Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, August 3, 2012

በሞያሌ ከተማ ውስጥ ውጊያ ተካሄደ

 -ሞያሌ የሚገኘው የጦር ካምፕ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል
ከኬኒያ ጋር በድንበር ከተማነትና በደረቅ ወደብነት በማገልገል ላይ በምትገኘውና በኦሮሚያና በሱማሌ ክልላዊ መንግስት በጋራ በምትተዳደረው ሞያሌ ከተማ ሐምሌ 20 ቀን 2004 ዓ.ም ውጊያ መከናወኑን ከሥፍራው ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት የአደጋውን መጠን በትክክል ለመግለጽ ቢቸገሩም ከ20 በላይ የሰው ህይወት መጥፋቱን እና በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ እንደነበር አስታውቀዋል ፡፡

Wednesday, August 1, 2012

በረከት ስምኦን “መለስ አልሞተም” አለ! ሙክታር ከድር የመለስን ቦታ ሸፍኖ እየሰራ መሆኑ ታወቀ!!

ኢ.ኤም.ኤፍ (ልዩ ዘገባ) – በአሁኑ ወቅት የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ከህክምና አገግሞ ለስራ ባለመብቃቱ፤ በሬዲዮ ፋና በኩል… “ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሞተ ማን ተክቶ ይሰራል?” በሚል ርዕስ ሰፊ ውይይት ተደርጎ ነበር።

 በዚህም ውይይት ወቅት የህግ ሰዎች “በምትኩ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተክቶት ይሰራል” የሚል ትንታኔ ሰጥተዋል። ይህ እንግዲህ በኢህአዴግ ሬዲዮ ፋና በኩል የተደመጠ ነው። በተግባር ግን አሁን የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ ስራ እየሰራ የሚገኘው የቀድሞው የኦሮሚያ ምክትል ፕሬዘዳንት የነበረው፣ ሙክታር ከድር መሆኑ ታውቋል። 

በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ እየተካሄደ ነው

(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/ 2012)፦ በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለ ወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ ነው። 
የመድረክ አባል ድርጅቶች የሆኑ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ኮንግረስ እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ በብዙዎች ሲጠበቅ የነበረዉን የፓርቲዎቻቸዉን ዉህደት፣ አመራሮቻቸዉ ባደረጉት ስብሰባ አጸደቁ።

የውጭ ጉዳይ ዜናዎች

 Source:ecadforum news
በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012)
  • አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!
  • አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን ወደ ጣሊያን አሸሸ!
  • አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው እንዲመለሱ ታዘዙ!
  • መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው!
አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!

Tuesday, July 31, 2012

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ


  • ከአብረንታንት እና ማይ ለበጣ ሁለት መነኰሳት ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋል፤ በዶንዶሮቃ ከ50 በላይ የመነኰሳት እና መነኰሳዪያት ቤት በፖሊስ ተፈትሿል
  • ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
  • የአብረንታንቱ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ እንደታሰሩ ናቸው
  • ከ49 ያላነሱ የቤተ ሚናስ መነኰሳት በፖሊስ ይፈለጋሉ
  • ‹‹እናንት ምታታሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎች ናችሁ›› /የማይ ፀብሪ ፖሊሶች/

Monday, July 30, 2012

የህወሃት አባላት ስብሰባ እንዲጠራ እየጠየቁ ነው!

ልዩ ግምገማ)
ኢ.ኤም.ኤፍ – ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ህመም በኋላ ከህወሃት አካባቢ መልካም ወሬ አይሰማም። በውጭ ሲታይ አሁንም የጠነከሩ ቢመስሉም ውስጥ ውስጡን ግን መጎሻሸማቸው አልቀረም። በተለይም የህወሃት (ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ) ሊቀ መንበር የነበረው መለስ ዜናዊ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተሽሎት ወደ ስራ እንደማይመለስ በመገለጹ፤ ከሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ይልቅ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራላቸው ለጽ/ቤቱ ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል። 

Sunday, July 29, 2012

VOA: Prof. Alemayehu G Mariam on Meles Zenawi and Power Succession Rights

Constitution guarantees no right for power succession: prof. Al Mariam

Professor Alemayehu Gebre Mariam tells Tizita Belachew of VOA that the Ethiopian consitution doesn't guarantee the transfer of power in the event of the death of the prime minister. He said in fact the deputy prime minister, who is expected to automatically replace the deceased pm, is only accountable to the PM, and doesn't have any clearcut succession rights.

የወያኔዎች አይረሴ አባባሎች (Highlights)

በተሻለ መንግሥቱ

1. “ኤርትራ ከየት ወዴት” –
የኢትዮጵያዊው መለስ ዜናዊ መጽሐፍ ፡፡ ስለ‹እናት ሀገሩ› ኢትዮጵያ አንድም አንቀጽ አለመጻፉን ልብ ይሏል፡፡
2. “በእናንተ ወገብ ላይ ያለው ቁስል በእኔም ወገብ ላይ አለ፡፡” መለስ ዜናዊ እነ ንጉሤ አስገልጠውን የመሰሉ ሆዳም አማሮችን አሥመራ ላይ አስጎንብሶ ሻዕቢያን ይቅርታ ባስጠየቀበት ዘመን በትግርኛ ተናግሮት ወዳማርኛ ከተመለሰው፡፡
3. “የአማራ ተረትና የሶማሌ በጀት ነው ያስቸገረን፡፡” መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የተናገረው፡፡

Saturday, July 28, 2012

ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አሁንም ከማገገሚያ ክፍል እንዳልወጣ ምንጮች ገለጹ

 ግንቦት ሰባት ዜና፣, Source: www.ecadforum.com
ቤልጂዬም ብራስል በሚገኘው የሴይንት ሉክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቁ ሰዎች የመተንፈሻና የፈሳሽ ምግብ ቱቦዎ ተገጥሞላቸው በሚተኙበት የሪከቨሪ ሩም እየተባለ በሚጠራው የህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ ከሆስፒታል ምንጮች ያገኘነው መረጃ አረጋገጠ።

መለስ ዜናዊ እራሱን ስቶ በቻርተር አውሮፕላን ወደ ቤልጂዬም ከተላከ ወዲህ ላለፉት 3 ሳምንታት እራሱን መቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹ ምንጮች ከአሁን አሁን ይሞታል ተብሎ ሲጠበቅ ነፍሱ መለስ እንደሚልና ተሽሎታል ተብሎ ሲታሰብ ደግሞ ወዲያውኑ መልሶ እንደሚወስደው አረጋግጠዋል።