ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ባለፉት ሁለት ወራት በጋምቤላ ክልል
ነዋሪዎች እንዲሁም የሼክ ሙሀመድ ሁሴን አላሙዲን ኩባንያ ሰራተኞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ፣ ከታጣቂዎች ጋር በመሆን
ጥቃቱን አስፈጽመዋል የተባሉት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ያለመከሰስ መብታቸው በክልሉ ምክር ቤት እንዲነሳ ተደርጓል።
ኮሚሽነሩ ያለመከሰስ መብታቸው ቢነሳም ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አለመታሰራቸው ታውቋል። የክልሉ
የንግድ ቢሮ ሀላፊና ምክትላቸው ፣ የፋይናንስ ቢሮ ሀላፊዎች ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ወደ እስር ቤት
ተወስደዋል። ሀላፊዎች ለእስር የተዳረጉት ከመምህራን ደሞዝ ጋር በተያያዘ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት በርካታ የክልሉ
ባለስልጣናት እንደሚታሰሩ ታማኝ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘጋቢያችን ገልጧል።
እንዲሁም በትናንትናው እለት
በእናሬ ወረዳ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ሰዎቹ የተገደሉት በወረዳው ነዋሪዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል
በተፈጠረ ግጭት ነው ተብሎአል። ሁለቱ ሟቾች በጋምቤላ ከተማ በዛሬው እለት የቀብር ስነስርአታቸው ተፈጽሟል።
No comments:
Post a Comment