Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, April 26, 2012

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ 5 ሚሊዮን ብር ተዘረፈ

 Source: www.fetehe.com
የአንበሳ ኢንተርሽናል ባንክ ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ሰራተኞች ቅዳሜ ዕለት ስራ ጨርሰው ከወጡ በኋላ ሰኞ ጠዋት ወደስራ ገበታቸው ሲመለሱ 5 ሚሊዮን 500 ሺ የሚጠጋ ገንዘብ ተዘርፎ መገኘቱን ምንጮች ለፍትህ ገለፁ። ባንኩን በዕለቱ ሲጠብቁ የነበሩት የጥበቃ ሰራተኛ የተሰወሩ ሲሆን የተቀሩት የጥበቃ አባላት ዝርፊያውን በተመለከተ ረቡዕ ሚያዚያ 10 ቀን 2004 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቀርበው ቃል ሰጥተዋል።

ምንጮቻችን ባንኩ የተዘረፈው የፋሲካ በዓል ዕለት እሁድ ሚያዚያ 7 ቀን 2004 ዓ.ም ሳይሆን እንዳልቀረ አስረድተዋል።ስለጉዳዩ ለማጣራት ባደረግነው ሙከራ የአንበሳ ባንክ ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ‹‹ፖሊስ የያዘው ጉዳይ ስለሆነ ምንም መረጃ የለኝም›› በማለት ለፍትህ ገልፀዋል።


No comments:

Post a Comment