የመድረክ አባል ድርጅቶች የሆኑ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ በብዙዎች ሲጠበቅ የነበረዉን የፓርቲዎቻቸዉን ዉህደት፣ አመራሮቻቸዉ ባደረጉት ስብሰባ አጸደቁ።
የተዋሃደዉ ፓርቲ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ሲሆን፣ ዶር መራራ ጉዲና (ሊቀመንበር)፣ አቶ በቀለ ገርባን እና አቶ ሙላቱ ገመቹን (ምክትል ሊቀምንበር) አቶ በቀለ ነጋን (ጸሃፊ) አቶ ደጀኔ ጣፋን ረዳት ጸሃፊ አድርጎ መርጧል።
እነዚህ የተመረጡት ስድስት የአመራር አባላት 24 ሰዎችን ያቀፈዉ የሥራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነዉ የሚሰሩ
ሲሆን ፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳን ያቀፈ በምክርና በሃሳብ የአመራር አባላቱን የሚደግፍ አዲስ የሽምግሌዎች አማካሪ
ኮሚቴም ተቋቁሟል።
ከተመረጡት የአመራር አባላት መካከል ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ በቀለ ገርባ በአሁኑ ሰዓት መሰረተ ቢስ በሆነዉ
የሽብርተኝነት ክስ ተከሰዉ ፣ ከአንድነት ለዲሞርካሲን ለፍትህ ፓርቲ ምክትል ሊቀመነብር ከሆኑት ከአቶ አንድዋለም
አራጌ ጋር በቃሊት እሥር ቤቱ ይገኛሉ።
የኦሮሞ ሁለቱ ድርጅቶች በአንድ መዋሃዳቸው ፣ የአገር ቤት ትግሉን የበለጠ እንደሚረዳ የገለጹት ያነጋገርናቸው
የፖለቲካ ተንታኝ፣ በተለይም በአሁኑ ወቅት ውህደቱ መፈጸሙ የኢትዮጵያ ፖለቲካ እየተቀየረ መምጣቱን የሚያሳይ
እንደሆነ ይነገራሉ።
በአንድነትና በብርሃንና መካከል የተደረገዉን ዉህደት ያስታወሱት እኝህ ተንታኝ «በመድረክ የታየዉ አብሮ
የመስራት ባህል፣ አንድነትና ብርሃንን እንዲዋሃዱ እንዳደረገዉ ሁሉ ኦሕኮን ና ኦፈዴን አዋህዷል» ሲሉ የሚቀጠለዉ
ሥራ የመድረክ ድርጅቶች በሙሉ ከግንባርነት ወደ ዉህደት ማሸጋገር ሲሉ አስተያየታቸዉን ቋጥተዋል።
No comments:
Post a Comment