Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, October 19, 2012

ቂል የያዘው ሰይፍ

(ፕሮፌሰር መስፍን):-
Sibhat Nega
በቅርቡ አቶ ስብሐት በአደረገው ቃለ መጠይቅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመው ወያኔ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማርኛ ተናጋሪዎችና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር ብሎአል፤ ልብ ላለው አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው  ነው፤ ከፊት ለፊት የተሰነዘረው አማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኙን ለመምተር ነው፤ ቂል የሚያደርገው አማራ የሚባል ጎሣ ቢኖርም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአማርኛ ተናጋሪዎች ታጥሮ ትግሬንና ኦሮሞን፣ ወላይታንና ጉራጌን፣ ሌሎችንም የማይነካ መስሎት ከባድ ስሕትት ላይ መውደቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ እሱን የሚያህል ሰው የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ አለማወቁ ያሳዝናል፡፡

የቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ዕውቅና እንዲያገኝ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ



የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት መንፈሳዊ ጉዳዮችን የምትከታተልበት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱንና ለተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያለው ግንኙነትና እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል ረቂቅ ሕጉ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ 
 
በትናንትናው ዕለት የተጀመረውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ 31ኛ መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ የቤተክህነቱ የሕዝብ ግንኙነት መምርያ ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ፣ ‹‹ቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አላት፡፡ መንፈሳዊ ቦታ በመሆኗ ግን እስር ቤት የላትም፡፡ ፖሊስም የላትም፡፡ ፍርድ ቤቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው መንፈሳዊ ተግባራትን ነው፤›› ብለው፣ የተጋጩ ሰዎችን በእርቅና በስምምነት እንዲፈቱ ማድረግ ነው፣ ከመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ውጭ የሆነ ጉዳይ ካጋጠመ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከመሀይምነት ባልተላቀቁ ሰዎች ብዛት ከዓለማችን ሶስተኛ ናት ተባለ

Ethiopia

ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ)፤ ከመሀይምነት የተላቀቁ ሰዎች ብዛትን በተመለከተ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ኢትዮጵያ ከዓለማችን በርካታ አገራት ከመጨረሻ ሶስተኛ መሆኗን ይፋ አደረገ።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ከሶስተኛ አለም አገራት ውስጥ አጥንቶ ይፋ ባደረገው በዚህ ጥናት፤ በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ፤ 28 በመቶው ብቻ ፊደል የቆጠሩና መጻፍና ማንበብ የሚችሉ ናቸው ብሎ፤ ከዓለም አገራት መጨረሻ ከተቀመጡት ከማሊና ደቡብ ሱዳን ቀጥሎ፤ ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሶስተኛ ናት ብሏል።

በዚህ ጥናት መሰረት፤ ህዝቦቻቸውን በበቂ ሁኔታ በማስተማር ከህዝብ ቁጥራቸው 99.9 በመቶ በማስተማር ኩባ አንደኛ፤ ህንድ 74.1 በመቶ የተማረ ህዝብ በመያዝ 2ኛ ስትሆን፤ በኢትዮጵያ 28 ከመቶ ብቻ ከአጠቃላዩ ህዝብ ውስጥ ከመሀይምነት የተላቀቀ ነው። ኢትዮጵያ ከ184 አገራት ውስጥ 182ኛ ሆና ነው በ3ኛ ደረጃ የተፈረጀችው።

በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል

ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት  በወለደች በማግስቱ  ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።