-ሞያሌ የሚገኘው የጦር ካምፕ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል
ከኬኒያ ጋር በድንበር ከተማነትና በደረቅ ወደብነት በማገልገል ላይ በምትገኘውና በኦሮሚያና በሱማሌ ክልላዊ መንግስት በጋራ በምትተዳደረው ሞያሌ ከተማ ሐምሌ 20 ቀን 2004 ዓ.ም ውጊያ መከናወኑን ከሥፍራው ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት የአደጋውን መጠን በትክክል ለመግለጽ ቢቸገሩም ከ20 በላይ የሰው ህይወት መጥፋቱን እና በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደነበር አስታውቀዋል ፡፡
ምንጮቻችን እንደሚሉት “የአካባቢው ባለሥልጣናት ግጭቱ የተደረገው በቦረናና በገሪ ብሔረሰብ መካከል እንደሆነ ቢገልፁም ባልታሰበ ወቅት ከተማውን በመውረር ተኩስ የከፈቱት ቋንቋቸው የማይታወቅና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎች በወሰዱት ፈጣን ወረራ ከሞያሌ ከተማ ኮረብታ ላይ የሚገኘውን ወታደራዊ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ያወደሙት ሲሆን በከተማው ውስጥ የነበሩትን ፖሊስ ጣቢያዎች ዘርፈዋል ተብሏል፡፡
ነዋሪዎቹ ስለደረሰው አደጋ ሲገልፁ 20 ሰው ሞቶ 16ቱ በአንድ ጉርጓድ መቀበራቸውን አይተናል፣ ጥቃቱ የተፈፀመው በየትኛውም ብሔርና ቋንቋ ተናጋሪ ላይ ሳይሆን በወታደራዊና በመንግስት ተቋማት እንዲሁም በታጣቂዎች ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይሁን እንጂ በተባራሪ ጥይት የሞቱ ሲቪሎች መኖራቸውን በመጠቆም በአካባቢው ያለው ኃይል ለጊዜው መቋቋም ተስኖት የነበረ ቢሆንም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ታጣቂዎቹ ከተማውን ለቀው በመሄዳቸው ውጊያው ለጊዜው ቆሞ
እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በኋላም በአካባቢው የተከሰተው ግጭት በከተማው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሥጋት መፍጠሩን፣ ከተማዋን የወረሩት ታጣቂዎች ቋንቋቸው አለመታወቁ ብቻ ሳይሆን የታጠቁት መሣሪያ የአገራችን ሠራዊትና ፖሊስ ከታጠቀው የተለየ ምናልባትም እጅግ ዘመናዊ ሳይሆን እንዳልቀረ ያላቸውን ግምት ሰጥተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የመንግስት አካላት አስተያየታቸውን እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡
Source; Finote Netsanet
Source; Finote Netsanet
No comments:
Post a Comment