Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, April 25, 2012

ዛሬም ሰው እየተቃጠለ ነው

አቤ ቶኪቻው

በዛ ሰሞን ዳውሮ ወረዳ ተርጫ ውስጥ የኔ ሰው ገብሬ የተባለ መመህር ራሱን አቃጠለ። ሞተም። መንግስትም አለ አይምሮው የተቃወሰ ሰው ነው። 

አይምሮ ያላቸውም ጠየቁ “አዕምሮውን ማን አቃወሰው?” መንግስትም መልስ አልነበረውምና ዝም አለ…! “ራሳቸው እያስለቀሱ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ያቋቁማሉ” የለው ማን ነበር? ከየኔሰው ገብሬ በኋላም ሆነ በፊት በርካታ መምህራን በመንግስት የተጠናገረ አስተዳደር የተነሳ ሲቃጠሉ ውለው ሲቃጠሉ እንደሚያድሩ ሰምተናል።

 ምን መምህራን ብቻ የሀይማኖት ሰዎች ነጋዴዎች ፖለቲከኞች ጋዜጠኞችም እየነደዱ ነው። እንግዲህ የሚቃጠል በሙሉ የአዕምሮ ህመምተኛ ከሆነ ጤነኛ ሰው ያለው በቤተመንግስት ብቻ ነው። ነገር ግን ሀገር ሁሉ እየተቃጠለ ያቺ የግንብ አጥር ከቃጠሎው ታድን ይሆን? ብለን የጠየቅን እንደሆነ መልሱ እንጃ ነው… እንጃ አይመስለኝም።፡ 

ከሁለት ወር በፊት በሰማሁት የጨረፍታ ዜና ደግሞ ጎንደር አካባቢ አንድ ግለሰብ ራሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ እሳት ለኩሷል። የአካባቢው ሰዎች እሳቱን ተረባርበው ካጠፉለት በኋላ በጎንደር ሆስፒታል የገባው ይህ ሰው በምን ሁኔተ ላይ እንዳለ ማወቅ አልተቻለም። (ጉድ እኮ ነው ብለው እየተገረሙ ይከተሉኝ…)

ትላንት ምሽትም አዲሳባ ውስጥ ሊያውም  ፒያሳ ዳዊት የተባለ የሰላሳ አመት ወጣት ራሱን አቃጥሏል።  ወጣቱ በአሁኑ ሰዓት የካቲት 12 ሆስፒታል ይገኛል። በህይወቱ ላይ ስለደረሰው ነገር ዝርዝር ገና አልሰማንም።
ይደረስ ለመንግስት ሰዎች
 ሀገሬው በሙሉ እየተቃጠለ እየተንጨረጨረ ነው። ሰው ሲቃጠል የአዕምሮ ህመምተኛ ነው ብሎ መልስ መስጠት ከእሳቱ ወላፈን ከጭሱም መታፈን አያድንም። የመዳን ቀን ዛሬ ነው እና ዛሬውኑ እባካችሁ ንስሃ ግቡ።

በመጨረሻም 1

በእሳቱ ለተቃጠለው ወዳጃችን ምህረትን ይላክ የሞቱትንም ነብስ ይማርልን!

No comments:

Post a Comment