Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, April 15, 2012

ፍትህ አጣሁ ያለው የመንግስት ሠራተኛ ፍ/ቤት ግቢ ውስጥ ካለው ዛፍ ወጥቶ አልወርድም አለ

By ፍኖተ ነጻነት, ቁ.37
በደቡብ ክልላዊ መንግስት ዳውሮ ዞን ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰው ሀብት ኃላፊ የነበሩት አቶ አባተ አየለ “ፍትህ አጣሁ” በማለት ፍ/ቤቱ ግቢ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ላይ ወጥተው አልወርድም ማለታቸውን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ የዜና ምንጮቻችን እንደሚሉት “አቶ አባተ አየለ በአመለካከታቸው ምክንያት ተደጋጋሚ በደል ተፈጽሞባቸዋል” ይላሉ፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት “አቶ አባተ አየለ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ አባል ናቸው፡፡ 

በአመለካከታቸው ምክንያት በተደጋጋሚ እያሠሩና እያጐሳቆሏቸው ቆይተዋል፡፡ በረሃ ወሰደው አስረዋቸዋል፡፡ ያለ ምንም ጥፋት ከሥራ አባረዋቸዋል፡፡ መ/ቤቱን ፍ/ቤት ከሶ ወደ ስራ እንዲመለስና የኃላ ቀሪ ደመወዙ እንዲከፈለው ተወስኖለታል፡፡ የደረሰበትን በደልም ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አመልክከቶ ተቋሙ አቤቱታውን በዝርዝር ተቀብሎታል፡፡ የፍ/ቤቱን ውሳኔ ለማስፈፀም በመንቀሳቀስ ላይ እያለ ፖሊስ ለምን እንባ ጠባቂ ተቋም አመለከትክ? እንዴት መ/ቤቱን ትከሳለህ? ብለው በድጋሚ አሰሩት፡፡ 

ጥፋት ካጠፋሁ ፍ/ቤት አቅርቡኝ እንጂ ወደ ሌላ ቦታ አልሄድም፡፡ ብሎ እንቢ በማለቱ ፍ/ቤት ግቢ ይዘውት ገብተዋል፡፡ በትላንትናው ዕለት ፍ/ቤቱ ግቢ ውስጥ እንደገባ ሮጦ በፍ/ቤቱ ግቢ ውስጥ በሚገኝ አንድ ዛፍ ላይ ወጥቶ ተቀምጧል፡፡ ውረድ ቢባል አልወርድም፤ የአካባቢው ባለሥልጣናት በጠቅላላ መጥተው ያነጋግሩኝ፤ በዳውሮ የህግ የበላይነት የለም፤ ፍትህ የለም፡፡ ፍትህ በሌለበት ሁኔታ መኖር አንችልም፡ ፡ በማለት ድምጹን ከፍ አድርጐ እየጮኽ ይገኛል፡ ፡ ህዝብ ተሰብስቦ እንዲወርድ ቢለምነው እንቢ ብሎአል፡፡

ሰው ወደ ዛፉ ሲጠጋ ራሴን ከዛፍ ላይ ጥዬ እገለላሁ በማለቱ ማውረድ አልተቻለም፡፡” በማለት ሂደቱን አብራርተዋል፡፡ ወደ ህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ አቶ አባተ አየለ ዛፍ ላይ እንዳሉ ሲሆን የአካባቢው  ህብረተሰብ ዛፉሥር ተሰብስቦ እየጠበቃቸው ይገኛል፡፡ የወረዳው ፖሊስ ጣቢያ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት በተደጋጋሚ በቢሮአቸው ስልክ ላይ ብንደውልም ስልኩን የሚያነሳ ሰው ባለመኖሩ ጥረታችን ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ከዚህ ቀደም በዚሁ በዳውሮ ከተማ ነዋሪ የነበሩት መምህር የኔሰው ገብሬ በዞኑ የህግ የበላይነት የለም ፍትህ ዴሞክራሲና ነፃነት በሌለበት አገር መኖር አያሻኝም፤ በማለት በራሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ራሱን በማቃጠል መሞቱ የሚታወቅ ቢሆንም በዚህ ወንጀል እስከ ዛሬ ተጠያቂ ሆኖ ለህግ የቀረበ የአካባቢው ባለሥልጣን አለመኖሩ የአገሪቱን የፍትህ ሥርዓት አጠያያቂ አድርጐታል፡፡ 

ዋጋው ቅጥ ያጣ፣ ለባህል ለባርነት የሚዳርግ፣ ኢኮኖሚን የሚየቃውስ፣ ሥነ-ልቡናዊ ጫናን የሚፈጥርና ሌሎች መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን የማቅረብ አቅም የሚያሳጣ ከሆነ “አያስፈልግም! በቃ!” ማለት መቻል አለብን፡፡ በዚህ የባህል ደረጃ አቋሞችን መውሰድ ካልቻልን፤በመሠረታዊ ዕቃዎች ገበያ ደረጃም አቋም መውሰድ አንችልም፡ ፡ በዚህ ደረጃም መውሰድ ካልቻልን መንግሥትን በሚመለከት ደረጃም አቋም መውሰድ አንችልም፡፡ በዚህ ሁኔታ እጣፈንታችን የሚሆነው በባህል እያመካኘንና እያልጎመጎምን ባሪያ ሆኖ መኖር ነው፡፡ በሠለጠኑ አገሮች ቆራጥ ዜጎች ከገበያ ባርነት ነፃ ለመውጣት የተደራጀ ተቃውሞ በማሰማት፣ ነፃና ፍትሐዊ የሆነ የግብይት ሥርዓት እንዲኖር ጫና ይፈጥራሉ፡፡ 

በተጨማሪ ነፃ የሸማቾች ማህበራትን በማቋቋም፣ከዚያም አልፈው የመሠረታዊ ዕቃዋች ሱቆችን በጋራ በመክፈት በሸማችነትም በኢንቨስተርነትም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ ይህን ለማድረግ ቁርጠኝነትና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ፣የማያቋርጥ ጥረትን ይጠይቃል፡፡ ከመንግሥት ባርነት ነፃ ለመውጣት፣ባህሉንና ገበያውን በተመለከተ እንደተባለው ቁርጥ አቋም መያዝና በሠላማዊና ሕጋዊ መንገድ መታገል ነው፡፡ ስለ ሠላማዊና ሕጋዊ ትግል በቃል ብዙ ተብሏል፡፡ አሁን የቀረው በዕውቀትና በሕጋዊነት ላይ የተመሠረተ ተግባር ነው፡፡ 

አምባገነን ሥርዓት በሰፈነበት አገር ውስጥ በዕውቀትና በሕጋዊነት ላይ የተመሠረተ ተግባር ጉዳት ያስከትላል፡፡ መደብደብ ፣መታሰር፣ መገደል፣ ሌላም የጭካኔ ተግባር ይኖራል፡፡ ይህን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆን ይኖርብናል፡፡ ስቃይ የሌለበት መውለድ፣ መደብደብ፣ መታሰር፣መገደል የሌለበት ነፃነት ቢኖር እንዴት ጥሩ ነበር! ሄንሪ ቫንዳይክ የተባለ አሜሪካዊ ገጣሚ “የድፍረት በሮች” (The doors of daring) በተባለ ግጥሙ እንዲህ ብሏል፡-
Say not too poor but freely give
Say not too weak but boldly try,
You can never begin to live
Until you dare to die ወደ አማርኛ ሲተረጎም የሚከተለውን ይላል፡-ደሀ ነኝ አትበል መስጠት ነው ያለህን ደካማ ነኝ አትበል ሞክር የአቅምህን አለሁ ብለህ ብትል ዘመን እየቆጠርክ መኖር አትጀምርም መሞትን ካልደፈርክ፡፡ አዎ፣ መሞትን ደፍረን በነፃነት መኖር መጀመር አለብን ነው፡፡ ያለው ሌላው አማራጭ እያማረሩ ፣ እያልጎመጎሙ፣ የሚረገመውን እየረገሙ፣ “እሱ ያመጣዉን እሱ ይመልሰው እያሉ የባህል፣ የገበያና የመንግሥት ባሪያ ሆኖ መኖር ነው፡፡ ይህ የኛ ምርጫ ሊሆን አይገባም፡፡ የአዋቂ አጥፊው ...

No comments:

Post a Comment