ግንቦት ሰባት ዜና፣, Source: www.ecadforum.com
ቤልጂዬም ብራስል በሚገኘው የሴይንት ሉክ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ህይወታቸው አደጋ ላይ የወደቁ ሰዎች የመተንፈሻና የፈሳሽ ምግብ ቱቦዎ ተገጥሞላቸው በሚተኙበት የሪከቨሪ ሩም እየተባለ በሚጠራው የህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ ከሆስፒታል ምንጮች ያገኘነው መረጃ አረጋገጠ።
መለስ ዜናዊ እራሱን ስቶ በቻርተር አውሮፕላን ወደ ቤልጂዬም ከተላከ ወዲህ ላለፉት 3 ሳምንታት እራሱን
መቆጣጠር በማይችልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጹ ምንጮች ከአሁን አሁን ይሞታል ተብሎ ሲጠበቅ ነፍሱ መለስ
እንደሚልና ተሽሎታል ተብሎ ሲታሰብ ደግሞ ወዲያውኑ መልሶ እንደሚወስደው አረጋግጠዋል።
የመለስ ዜናዊን ህመም በቅርበት ሆኖ እያስታመመ ያለው የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዴታ ተብሎ ለሃይለማሪያም ደሳለኝ
በታኮነት ከመመደቡ በፊት በዩናይትድ ስቴትስና በቤልጂዬም የወያኔ አምባሳደር በመሆን ለ19 አመት ያገለገለው ብርሃኔ
ገብረክርስቶስ መሆኑ ተረጋግጧል።
የግንቦት 7 መረጃና ክትትል ጓዶች ባካሄዱት ስውር ክትትል ብርሃኔ ገብረክርስቶስ ዘወትር ጠዋት በአንድ
አፍሪካዊ በሚሽከረከር የኮር ዲፕሎማቲክ መኪና መለስ ዜናዊ ብራሰልስ ውስጥ ወደተኛበት ሆስፒታል እንደሚመላለስ
ለማረጋገጥ ተችሏል። መለስ ዜናዊ ሆስፒታል ከገባበት ቀን ጀምሮ ብርሃኔ ገብረክርስቶስ ለአንድም ቀን በአስታማሚነት
ከጎኑ ተለይቶ እንደማያውቅ ተደርሶበታል።
በአንጻሩ የመለስ ዜናዊ ባለቤት አዜብ መስፍን የብርሃኔ ገብረክርስቶስን
ግማሽ ካባለቤቷ ጋር ለመቆየት አለመፈለጓ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉትን ሁሉ ያስገረመ ሆኖአል ተብሎአል።
ይህ በዚህ እዳለ በወያኔ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ሚዲያዎቻና አፍቃሪዎቻቸው አለቃቸው መለስ ዜናዊ በዕረፍት ላይ
እንደሆነ አስመስለው የሚያሰራጩትን ዜና አጠናክረው እንደቀጠሉበት ለማወቅ ተችሎአል።
በትናንትናው ዕለት የታተመው
ሪፖርተር ጋዜጣ “ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ከሐኪሞቻቸው ባገኙት ምክር መሠረት በውጭ አገር በዕረፍት ላይ
እንደሚገኙ ምንጮች ገለጹ” በሚል አርዕስት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለባቸው ከፍተኛ የሥራ ጫና ምክንያት ላጋጠማቸው
ሕመም ረዘም ያለ ዕረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ይህንኑ በውጭ አገር እየፈጸሙ እንደሆነ
ታውቋል፡፡” በማለት ዘግቧል።
በአንድ ወቅት ከበርከት ስምዖንና ከሼህ አላሙዲን ጋር በፈጠረው የጥቅም ግጭት እየተከታተለ ሲያጋልጣቸው
የነበረው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊ፤ የመለስ ዜናዊ ህይወት አደጋ ውስጥ መግባቱ በፈጠረበት ስጋት
የባላንጣውን የበረከት ስምዖን የውሼት መግለጫ መላልሶ በማስተጋባት አንባቢዎቹን ለማደናገር እየሞከረ መሆኑ ለመታዘብ
ተችሏል።
በውሸታቸው ብዛት በህዝብ ዘንድ ታአማንነት እንደሌላቸው የተረዱት የወያኔ ቁንጮዎችና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው እንደ
አይናቸው ብሌን የሚሳሱለት የፖለቲካ ማህንድሳቸው አየር መተንፈሻው ተዘግቶ በተገጠመለት የአየር መተንፈሻ ቱቦ ላይ
ሆኖ እያጣጣረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት አንዴ በሰላም ወደ አዲስ አበባ ተመልሶአል ሲሉ ሌላ ጊዜ ደግሞ “ ከሕመማቸው
አገግመው በቅርቡ ወደ ሥራ ገበታቸው ይመለሳሉ በማለት እርስ በርሱ የተምታታ መግለጫ እየሰጡ ነው።
የወያኔ ቁንጮዎች የተምታታ መግለጫ መሳቂያ መሳለቂያ እያደረጋቸው ባለበት ሰዓት ሪፖርተር በትናትናው ዕለት
ዘገባው “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዕረፍት ጊዜያቸውን በአሜሪካ እያሳለፉ ነው ቢባልም፣ ምንጮቻችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ
ደኅነንት ሲባል ያሉበትን አገር ከመግለጽ ተቆጥበዋል” በማለት መዘገቡ አንባቢዎቹን የአይጥ ምስክር ድንቢጥ እንዲሉ
አድርጓቸዋል።
No comments:
Post a Comment