Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Sunday, April 22, 2012

ኢቲቪ በአኪልዳማ ድራማ የተነሳ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው (አሉ).

 By Abetokichaw
ሰሞኑን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከነ አንዷለም አራጌ ጋር በተያያዘ ባወጣው ዘገባ ምክንያት አቃቤ ህግ “በፍርድ ሂደቱ ላያ ጣልቃ ገብተሀል” በሚል ፍርድ ቤት እንዳቀረበው ይታወሳል። (በቅርቡ አይደል እንዴ… እንዴት ይረሳል…? ብለው ይከተሉኝ) ያንን ወሬ ባቀበልኩዎ ግዜ ከዚህ በፊት ኢቲቪ አካልዳማ የተባለውን “ፊልም” ሲያቀርብ  አቶ አንዷለም አራጌ “ኢቲቪ በፍርድ ሂደቱ ጣልቃ ገብቷል” ብለው ቢከሱ የሚሰማቸው እንዳላገኙ አውርተን ነበር።

  በነገራችን ላይ አቶ አንዷለም በወቅቱ የኢቲቪን አኪልዳማ በከሰሱ  በነጋታው ፊልሙ በህዝብ ጥያቄ ተብሎ ተደግሟል። (በወቅቱ እኔም በሆዴ በብሽሽቅ እኮ መንግስቴን የሚችለው የለም። ብዬ አድንቄ ነበር።) ትላንት ማታ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዳወራው ደግሞ የአኪልዳማ አዘጋጅ ጋዜጠኛ እና ኢቲቪ፤ አንድነት ፓርቲ በከሰሳቸው መሰረት ሚያዝያ 24/2004 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሆነ ነግሮናል።

 ዜናው በዚህ አበቃ ቀጥሎ የኔ አስተያየት ይቀርባል። አዲስ መስመር ላይ እንገናኝ…እኔ የምለው ወዳጄ ፍርድ ቤቱ በኮመዲያኖች ቁጥጥር ስር ውሏል እንዴ? ብዬ ልጠይቅ ነበር አጓጉል መዳፈር ይሆንብኛል ብዬ ትቼዋለሁ። ነገር ግን፤ አቶ አንዷለም አራጌ በአኪልዳማ ላይ አቤቱታ ካቀረቡ ስንት ግዜያቸው? ያኔ እርሰቸው አቤቱታውን ሲያቀርቡ የተሰጣቸው ምላሽ ወደር የለሽ ድብደባ እና “ምን ታመጣለህ!” በሚመስል መልኩ ፊልሙን ደጋግሞ ማሳየት ነበር።በዚህ የተነሳ በርካቶች “የተከበረውን ፍርድ ቤት” የተቀበረ ብለውታል ምን እርሱ ብቻ ብዙ ምድራዊ ስድቦችን እና ርግማኖችንም አውርደውበታል።

ታድያ ዛሬ እነ ተመስገን ፍርድ ቤት በቀረቡ በነጋታው ኢቲቪም ተጠራ። ከዚህ ምን አንደምጠረጥር ልናገርማ…ኢቲቪ ያደረገው ስህተት ፍርድ ቤቱ አላጣውም… ታድያ ያኔውኑ አቶ አንዷለም እንደከሰሱት ችሎት ላይ ሊያቆመው ፈልጎ ነበር። ነገር ግን ፍርድ ከላይ ነውና “እነ ፍትህ ካልቀረቡ ኢቲቪም አይቀርብም ሲሉ የበላዮቹ አዘዙ… (መጠርጠር መብቴ ነው) ታድያ እነ ፍትህ ጋዜጣ  በምን ስህተት ፍርድ ቤት ይቅረቡ? ሲፈለግ ሲፈለግ ይሄንን ያህል ግዜ ወሰደ። አሁን ገና በአቃቤ ህጉ አይን ፍትህ ጋዜጣ ላይ ስህተት የሚመስል ነገር ተገኘ።

 ከዛስ… ከዛማ በል ኢቲቪ አሁን አንተም ና… ተባለ።  ይሄ ልጅነቴን አስታውሰኛል…ልብስህን ቀይር…. እርሱ ካልቀየረ አልቀይርም።ትምህርት ቤት ሂድ … እርሱ ካልሄደ አልሄድም።ፍርድ ቤት ቅረቡ እነሱ ካልቀረቡ አንቀርብም….! (አይ ጉልቤ መሆን ደጉ) እኔ ደንቆኛል… እርስዎስ…?

No comments:

Post a Comment