ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት በወለደች በማግስቱ ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።
ኢትዮጵያዊቷ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በዱባይ ፖሊስ የታሰረችው፤ ከጋብቻ ውጪ በመውለድ የ አገሩን ህግ ጥሳለች ተብላ ነው። ኢትዮጵያዊቷ ሴት ልጇን የወለደችው ከባንግላዴሸዻዊ ሾፌር ጓደኛዋ ነው። ጓደኛዋም ከጋብቻ ውጪ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት በመፈፀም ወንጀል ተከሶ በ እስር እንደሚገኝ< አመልክቷል። የ አንድ ቀን አራሷ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሠራተኛ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ሁለት እግሮቿ በሰንሰለት በመታሰራቸው፤ ህፃን ልጇን ሜሪያምን ማቀፍ ተስኗት መታየቷን ድረ-ገጹ አስነብቧል።
ኢትዮጵያዊቷ እናት ለፍርድ ቤት በሰጠችው ቃልም ከእስር ከተለቀቀች ከህፃኗ ጋር ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ተናግሯለች። የወህኒዎቹ ሃላፊዎች ግን አራሷ ኢትዮጵያዊት ከወህኒ የምትወጣው የ እስር ጊዜዋን ከጨረሰች በሁዋላ እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ህፃን ልጇን ይዛ መሄድ ትችላለች?ወይስ አትችልም? የሚለው ጉዳይም ለወደፊት በ ህግ የሚታይ መሆኑን ነው የገለፁት። ወደ
መካከለኛው ምስራቅና አረብ አገራት በሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እጅግ አሳዛኝና
አስደንጋጭ ደረጃ በደረሰበት ሰ ዓት የ ኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ለመታደግ ምንም እንቅስቃሴ ሲያደርግ አመታዬቱ፤
ብዙዎችን ካሳዘነ ውሎ አድሯል።
No comments:
Post a Comment