Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, April 25, 2012

ተቃውሞ ለማድረግ የሞከሩ የስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፖሊስ ተበተኑ

ኢሳት ዜና:-
በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ጊዮርጊስ አደባባይ እራሱን በቤንዚን ያቃጠለው ጎልማሳ ሁኔታና ምክንያት ይጣራ ሲሉ የጠየቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስድስት ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች በፖሊስ ተበትነዋል፡፡

የተወሰኑ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችም ተጎጂው በትላንትናው እለት ለህክምና ተኝቶበታል በተባለው የካቲት 12 ሆስፒታል ተሰብስበው ለመግባት ያደረጉት ሙከራም በፖሊስ ተበትኗል ። ዘጋቢያችን በዛሬው እለት ለማጣራት እንደሞከረው እራሱን ያቃጠለው ግለሰብ የ1998 ዓ.ም ቅጥር የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲሆን ለፍትህና ለርትዕ በሚያደርገው ውስጣዊ ትግል በአሻጥር ከፖሊስ ሠራዊቱ የተበተነ ነው ሲሉ ለግለሰቡ ቅርበት አለን ያሉ ሰዎች ገልጸዋል፡፡

አሁንም ቢሆን በየካቲት 12 ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገለት ነው ያሉን ምንጮች መርማሪ ፖሊስ ቃሉን እንደተቀበለውና የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድርጅት /ኢቲቪ/ ሰውየውን ሆስፒታል ክፍሉ ገብቶ መቅረጹንና ነርሶቹ የህክምና ባለሙያዎችና ነርሶች በኢቲቪ ለመቀረጽ ባለመፍቀዳቸው እንክብካቤ ሲያደርጉለት እጃቸው ብቻ እየታየ ተቀርጸዋል ፡፡

ግለሰቡ የፖሊስ አባል እንደነበር ከታወቀ በኋላ የፌዴራል ፖሊስና የደህንነት ሠራተኞች ቁጥጥርና ጓደኞቹን የማዋከብና ምንም እንዳይተነፍሱ ለማድረግ እየሞከሩ እንደሆነ አንድ እማኝ ለዘጋቢያችን ገልጾአል፡፡ በትላንትናው እለትም ግለሰቡን የሚያውቁ የአዲስ አበባ ፖሊሶች ለተሻለ ህክምና ገንዘብ ማዋጣት መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

መምህር የኔሰው ገብሬ ራሱን በእሳት አቃጥሎ ከገደለ በሁዋላ፣ ተመሳሳይ ድርጊቶች ተፈጽመዋል። በደብረማርቆስ ከተማ አንድ የትግራይ ተወላጅ ራሱን ማቃጠሉ ይታወቃል። በ ደቡብ ክልል በርካታ አርሶ አደሮች ራሳቸውን ገደል ውስጥ እየወረወሩ አጥፍተዋል። ብዙዎች እንደሚሉት በአገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት ወጣቶች ተስፋ እንዲቆርጡ እና በራሳቸው ላይ እርምጃ እንዲወስዱ እያደረጋቸው ነው።

No comments:

Post a Comment