Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, April 23, 2012

ሰማያዊ ፓርቲ እስከ አሁን ፈቃድ አላገኘም

ኢሳት ዜና:-
በወጣቶችና በምሁራን የተገነባው አዲሱ ሰማያዊ ፓርቲ እስከ ዛሬ ፈቃድ ሊያገኝ አልቻለም። ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የፓርቲው መስራቾች በቦርዱ የታዘዙትን መስፈርቶች ሁሉ ቢያሙዋሉም፣ የቦርዱ አባላት ግን ፈቃዱን ሊሰጡዋቸው አልቻሉም።

አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የድርጅቱ ሰራተኛ ለኢሳት እንዳሉት፣ ፓርቲው በመላ አገሪቱ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ፊርማዎችን አሰባስቦ ለህዝብ ይፋ ማድረጉ ቢረጋገጥም፣ የቦርድ አባላት ግን ከመንግስት አቅጣጫ አልመጣልንም የሚል ምክንያት በማቅረብ ፣ ፈቃዱን ሊሰጡዋቸው አልቻሉም። የመንግስት አቅጣጫየሚባለው ፣ ከኢህአዴግ ጽህፈት ቤት የሚሰጠው ይሁንታ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታዋቂ ምሁራን ለፓርቲው አባላት ትምህርቶችን እየሰጡ ነው። በቅርቡ ረዳት ፕሬፌሰር ዝናቡ አበራ በኢትዮጵያ ውስጥ በየ14 አመቱ የልውጥ እንቅስቃሴ እንደሚኖር ለፓርቲው አባላት ትምህርት ሰጥዋል። በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር በፈቃዱ ደገፌ ለወጣቶች ትምህርት እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሎአል። የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ፈቃድ በመከልከላቸው ዙሪያ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።

No comments:

Post a Comment