Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, April 23, 2012

የኢትዮጵያ መንግስት መጠላቱን የሚያሳብቁ ምልክቶች



እንደግለሰብየምንጠላቸውን እንጂ የሚጠሉንን የማወቅ ዕድላችን ጠባብ ነው፡፡ እንደመንግስት ግን ጠባብ አይደለም፤ ሆኖም መንግስታቱ አምባገነንከሆኑ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ጥላቻቸውን የሚገልጹበት ድፍረት አያገኙም ስለዚህ እንደተጠሉ ላያውቁ ይችላሉ የሚል የግል ስጋት አለኝ፡፡ፊደል ካስትሮ በስልጣናቸው ዘመን፣ በሕይወት ታሪካቸው ላይ የተሰራውን ፊልም ሕዝቡ በምን ዓይነት የፍቅር ስሜት እንደሚመለከተውለማየት ራሳቸውን ቀይረው ሲኒማ ቤት ገቡ አሉ፡፡ 
 
እናም ገና ፊልሙ እንደጀመረ የፊደል ካስትሮ ፊት መታየት ሲጀምር ተመልካቹ በሙሉቆሞ አጨበጨበ፡፡ እርሳቸው በደስታ እየፈነደቁ ፀጥ አሉ፡፡ ታዲያ ከጎናቸው ተቀምጦ የነበረው፣ ‹‹አንተ፤ እየተነሳህ አጨብጭብ እንጂ!ካድሬዎቹ ያዩሃል’ኮ›› አላቸው ይባላል፡፡ ስለዚህ የኛዎቹም ይህ ዓይነት ቅዠት ውስጥ ሊሆኑ ስለሚችሉ÷ ሕዝብ እንደጠላቸው የሚያሳብቁአንዳንድ ነገሮችን እናስታውሳቸው፡፡

1. የጋዜጦች አቋምና የስርጭት ብዛታቸው ጉዳይ
አገራችን በሕገመንግስቷ‹ሐሳብን በነፃ የመግለፅ› መብት እንዳስቀመጠች ቢነገርላትም ‹‹ነፃ›› የሚለው እስከምን ድረስ እንደሆነ አጠራጣሪ እውነታዎች እየተከሰቱነው፡፡ መንግስትን የሚነቅፉ ጋዜጦች እና ጋዜጠኞች ወይ ይታሰራሉ አሊያም በስደት አሳራቸውን ያያሉ፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ግን ‹የሚነቀፈውንለመንቀፍ› በሚል የተቋቋሙት ጋዜጦች ቀርቶ ለወትሮው በውበት፣ ፋሽን፣ ፍቅር እና ጤና ጉዳዮች ላይ ብቻ ያጠነጥኑ የነበሩ መጽሄቶችሳይቀሩ ፖለቲካ እንደቅመም ይዘው መውጣት ጀምረዋል፡፡

አንድ ሰሞንቴዲ አፍሮን የሽፋን ገጽ ላይ ይዞ መውጣት የመጽሄቶች ሕልውና እንደነበር ይታወሳል፡፡ አሁን ደግሞ መንግስትን የሚነቅፍ ጽሁፍ ይዞመውጣት ለተነባቢነት ሁነኛ መፍትሄ ሆኗል፡፡ የፍትሕ ጋዜጣ ኮፒ መመንደግ ከዚሁ ከመንግስት መጠላት እና የፍትሕ ጋዜጠኞችም መንግስትንየመንቀፍ ድፍረት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት አለው፡፡

2. ፌስቡክ እና ጦማሮች
አግኝተውትየማያውቁትን ወዳጅ ፍለጋ ፌስቡክ ውስጥ ከሚገቡ ኢትዮጵያውያን ይልቅ ስለወቅታዊ ጉዳዮች ‹ማን ምን አለ?› የሚለውን ፍለጋ የሚገቡትብዙ ናቸው፡፡ በተለይም ከዓረቡ ዓለም የፌስቡክ አብዮት ወዲህ የአገር ልጆች ፌስቡክም በአብዮት ናፍቆት እየተናጠ ነው፡፡ ፌስቡክውስጥ መሪዎቻችንን መሳቂያ፣ መሳለቂያ የሚያደርጉ ምስሎችን ማየት፣ እያንዳንዷን የመንግስት እርምጃ የሚተቹ ጽሁፎችን ማንበብ የተለመደነው፡፡

በተጨማሪምበርካታ ጦማሪዎች የግል ጦማር (blog) እየከፈቱ የግል አስተያየታቸውን መሰንዘር ጀምረዋል፡፡ በዙዎቹ ጦማሪዎች በአገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሲሆኑ÷ መንግስትን በአለንጋ ትችቶቻቸው ከመሽንቆጥ የማይመለሱ ናቸው፤ ለማወደስየተቋቋሙ ጥቂት ጦማሮች ቢኖሩም ባብዛኛው በአንባቢ ድርቅ የሚሰቃዩ ናቸው፡፡

3. የቴዲ አፍሮ ክብረወሰን
በኢትዮጵያሕዝብ ልቦና ውስጥ ቴዎድሮስ ካሣሁን ያለው ቦታ የዘፋኝነት ብቻ ሳይሆን የአርበኝትም ጭምር ነው፡፡ ቴዲ አፍሮ በአጋጣሚ የሚናገራትምሆነ በግጥሙ ውስጥ የሚያስቀምጣት ሐረግ ፖለቲካዊ ፍቺ ይሰጣታል፡፡ የዘንድሮው አልበም ገበያም የደራው እና 10 ሚሊዮን ብር በመሸጥየሃገር ውስጥ ክብረወሰን ለመስበር የበቃው÷ ሕዝብና አጋጣሚ በቸረው የመንግስት ተፃራሪ አቋሙ ነው፡፡

የቴዲ አፍሮ‹ጥቁር ሰው› የተሰኘ አልበም ጥሩ እንደሆነ ሊያስረዱኝ ይሞክሩ ከነበሩ ሰዎች መካከል ይጠቅሱልኝ የነበረው ‹ጥቁር ሰው› እና‹ስለ ፍቅር› የተባሉትን ዘፈኖች ነው፡፡ ስለፊተኛው ‹‹ምኒልክ መወደሳቸው የኅወሓት ሰዎችን አንጀት ያሳርራል›› በሚል፣ ስለኋለኛውደግሞ፡-
‹‹… አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ
     ለምን ይሆንየራበው ሆዴ?....›› የሚለውን ግጥም ይጠቅሱልኛል፡፡

እንግዲህ የቴዲአፍሮ ተወዳጅነትም የሚያረጋግጠው የመንግስትን መጠላት እንደሆነ መፍረድ ቀላል ነው ማለት ነው፡፡

4. የጀማሪ አባሎች ስጋት
ኢሕአዴግ ሰባትሚሊዮን አባላት እንዳሉት ይናገራል፡፡ በርግጥ የአባላት ብዛት የተደጋፊነትን ብዛት እንደማያረጋግጥ (በምርጫ 97) ያረጋገጠው ብቸኛየዓለማችን ፓርቲ ኢሕአዴግ ራሱ ይመስለኛል፡፡ ሆኖም በአባሎቹ ቁጥር ብዛት ሲቪውንና ደረቱን ለማሳበጥ ከመሞከር አልተቆጠበም፡፡ይህ በእንዲህ እናዳለ ምናልባት ሥራ ከተገኘ፣ ምናልባት ሹመት ከተገኘ፣ ምናልባት ነፃነት ከተገኝ፣ ምናልባት ምናምን ከተገኘ ብለውበየወሩ የአባልነት መዋጯቸውን በምናልባት የሚገፈግፉ አባላት÷ አባልነታቸውን በምስጢር መያዝ ይወዳሉ፡፡ መረጃ አፈትልኮ የታወቀባቸውዕለት እንኳን የሚዘባርቁት ምክንያት የገዢው ፓርቲ አባልነት ማሕበራዊ ነውር የሆነ ያስመስለዋል፡፡

ይሄ ሁሉ የሆነውየሆድ ነገር አባል ያደረጋቸው ዜጎች ከተጠላው መንግስት ተርታ ተሰልፈው ከወገናቸው ወዲያ እንዳይመደቡ በመስጋታቸው ነው፡፡

5. ኢቴቪዮጵያ
የኢሕአዴግመንግስት ሁሉንም የመንግስት ሚዲያዎች የፓርቲ ልሳን ቢያደርጋቸውም እንደኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ግን በየቤቱ እያንኳኳ የሚገባ ደፋርየለም፡፡ ምን አስቦ እንደሆነ ባይታወቅም (በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ) ከነጋዴው፣ ከመምህሩ፣ ከክርስቲያኑ፣ ከሙስሊሙ… ከተገኘውሁሉ ጋር በመቀያየም ላይ አትኩሮ እየተንቀሳቀሰ ያለው ኢሕአዴግ በኢቴቪ የሚያቀርባቸው የፕሮፓጋንዳ ዶኩመንተሪዎች የታለመላቸውንያህል ውጤት በማስመዝገብ ፈንታ ለቴሌቪዥኑ ቅጽል ስሞችን አፍርተውለታል፡፡

በኢቴቪ በኩልመንግስት ‹እንዲህ አደረግኩላች› ሲል÷ ‹እንዲህ አደረግኳችሁ› እንደማለት፣ ‹እንዲህ አደረጓችሁ› ሲል ደግሞ ‹እንዲህ አደረጉላችሁ›ያለ ይመስል በተቃኒው ይተረጎምበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ነገርን ጠምዝዞ የመተርጎም ልምድ ያፈራው ከኢሕአዴግ ቴሌቪዥን(ኢቴቪ) ወዲህ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ አንድምታ ከጠሉት መንግስት እውነት የራስ ውሸት ይሻላል የሚል ነው፡፡

መደምደሚያ፡- የኢትዮጵያመንግስት ተጠልቷል፡፡ በርግጥ ይህንን መንግስት እያወቀ ችላ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት ነው፣ ምናልባትም ደግሞ መንግስትምየኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚጠላው የተለየ ነገር አይጠብቅ ይሆናል፣ ምናልባትም ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ጥሩ ነገር ተሳክቶልኝ ሰርቼእክሳቸዋለሁ ብሎ አስቦ ይሆናል፡፡ የመንግስት ፍላጎት ምንም ቢሆን ምን የሕዝቡ ጥላቻ ግን የሚያመለክተው ለውጥ እየፈለገ እንዳጣብቻ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment