛቶች የሚያጠቃልል እንደሆነ በአስረጅነት ሰፍሯል። ዳሞት በዘር ግንድ፣ በባህል፣ ልምድና ሀይማኖት የአገውና የአማራ ደም ያላቸውና ቋንቋቸውም የአገውና አማርኛ ቅይጥ ወይም በክርስትና ከአክሱም ወደ ታች መስፋት በተነሳ ግዕዝ ተናጋሪዎች እንደሆኑ ታሪክ ይጠቁማል። ጋፋት በመሰረቱ አማራ ሲሆን ቋንቋው ራሱ አማርኛ ሆኖ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ (ክሪዮል) ወይም የወፍ ቋንቋ አጥብቀው በልምድ ሲወርድ ሲዋረድ ይጠቀሙ እንደነበር በጥናት ተረጋግጧል። 

እዚህ ላይ ጋፋት ሞቷል የሚባለው የወፍ አፍን መሰረት ያደረገ የነበረው መግባቢያዊ ስልትና ልማድ መጥፋቱን የተንተራሰ እንጂ የሕዝቡን ታሪካዊ የዘር ግንድና ባህል በተጨማሪም የቋንቋውን ይዘት፣ ቅርፅና መገለጫ 99 በመቶ አማርኛ መሆኑን ያላገናዘበ ድምዳሜ እንደሆነ ተመራማሪዎች ደርሰውበታል። ዎልፍ ሌስላው የትባሉት የቋንቋ ተመራማር የጋፋት ሰነዶች በሚለው 50 ዓመት በፈጀ ጥናታቸው እንዳጠቃለሉት “የቋንቋ ጥናት አዋቂን ሊስበውና እንድያውቀው የምሻው በምርምሬ በጋፋት ነጋዴዎች፣ ቀልደኞች (አዝናኚዎች)ና ውቃቢ ያለባቸው ሁሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ሲሆኑ ለስራቸው መጠቀሚያ (professional purposes) ቢበዛም ቢያንስም አርቲፊሻል ቋንቋ ይጠቀሙ እንደነበር ነው።” በዚህ ነጥብ ላይ በአማርኛና ጋፋት መካከል ልዩነት አለመኖሩን ማወቅ ካስፈለገ (Gafat Swadesh List the Rosetta Project) መመልከት በቂ ይመስለኛል። 

ይህ ሰነድ ቃል በቃል ጋፈትና አማርኛ አንድ መሆናቸውን በማያሻማ መልኩ አጠናቅሮ አቅርቦታል። የጋፋትን ግዛት በተመለከተ ሮናልድ ኦሊቨር የሚከተለውን ፅፏል “…ሁሉም ጥንታዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጋፋት የሚገኘው በዋነኛው አዋሽ ወንዝ ጅረትና (headwaters) በአባይ ወንዝ ሸለቆ መካከል ነው። … አንዳንድ የጋፋት ጎሳዎች ከታችኛው የጀማ (ጃማ) ወንዝ አካባቢ እስከ ሙገር ወንዝ … የግማሽ ጨረቃ ቅርጽ ያለውን ሰፊ መሬት … ወደ ምዕራብ በመካከለኛው ዘመን ዳሞት እስከ ጉደር ወንዝ ይደርሳል።” ይህን ሁሉ መዘርዘር አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት የአማራ ሕዝብ በውስጡ በርካታ ጎሳዎች እንደማንኛውም ብሔረሰብ አካቶ የያዘና አንድ ወጥ አለመሆኑን ለማመልከት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁትና ማንም በዚህ ነጥብ ሲወያይ ባለመስማቴም ጭምር ነው። 

ለምሳሌ በታሪክ ደምቢያ፣ ወገራ አንጎት(ያሁኑ ወሎ) ፣ ጎጃም፣ መንዝ፣ ተጉለት፣ ቡልጋ በራሳቸው የሚተዳደሩ አማራዎች እንደነበሩ ከብዙ በጥቂቱ መጥቀስ ይቻላል። በተጨማሪም የአማራውን ታሪካዊ የግዛት ስፋትና አሰፋፈር በማያሻማ ሁኔታም ማስቀመጡ ካለንበት ተጨባጭ እይታ አኳያ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘሁት ነው። አማራ ከአረብ አገር ፈለሰ የሚባለው ደግሞ ስለትክክለኛነቱ አሳማኝ ታሪካዊ ማስረጃ ያልተገኘበትና በጥናት ላይ ያልተመረኮዘ አገላለጥ ለመሆኑ ጠንካራ ጠቋሚዎች አሉ። ይህንን ፅሁፍ አማራ ኩሽ ነው ብዬ ነበር የጀመርኩት። እንደሚታወቀው ሁሉም የአረብ ታሪክ ፀሀፊዎች ማለት ይቻላል እንደ ጥንት ግሪኮች ኢትዮጵያን የኩሽ አገር ብለው እንደሚጠሯት ማንም ያውቃል። ለዚህም ዲዮደረስ ሲኩለስን (90-21ክ/ል/በ)፣ ሄሮዶተስ(490- 425 ክ/ል/በ) ወዘተ. መጥቀሱ በቂ ነው። እዚህ ላይ ግልፅ መሆን ያለበት ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ ሰፊ ግዛትን ከደቡብ ግብፅ ጀምሮ እስከ መላው የአፍሪካ ቀንድ በድሮ ግዜ ይሸፍን እንደነበር መታወቅ አለበት። 

Myth, Hypotheses and Facts በሚለው ታሪካዊ ትንተና “የኩሽ ሕዝቦች በጥንት ግዜ በመላው አረቢያ፣ ደቡብ ሜሶፖታሚያ፣ ኤላምና እስከ ሕንድ ድረስ ይኖሩ ነበር” ይላል። በዚሁ ፅሁፍ “ደቡብ አረቦች በመጀመሪያ (originally) ኩሾች(ኢትዮፒክ) ነበሩ። ጥንታዊ ሳባዊያን ከኑቢያኖችና ሀበሾች ጋር የቅርብ ዝምድና (closely related) ነበሩ” ይላል። አማርኛ መሰረቱ ግዕዝ በመሆኑና ፊደሉ ደግሞ አሲራዊያን አረቦችን ወደ ሴምነት ከለዋጧቸው በኋላ በተፈጠረው ቋንቋ ጋር ስለሚወራረስ በተጨማሪም አክሱማዊያን ስልጣኔያቸውና በደምም ወዘተ. ከመካከለኛው ምስራቅ (አረቢያን) ጨምሮ ስለሚዛመድ፣ አማራው ደግሞ በጉርብትና ካለው ኩታ ገጠምነት የተነሳ በባህልና ሀይማኖት ተከታይ ሆኖ ስለተገኘ (አማራውን) ሴማዊና መጤ ነው የሚለው አገላለፅ መሰረት የለውም። 

 ለምሳሌ አገዎች ቀሚርንና ሌሎቹን ጨምሮ ልክ እንደ አማራው በአክሱሞች ባህልና ሀይማኖት ተከታይ ቢሆኑም ቋንቋቸው ኩሽ ስለሆነ ከሴም ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲጠራ አይሰማም። ኮድካ ሶማሊንግ አልቢድል Ethnic groups of Ethiopia ብሎ ባቀረበው ፅሁፍ “አማራ ልክ እንደ አፋር ኩሽ ሲሆን አማርኛ ቋንቋው ግን … ከሴም ቋንቋዎች ጋር ይመደባል … ለፅሁፍ የሚጠቀምበት ፊደሉም ከ2ሺህ ዓመት በላይ ያስቆጠረና በጥንታዊ አረብ አፃፃፍ ላይ የተመሰረተ ነው” ሲል አብራርቷል። ባጭሩ እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች የሆኑ አፍሪካዊያን፣ አረብኛ የሚናገሩ ሰሜን አፍሪካዊያን፣ ስፓኒሽ ተናጋሪ ደቡብ አሜሪካኖች፣ ፈረንሳይኛ የሚጠቀሙ አፍሪካዊያንና የሩስያን ቋንቋ የሚናገሩ የድሮው ሰቭየት አካል የነበሩ ሁሉ ወዘተ. እንግሊዞች፣ አረቦች፣ ስፓኞች፣ ፈረንሳዮች ሩስያዎች ወዘተ… እንዳልሆኑ ስለሚታወቅ አማራን ከአክሱሞችና ተወላጆቻቸው በማያያዝ ሴምና አረባዊ ማድረጉ ትክክል አይደለም። 

በ7ኛው ክ/ዘ አካባቢ የአክሱም ሀይልና ሀብት በአረቦች በቀይ ባህር፣ ኤደን የባህረ ሰላጤ፣ በመካከለኛው ምስራቅና ግብፅ ወዘተ… ድልን በድል መቀዳጀትና ሀያል መሆን አክሱም በከፋ ሁኔታ እንዲዳከም ተገዷል። Kingdom of Africa Cradle of Civilization and Humanity በሚባለው መፅሀፍ “በአክሱም መዳከም ተጠቅመው የቤጃ ሰዎች ወደ (አክሱም) ሲዘምቱ አክሱሞች በበኩላቸው ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች የነበሩ በትናንሽ ግብርና ተዳዳሪዎችን በማሸነፍ በአማራ ሰፍረዋል።” ይህ በግልፅ የሚያመለክተው ልክ እንደ አቡነ ተክለሀይማኖት ገድል አማራ ከአክሱሞች የተለየና ከየመን ወይም አረብ አገር ፈልሶ ያልመጣ መሆኑን ነው።

በአጠቃላይ በተለያዩ ግዜዎች ገነው የነበሩት አክሱሞች ዛግዌ፣ አዳል (ሀውዳል) በተለይም በግራኝ ዘመን፣ የኦሮሞ ወረራ ወዘተ. በአማራው ላይ አዎነታዊና አሉታዊ ተፅኖዎች አሳድረዋል። ለምሳሌ ከክርሰትና ሀይማኖት ጋር በተያያዘ የተከተለው መተዋወቅና የአማርኛ ቋንቋ መጎልበት እንዲሁም በንግድ ልውውጥ መጠቀምና አቅምን ማጠናከር ለአማራው የጠቀሙ ክስተቶች ሲሆኑ በተለይም ከግራኝ በኋላም በኦሮሞ ወረራ የብዙ መቶ ሺህና ከዛም በላይ አማራዎች መጨፍጨፍ፣ የገዳሞችና ታሪካዊ ንብረቶች መውደምና የቅርሰ መሬት(ታሪካዊ ግዛት) በሀይል መነጠቅና የመሳሰሉት አፍራሽ ተፅኖዎች ናቸው።

 ከፍ ሲል በተጠቀሱት ጉዳዮችና ሌሎችም ንክኪዎች ሳቢያ አማራው ከተለያዩ ህዝቦች፣ ባህልና ልምዶች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲተዋወቅና እንዲዋለድ አስገድዶታል። ስለዚህ James Minahan, Minatu e Empires … በሚላው ፅሁፍ “የዛሬው አማራ የሴም፣ የሀምና የጥቁር አፍሪካ ድብልቅ የመደብ ጀርባ ያለው ነው።” ሲል ሀቁን አቅርቧል። በአማራው ላይ ወረራና የግዛት መስፋፋትን ተገኑ ስላደረገው ኦሮሞ Richard Pankhurst በዚህ ፅሁፍ በጠቀስኩት መፀሀፋቸው እንደሚከተለው አቅርበውታል “እ.አ.አ ከ1562-1570 በሉባ ሀርሙፋ አማካኝነት ወደ አማራ እስከ በጌምድርና አንጎት ዘልቀዋል። … እ.አ.አ. 1570-1578 በሮበሌ የሉባ መሪነት ኦሮሞ ተዋጊዎች ሸዋን አውድመው ጎጃም ድረስ ገብተዋል። በወቅቱ የኦሮሞ መስፋፋት በአፄ ስርፀ ድንግል ዝዋይ ላይ የጋላ ጦርን ጠንክረው ተዋግተው ወደ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ አባረዋቸው ነበር።

ነገር ግን እ.አ.አ ከ1586 – 1594 የኦሮሞ ግፊትና መስፋፋት በሙለታ የሉባ መሪነት ቀጥሎ አብዛኛው ሸዋና ዳሞት በቁጥጥራቸው ስር ውለዋል።” በዚህ ፅሁፍ በርካታና ግልፅ ታሪካዊ ክስተቶችን በማቅረብ የመንደርደሪያ ማስረጃዎችን በማመላከት ለደጋፊና ተፃራሪ ፀሀፊዎች ወደፊት መወያያ እንዲሆን ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ተሞክሯል። በአማራው ላይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመረው የኦሮሞ ወረራ፣ መስፋፋትና ጭፍጨፋ አሁንም በኦነግ አማካኝነት ቀጥሎ በመካሄድ ላይ መሆኑን በዝርዝርና በማስረጃ አስደግፌ በሌላ ፅሁፍ እመለስበታለሁ።

(ጸሃፊውን በዚህ ኢሜል ማግኘት ይቻላል Telaashenafee74@yahoo.com)

No comments:

Post a Comment