Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, October 23, 2012

የሙስሊሞች ተቃዉሞና የፖሊሶች ግድያ

 Die Gambia Street und Churchill Avenue führen schnurgerade auf das Rathaus der äthiopischen Hauptstadt Addis Abeba. Aufnahme vom Januar 2007. Foto: Peter Smolka +++(c) dpa - Report+++
Addis Ababa

በግጭቱ ከተገደሉት አንዱ ፖሊስ መሆኑን አቶ ሽመልስ አስታዉቀዋል።በስልክ ያነጋግርናቸዉ የአይን ምስክሮች እንደሚሉት ግን ግጭቱ የተፈጠረዉ ገርባ መስጊድና አካባቢዉ ነዉ። ሁለቱን አነጋግረናል። 

ኢትዮጵያን የተመለከተ ውይይት በበርሊን

Sibhat Nega
ከኢትዮጵያ፡ ከኬንያ እና ከማሊ የተጋበዙ እንግዶች በበርሊን የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቶች ፓርቲ፡ ኤስ ፔ ዴ በየወሩ በጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት፡ ቡንድስታግ በሚያዘጋጀው እና ባለፈው ዓርብ በተካሄደው የአፍሪቃ ከበብ ውይይት ላይ ተገኝተው ነበር።

Sunday, October 21, 2012

ጉዞ ኃይለ ማርያም - ከአረካ እስከ አራት ኪሎ

በዮናስ አብይ
ጉዞ ኃይለ ማርያም - ከአረካ እስከ አራት ኪሎ
Prime Minister Hailemariam Desalegn
የ43 ዓመቱ ጐልማሳ መንገሻ መንዳዶ የተወለደባትንና አድጐ የተማረባትን አነስተኛዋን የአረካ ከተማን ለቆ መኖርያውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካደረገ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ዛሬ የሥራ ጠባዩ በፈጠረለት አጋጣሚ ሙሉ ጊዜውንና ኑሮውን በአርባ ምንጭ ላይ በመመሥረቱ አልፎ አልፎ በአዕምሮው ውልብ ከሚሉበት ትዝታዎች በስተቀር ስለተወለደባት የአረካ ከተማ ሲያወሳ አይሰማም፡፡ 

ነገር ግን ስለተወለደባት ከተማ ከማይረሳቸው የልጅነት ትውስታዎቹ ውስጥ አንድ አስገራሚ ታሪክን ከተማሪነት ዘመኑ መዝዞ በፈገግታና ኩራት በተሞላበት ሁኔታ ሲያወጋ፣ ያድማጭን ጆሮ በጉጉት ሊያቆም እንደሚችል በቅድሚያ ከገጽታው ደማቅነት መረዳት ይቻላል፡፡ የታሪኩ ክስተት ወደኋላ 28 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ 300 ኪሎ ሜትር በምትርቀው በአረካ ከተማና በነዋሪዎቿ ታላቅ የመደነቅ ስሜትን ስለፈጠረ  የአንድ ጎበዝ ተማሪን አስደናቂ ጉዳይ ያወሳል፡፡

Friday, October 19, 2012

ቂል የያዘው ሰይፍ

(ፕሮፌሰር መስፍን):-
Sibhat Nega
በቅርቡ አቶ ስብሐት በአደረገው ቃለ መጠይቅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመው ወያኔ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማርኛ ተናጋሪዎችና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር ብሎአል፤ ልብ ላለው አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው  ነው፤ ከፊት ለፊት የተሰነዘረው አማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኙን ለመምተር ነው፤ ቂል የሚያደርገው አማራ የሚባል ጎሣ ቢኖርም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአማርኛ ተናጋሪዎች ታጥሮ ትግሬንና ኦሮሞን፣ ወላይታንና ጉራጌን፣ ሌሎችንም የማይነካ መስሎት ከባድ ስሕትት ላይ መውደቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ እሱን የሚያህል ሰው የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ አለማወቁ ያሳዝናል፡፡

የቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ዕውቅና እንዲያገኝ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ



የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት መንፈሳዊ ጉዳዮችን የምትከታተልበት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱንና ለተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያለው ግንኙነትና እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል ረቂቅ ሕጉ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ 
 
በትናንትናው ዕለት የተጀመረውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ 31ኛ መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ የቤተክህነቱ የሕዝብ ግንኙነት መምርያ ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ፣ ‹‹ቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አላት፡፡ መንፈሳዊ ቦታ በመሆኗ ግን እስር ቤት የላትም፡፡ ፖሊስም የላትም፡፡ ፍርድ ቤቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው መንፈሳዊ ተግባራትን ነው፤›› ብለው፣ የተጋጩ ሰዎችን በእርቅና በስምምነት እንዲፈቱ ማድረግ ነው፣ ከመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ውጭ የሆነ ጉዳይ ካጋጠመ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከመሀይምነት ባልተላቀቁ ሰዎች ብዛት ከዓለማችን ሶስተኛ ናት ተባለ

Ethiopia

ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ)፤ ከመሀይምነት የተላቀቁ ሰዎች ብዛትን በተመለከተ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ኢትዮጵያ ከዓለማችን በርካታ አገራት ከመጨረሻ ሶስተኛ መሆኗን ይፋ አደረገ።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ከሶስተኛ አለም አገራት ውስጥ አጥንቶ ይፋ ባደረገው በዚህ ጥናት፤ በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ፤ 28 በመቶው ብቻ ፊደል የቆጠሩና መጻፍና ማንበብ የሚችሉ ናቸው ብሎ፤ ከዓለም አገራት መጨረሻ ከተቀመጡት ከማሊና ደቡብ ሱዳን ቀጥሎ፤ ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሶስተኛ ናት ብሏል።

በዚህ ጥናት መሰረት፤ ህዝቦቻቸውን በበቂ ሁኔታ በማስተማር ከህዝብ ቁጥራቸው 99.9 በመቶ በማስተማር ኩባ አንደኛ፤ ህንድ 74.1 በመቶ የተማረ ህዝብ በመያዝ 2ኛ ስትሆን፤ በኢትዮጵያ 28 ከመቶ ብቻ ከአጠቃላዩ ህዝብ ውስጥ ከመሀይምነት የተላቀቀ ነው። ኢትዮጵያ ከ184 አገራት ውስጥ 182ኛ ሆና ነው በ3ኛ ደረጃ የተፈረጀችው።

በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል

ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት  በወለደች በማግስቱ  ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።

Saturday, October 13, 2012

ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ባህር ዳር ላይ የጀምረውት የነበረው የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ ተቋረጠ

Radio station

መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በቆየባቸዉ አመታት ያከናውናቸው የነበሩት በርካታ ጉዳዮችን ለፓርቲውም ሆነ ለሚንስትሮች ምክር ቤትም ወይም ለይስሙላ ፓርላማ እንደማያሳውቅ ምንጮች አጋለጡ::ምንጭ አክሱማዊት በፌስቡክ እንዳወረሰችን


ኢትዮጵያ አገራችንን ለ21 አመታት የገዛው ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ ትላልቅ ውሳኔዎችን በዙሪያው ላሰባሰባቸው የካቢኔ ምንስትሮችም ሆነ ለፓርላማው ሳያሳውቅ በራሱ ፈቃድ ብቻ ያስተላልፍና ያስፈጽም እንደነበረ ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ ከነበሩ ሚንስተሮች የተገኘ መረጃ አጋለጠ።

መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት ለማንም ሳያማክር በግል ሥልጣኑ አስጀምሮት ከነበሩ ፕሮጄክቶች አንዱ ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ይሰጥ የነበረው የፋይናንስና የማቴሪያል እርዳታ እንደነበረ የገለጹ ምንጮች የርሱን መሞት ተከትሎ ተቃዋሚዎቹ ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው ገልጸዋል።

በጋምቤላ የሚንቀሳቀሰው የናይሎቲክ ህዝቦች ንቅናቄ፤ ሰሞኑን ከኢትዮጲያ መንግስት ወታደሮች ጋር መጋጨቱ ተገለጸ

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ተባባሪ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አግዋ ጊሎ፤ የጋምቤላ ምንጮችን በመጥቀስ እንዳመለከተው፤ በቅርቡ በተካሔደው ግጭት አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሲገደል፤ ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል።

Sunday, October 7, 2012

ከፖለቲካ ፍጥጫው በስተጀርባ (ከእየሩሳሌም አርአያ)

Journalist Araya
በገዢው ሰፈር ጎራ ለይቶ ከተለኮሰው የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ ጀርባ አገር እና ህዝብን የሚጎዳ አደገኛ ተግባር በግልጽ እና በስውር እየተካሄደ እንዳለ ከተለያዩ የፓርቲው ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

በተለይ በብአዴን እና በህወሃት ቱባ አመራሮች መካከል ስር ሰዶ የቆየው እና የአቶ መለስን ህልፈት ተከትሎ ያገረሸው የውስጥ ሽኩቻ ሁለት ቡድኖች የሃይል አሰላለፋቸውን ለማጠናከር«ይረዱናል » የሚሏቸውን የሌሎች ፓርቲ ሹማምንት እና የመከላከያ የጦር አዛዦች ከጎን የማሰለፉን ተግባር ቀጥለውበታል።ለግንዛቤ እንዲረዳ የሃይል አሰላለፉን በጥቂቱ በመዳሰስ ወደ ዋናው ነጥብ እናምራ ።

ከበረከት እና ዓዜብ ጎን በመሰለፍ ቀዳሚ የሆኑት አቶ ተፈራ ዋልዋ እና አዲሱ ለገሰ ናቸው።አቶ አዲሱ በይፋ ከሚታወቀው የአየር መንገድ የቦርድ ሃላፊነታቸው ባሻገር ኮተቤ መስመር በሚገኘው እና «የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ማኔጅመንት ት/ቤት »ተብሎ በተከፈተው ተቋም ዋና ሃላፊ እና ለባለስልጣናት እንዲሁም ካድሬዎች መምህር ጭምር ናቸው ። ከመለስ መታመም ወዲህ የህወሃት ካድሬ ላልሆኑ በአቶ አዲሱ እየተሰጠ ያለው ፖለቲካዊ ትምህርት ሳይሆን የበረከትን አቋም የሚያቀነቅን እና ህወሃትን የሚያጥላላ ቅስቀሳ ሆኖአል ።