Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, September 1, 2012

ስብሐት ነጋ የቀድሞ የህወሓት አመራር አባላትን እያደራጁ ነው

አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መስራችና የድርጅቱ የሞራልና የፍልስፍና አባት ተደርገው የሚወሰዱት አቶ ስብሐት ነጋ በ1993 ዓ.ም ክፍፍል ወቅት ከድርጅቱ የተሰናበቱ አባላትን አንድ በአንድ በማነጋገር ድርጅቱ በአዲስ መልክ ህልውናውን እንዲያጠናክር በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ የአውራምባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል፡፡

‹‹መለስ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሀወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው››Nየሚሉት ስብሐት ነጋ ‹‹በትጥቅ ትግሉ ወቅት የጎላ ድርሻ የነበራቸውና ችግርና መከራን ተጋፍጠው ህወሓት ውስጥ በጽናት የዘለቁ አመራሮች ወደ ጎን ተገፍተው፤ ዛሬ ድርጅቱ የእነ አዜብ መፈንጫ ሆኗል››Nማለታቸውን ጠቅሰው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

Ethiopia vs. North Korea - Cry or Die - Movie Trailer [Find Movie link below.

Ethiopia vs. North Korea - Cry or Die - Movie Trailer [Find Movie link below.

Friday, August 31, 2012

ውሸት ሲደጋግሙ እውነት የመሰላቸው ወያኔዎች: ጌዲዮን ደሳለኝ ከኖርዎይ

ይገርማል እኔ በበኩሌ ይኀው ነፍስ ካወኩ ጀምሮ ከወያኔ እውነት የሰማሁበት ቀን አንድም ግዜ ትዝ አይለኝም፥ ውሸታቸው ለራሳቸውም እውነት እስኪመስላቸው ድረስ ነው:: ታድያ ሌላውም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደነሱ ውሸትን እውነት አድርጎ እንዲቀበል ይፈልጋሉ፥ እስከማስገደድ ድረስ::

ሰዎችን የተለያየ የውሸት ማስረጃ እያቀረቡ ማሰር ከመዘውተሩ ብዛት እውነት እየሆነ ማቷል፥ሲሳይ አጌና ለእትም ያቀረበው ያቃሊቲው መንግስት የሚለው መፅሃፉ ለዚህ በጣም ብዙ ማስረጃ ይሰጠናል፥በመጀመርያ ለሲሳይ ትልቅ ምስጋና ይቅረብልኝ::

የወያኔ መንግስት ምን ያህል ለተንኮል ቆርጦ እንደተነሳ፥ስልጣኑን ላለማጣት የት ድረስ እንደሚቆፍር ለመረዳት አያዳግትም፥ የሚያቀነባብሩአቸው ውሸቶች ደሞ ከትልቅ ውሸት እስከ ተራ ውሸት ሊሆን ይችላል፥ ይሄ ለወያኔዎች Normal ነው:: የሚገርመው ግን ህዝቡ ሊጠረጥር ይችላል ብለው እንኩአን አለማፈራቸው ነው፥፥ እስቲ ወደሲሳይ አጌና መፅሃፍ መለስ ላርጋችውና  ገፅ 372 ተመልከቱ::

አዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር ስር ትገኛለች ተባለ::

ኢሳት ዜና:- ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው እለት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ተሰማርተው የጸጥታ ስራ እየሰሩ ነው።

የጸጥታ ቁጥጥሩ እንዲጠናከር የሆነበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ባይቻልም በአንድ በኩል የሙስሊሙ ማህበረሰብ በነገው እለት ተቃውመ ያነሳል በሚል ፍርሀት ወይም በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ የሽኝት መርሀግብር እንዳይደናቀፍ ለማድረግ ታስቦ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስፍሯል።

ህዝቡ በአቶ መለስ ዜናዊ የተንዛዛ የለቅሶ ስርአት ተቃውሞውን እየገለጠ ነው::

ኢሳት ዜና:- የኢሳት ዘጋቢዎች ያነጋገሩዋቸው የህብረተስብ ክፍሎች እንደገለጡት የአቶ መለስ ዜናዊ የተንዛዛ የለቅሶ ስርአት በህይወታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያመጣ ነው።

አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ በኢግዚቢሽን ማእከል ውስጥ በሚካሄደው ባዛር  ባለፈው ሳምንት በ20 ሺ ብር የንግድ ቦታ የገዛ ሰው ለኢሳት እንደተናገረው ፣ የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ተከትሎ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ሆነ የራዲዮ ጣቢያዎች ማስታወቂያዎችን ማስተላለፍ በማቆማቸው፣ የእርሳቸውና በውስጡ ከፍተኛ ገንዘብ በማፍሰስ ቦታ የገዙ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ነጋዴዎች ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገዋል።

Thursday, August 30, 2012

ከጠ/ሚ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ የአንድነት አባላት እየታሰሩ ነው

ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ በደቡብ ክልላዊ መንግስት ደራሼ ወረዳና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ የአንድነት ፓርቲ አባላት እየታሰሩ መሆናቸውን የወረዳው የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ በተለይ ለፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ አስታወቁ፡፡ የወረዳው ሰብሳቢ ለዝግጅት ክፍላችን እንዳስታወቁት ‹‹አቶ መለስ በመሞታቸው ህዝብ ኢህአዴግን በማውገዝና በመቃወም ይንቀሳቀሳል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል፡፡

ህዝብ ለዚህ አላማ እንዳይንቀሳቀስ በየአካባቢው በህዝብ ተደማጭነት ያላቸውና በወቅቱ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸውን በማደን የፈጠራ ወንጀል በመፈብረክ እየታሰሩ ናቸው፡፡ ›› ይላሉ፡፡ የደራሼ ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳፊኮ ታዬ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት ‹‹ የአካባቢው የኢህአዴግ ካድሬዎችና ደህንነቶች ተሰባስበው በህዝብ መካከል መለስ ታሟል መለስ ሞቷል እያሉ የሚያወሩትን እየተከታተሉ ለማሰር ማቀዳቸውን መረጃ ደረሰን፡፡

Wednesday, August 29, 2012

የአቶ መለስ እና የአቡነ ጳውሎስ ህልፈት ለዋልድባ ገዳም መነኮሳት ሌላ መከራ ይዞ መምጣቱን መነኮሳቱ ተናገሩ::

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ያነጋገራቸው የዋልድባ ገዳም መነኮሳት እንደተናገሩት አቶ መለስ ዜናዊ እና አቡነጰ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ ጀምሮ በመኖካሳቱ ላይ የሚደርሰው እንግልት ጨምሯል።

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ወታደሮችን ልከው መነኮሳቱን እያሳደዱ መገኘታቸው፣ ከ13 በላይ መነኮሳት ከገዳሙ ወጥተው እንዲሸሸጉ ግድ ማለቱን ኢሳት ያነጋገራቸው አባት ገልጠዋል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በልዩ ትእዛዝ ተፈታ::

ኢሳት ዜና:- ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ልዩ ትዕዛዝ በፌዴራል ዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ተቋርጦ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲፈታ በተወሰነው መሰረት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተፈትቷል።

ምንጮቻችን እንደገለጹልን በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ተኛ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ የጋዜጠኛውን የዋስትና መብት የማያስነፍገው ሆኖ ሳለ ዐቃቤ ህግ በማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን ይከራከርልኝ ስላለ ብቻ የችሎቱ ዳኛ ማጽደቃቸው እና የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መታሰር፣ እንዲሁም በዕለቱ ችሎት የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነው የኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ባለቤት ሳምሶም ማሞ እና የትዳር አጋሩ የተከሰሱበት የንግድ ፈቃድ ሳያድሱ የመስራት ወንጀል በፍትህ ሚንስትር ዲኤታ ውሳኔ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ መሰናበቱ የፍትህ ሥርዓቱን በሀገር ዓቀፍና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያጋለጠና ያሳጣ ጉዳይ ሆኖ በመንግሥት ላይ ኪሳራ አምጥቷል፡፡

አባይን የደፈረ መሪ የሚል ፎቶ ግራፍ እያዞሩ የሚሸጡ የጎዳና ላይ ነጋዴዎች በፖሊስ እየተዋከቡ ነው::

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ዜናዊን ከዚህ አለም በሞት መለየት ተከትሎ፣ መንግስት በይፋ በየከተማው ሙሾ እአስወረደ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ የአዲስ አበባ ፖሊሶች  “አባይን የደፈረው መሪ” የሚል ጽሁፍ ያለበትን የአቶ መለስ ዜናዊን ፎቶ ግራፍ በፒያሳ ጎዳናዎች ላይ ፣ በ5 ብር ሲሸጡ የተገኙ የጎዳና ላይ አዟሪዎች በፖሊስ ተይዘው የሚሸጡዋቸውን ፎቶዎች እንዲቀሙ ተደርጓል።

Tuesday, August 28, 2012

ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ በበርካታ ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ።

ኢሳት ዜና:- (Aug. 28) የአብዴፓ ፕሬዚዳንት ተደብድበዋል፤ የአንድነት ፓርቲ አባላትም እየታሰሩ ነው። በቂሊንጦ እስር ቤት፡የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር፦“መለስ መሞታቸው በቴሌቪዥን በተነገረበት ጊዜ ሌሎቹ ሲያለቅሱ፤ አንተ ስቀሀል” ተብለው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።

ስብሐት ነጋ የቀድሞ የህወሓት አመራር አባላላትን እያደራጁ ነው

Ethioforum.org: አውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መስራችና የድርጅቱ የሞራልና የፍልስፍና አባት ተደርገው የሚወሰዱት አቶ ስብሐት ነጋ በ1993 ዓ.ም ክፍፍል ወቅት ከድርጅቱ የተሰናበቱ አባላትን አንድ በአንድ በማነጋገር ድርጅቱ በአዲስ መልክ ህልውናውን እንዲያጠናክር በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ የአውራምባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል፡፡

‹‹መለስ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሀወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው›› የሚሉት ስብሐት ነጋ ‹‹በትጥቅ ትግሉ ወቅት የጎላ ድርሻ የነበራቸውና ችግርና መከራን ተጋፍጠው ህወሓት ውስጥ በጽናት የዘለቁ አመራሮች ወደ ጎን ተገፍተው፤ ዛሬ ድርጅቱ የእነ አዜብ መፈንጫ ሆኗል›› ማለታቸውን ጠቅሰው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ 

Monday, August 27, 2012

በመለስ ዜናዊ ሞት ደስታዋን የገለጸችው ወጣት በአደባባይ ተገደለች

ባሳለፍነው ሳምንት የህይወት እልፈታቸውን የሰማነው የህወሃት ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር እና የኢትዮጵያ የቁጭ በሉ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑትን የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት አስመልክቶ ከፍተኛ እና ሳዛኝ ዜና ከሃገራችን የደረሰን ሲሆን በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከልም ከፍተኛ ቅራኔን እየፈጠረ ነው ። 

በተለይም  የጠቅላይ ሚንስትሩን ሞት የዜናን እወጃ ስመልክቶ እንኳን ሞተ ጨካኝ ነበር በማለት የውስጥ ፍላጎቷን በድንገተኛ ሰሜት የገለጸችውን ወጣት ከሜሪካ ለጉብኝት የሄደው የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊ እየተዝናኑ ባሉበት ካፍቴሪያ ውስጥ  በጠርሙስ ጭንቅላቷ ላይ በመምታት የገደላት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።

ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተከትለው ሄደዋል መሞታቸው በአዲስ አበባ በስፋት እየተነገረ ነው።

ዘንድሮ ወያኔን እና ወያኔን አፍቃሪያን ምን ነካቸው ያሰኛል በከፍተኛ አመራሮች ላይ ክፉኛ የሞት ጥላ ጥላውን አድርቶባቸዋል።በዚህ ወር ብቻ ሶስት ታላላቅ ወያኔ እና ወያኔ አፍቃሪያንን በሞት ጥላ ተነጥቀናል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ፣በአዲስ አበባ በአሁን ሰአት በከፍተኛ ደረጃ እየተናፈሰ ያለው ወቅታዊ ወሬ ከመለስ ዜናዊ ሞት ባሻገር  የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ መሞት እንደሆነ ተገልጾአል ። 

የ21 ዓመታት መከራን ያላገናዘበ የወ/ሮ አዜብ መስፍን መሪር ሀዘን፡ በፍቅሬ ዘለቀው (ኖርዎይ)


የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ም/ቤት ታማኝ ምንጮችን ጠቅሰው የአቶ መለስ ዜናዊን ዜና እረፍት ካወጁ እነሆ ከአርባ ቀናት በላይ አለፈው። ይሁን እንጂ አቶ በረከት ስምዖን የሚመሩት የኮምኒኬሽን ሚኒስቴር ቢሮ ሲያቀናብረውና ሲያሰራጨው ከነበረው የውሸት ድራማ፣ አይቀሬነቱ ደርሶ እነሆ በ15/12/04 ዓ.ም ውዥንብር ውስጥ ከተውት ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ተደርጓል። ይህንንም ተከትሎ የአቶ መለስ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ወዳጆች፣ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሪር ሀዘናቸውን እየገለፁና በማስገደድ እያስለቀሱን ይገኛሉ።

የኢህአዲግ አጋር የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የክልል መስተዳድር አካላት፣ በአምሳላቸው ተጠፍጥፈው የተሰሩ የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት ሐላፊዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ ታዋቂ ነጋዴዎች፣ ግለሰቦችና ከመቼውም በላይ በሥርዓቱ ተጠቂ የሆኑውን ብዙሀን ማሕበረሰብ በካድሬዎች እየተገደዱ፣ እንደ ጣዖት ለሚያመልኩት መሪያቸው ሕዝቡን በማስፈራራት በርሀብ በጠበሰ አንጀት እያስለቀሱና ድራማ እያሰሩት ይገኛሉ። እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ ለማኞችና በሆስፒታል የተኙ በሽተኞች የመሪያችሁን ሀዘን ወጥታችሁ ግለፁ መባላቸው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪሚል ሱንግ በሞተ ጊዜ ከተፈፀመው በከፋ ሁኔታ ከላይ ከመንግስት በወረደ ትዕዛዝ እምባ ለማውጣት ሲታገሉ ማየት የሚያሳፍርም የሚገርምም ነው።

Sunday, August 26, 2012

የአቶ ሀይለማርያም ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ኢህአዴግን እያወዛገበ ነው

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ከአራት ቀናት በፊት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ይፋ ባደረገበት ወቅት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤አቶ መለስን ተክተው በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ መወሰኑን ይፋ ቢያደርግም፤ በተለይ በህወሀት በኩል በተቀሰቀሰ ከፍተኛ ተቃውሞ እስካሁን የአቶ ሀይለማርያም ሹመት ሊጸድቅላቸው እንዳልቻለ  የኢሳት የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል።

አቶ ሀይለማርያም ፤የአቶ መለስ አስከሬን ከብራሰልስ አዲስ አበባ የገባ ዕለት ምሽት  በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ሢሰጡ፤ “መለስን መተካት ከባድ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

የኩማ አስተዳደር በይፋ ድንኳን ተክሎ ለቅሶ ተቀመጠ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የኩማ አስተዳደር በተለምዶ ማዘጋጃ ቤት ተብሎ በሚጠራው ቅጥር ግቢ ውስጥ የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን  ሞት አስመልክቶ ሁለት ትልልቅ ድንኩዋኖችን በግቢው ውስጥ ተክሎአል።

አስተዳደሩ ከፌዴራል መንግስት በተለየ የከተማዋ ነዋሪዎች ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ቦታ ያስፈልጋል በሚል ሁለት ትልልቅ ድንኩዋን ትላንት የተከለ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ሐዘናቸውን በለቅሶ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዳይጎበኝ በበላይ አካል ተከልክሏል” ይላሉ የማረሚያ ቤት ምክትል ኃላፊ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ከትላንት በስተያ ዕለት በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16 ወንጀል ችሎት የዋስትና መብቱ ተገፎ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከላከል የተፈረደበት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የታሰረበት ዞን /ቀጠና/ እና ክፍል አልታወቀም፤ ሊጎበኙት የመጡ ሰዎች ሁሉ እንዳያገኙት ተከልክለዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ መጥተው አለ የተባለበት ቦታ ባለመገኘቱ እና የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ሊያቀርቡላቸው ባለመቻላቸው  የተማረሩት የሙያ አጋሮቹ የማረሚያ ቤትን ምክትል ኃላፊን ሄደው ቢያነጋግሩም ኃላፊው “ የፍትህ ጋዜጣ ተመስገን ደሳለኝን ነው፣ በሉ እርሱን መቼም ልታገኙት አትችሉም፣ ይህ የበላይ አካል ውሳኔ ነው፤ ዝም ብላችሁ ምግቡን ብቻ ጥላችሁለት ሂዱ፣ እኛ እናደርሳለን” ብለዋል፡፡