Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, October 26, 2012

ኢቲቪ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነገረው! .....አቤ ቶክቻው

በመላው ሀገሪቱ ለአረፋ በዓል የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሟቸውን አሰሙ። ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም (ነጠላ ሰረዝ) ኮሚቴዎቻችን እና ሌሎች ንፁሐን ይፈቱ (ነጠላ ሰረዝ) ምርጫው ህገወጥ ነው (ነጣላ ሰረዝ) ግድያው ይቁም (አራት ነጥብ) እና በሌላ ነጠላ ሰረዝ ደግሞ ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን ዎችን ከቢጫ ካርድ ጋር አንግበው ለመንግስት አበርክተውለታል!
 
በተለይ ኢቲቪ በገዛ ደጃፉ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነግሮታል። ኢቲቪ በእኔ ቁጥር የመገመት ችሎታ የማይደፈሩ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጮክ ብለው ልክ ልኩን ሲነግሩት ህንፃው በሀፍረት ሽምቅቅ ብሎ አለመስመጡ እንዴት ያለ ግንበኛ ቢሰራው ነው ብለን እንድንደነቅ አድርጎናል።
 
“ኢቲቪ አሸባሪ” “ኢቲቪ ውሸት አውሪ” “ኢቲቪ የማታፍሪ” “ኢቲቪ ነሽ ደባሪ” “ኢቲቪ ወዲያ ቅሪ” ብለው መፈክር አሰምተዋል። (በቅንፍም መፈክሩን በግጥም ለማድረግ በማሰብ የራሴን የፈጠራ መፈክሮች መጠቀሜን እገልፃለሁ!) 
 
ከቅንፍ ውጪ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚለቁ ተጨማሪ ሰራተኞችን እንደምናይ እናስባለን! ከእንዲህ ያለ ተቃውሞ ጋር ያለ እንከን ከሰሩ የጤና እንከን አለ ማለት ብለንም እንጠረጥራለን! በአዲስ መስመርም መንግስት በመላው ሀገሪቱ የተሰማውን ተቃውሞ እየሰማ እንዳልሰማ ከሆነ የገዢው ፓርቲ አባላት ራሳቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ማለት ነው ብለን እናስባለን!
 
                        

No comments:

Post a Comment