ኢሳት ዜና:-የኢሳት ተባባሪ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አግዋ ጊሎ፤ የጋምቤላ ምንጮችን በመጥቀስ እንዳመለከተው፤ በቅርቡ በተካሔደው ግጭት አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሲገደል፤ ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል።
የጋምቤላ
መንግስት በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፤ በአካባቢው የሚገኙትን ጸረሰላም ሀይሎች አስወግጃለሁ ቢልም፤ በጋምቤላ ያለው
አለመረጋጋት መቀጠሉንና፤ ከ5 ወራት በፊት የተሾሙ ባለስልጣናትን በመሻር፤ አንዳዶቹን እያሰሯቸው መሆኑ ተመልክቷል።
ከወራት በፊት ልጃቸው በመከላከያ ሰራዊት የተገደለባቸው የዲማ ወረዳ ሊቀመንበር በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና መታሰራቸውን ከአጉዋ ጊሎ ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።
የክልሉ
ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ እሬሶ እንደተሰወሩ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፤ የክልሉ የፍትህ ቢሮ ሃላፊና የፖሊስ አዛዡ
ከሃላፊነታቸው እንደተነሱም ለማወቅ ተችሏል።
በጋምቤላ ክልል የሚኖሩ አርሶ አደሮችም ለሽምቅ ተዋጊዎቹ ስንቅ
ታቀብላላችሁ በሚል ሠበብ እየተዋከቡ መሆኑንም የጋምቤላ ምንጮችን በመጥቀስ ጋዜጠኛ አግዋ ጊሎ አብራርቷል።
No comments:
Post a Comment