Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, October 23, 2012

የህወሀቱ መስራች አቶ ስብሀት ነጋ፦”የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም” አሉ

Mr. Sibhat Nega
ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት ይህን ያሉት   <የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከ አቶ መለስ ሞት በሁዋላ ምን ለውጥ ይኖረዋል?>በሚል ርዕስ ከጀርመን  ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። በበርሊን በተደረገውና ኢትዮጵያ፤ኬንያ እና ማላዊ ላይ ባነጣጠረው በዚሁ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ መለስ ቢሞቱም ፖሊሲን በተመለከተ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይኖር ተናግረዋል።

<<መለስ አንድ ሰው ነው፤በ አንድ ሰው ሞት የድርጅቱ ዓላማ አይቀየርም፤ስለዚህ በ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል የፖሊሲ ለውጥ አይኖርም” ነው ያሉት አቶ ስብሀት። መንግስታቸው የደርግ ተከታዮችንና የፊውዳል ርዝራዦችን ለመቆጣጠር ብዙ ዓመታት እንደሠራ የጠቀሱት አቶ ስብሀት፤<<በደርግ የተበላሸውን የ ኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተማር ብዙ ጊዜ አጥፍተናል>ብለዋል።

ንግራቸውንም የዘጉት፦<የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም>> በማለት ነው። መድረኩ ለውይይት ክፍት መሆኑን ተከትሎ በስፍራው የተገኙት ኢትዮጵያውያን በ አቶ ስብሀት ላይ ጠንካራ የተቃውሞ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰንዝረዋል።

በተለይ አንድ ተናጋሪ፦<<የኢትዮጵያ ህዝብ ሥርዓት ያለው ሕዝብ ነው። ከላይ ሆናችሁ በቴሌቪዥንና በሚዲያዎቻችሁ ጭምር እየተሳደባችሁ ሰውን ሥነ-ስርዓት እንዳይከተል ያደረጋችገሁት እናንተ ናችሁ”ብለዋል።

<<ባለፉት ዓመታት የብዙሀንን ንጹሀን ደም በከንቱ አፍስሳችሁዋል>> በማለት  በአቶ ስብሀት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሌላው ኢት  ዮጵያዊ፦<< በኬንያ የሰው ደም ያፈሰሱት ለፍርድ እንደቀረቡ ሁሉ እናንተም ለፍርድ ልትቀርቡ ይገባል”ብለዋቸዋል።

ከዚህም ባሻገር በ 1997 ምርጫ ወቅት የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ፎቶግራፎች በመያዝ ወደ ስብሰባው የመጡ ኢትዮጵያውያን፤ ሟቾቹን ፎቶዎች ለጀርመኑ የምክር ቤት አባላትና ለስብሰባው ታዳሚዎች በማሳየት አቶ ስብሀትና መንግስታቸው በደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች መሆናቸውን አሳይተዋል።

ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያንም በስብሰባው በመገኘት በአቶ ስብሀት ላይ ተቃውሟቸውን ሰንዝረዋል። በስተመጨረሻም ስብሰባውን ሲመሩ ከነበሩት ጀርመናውያን አንዷ፡- ከ ኢትዮጵያ ተወካይ ጋር መወያዬት ያስፈለገው ከ አቶ መለስ በሁዋላ ምን ዓይነት ለውጥ ይኖራል?በሚለው አጀንዳ ላይ እንደነበር፤ሆኖም ምንም ለውጥ እንደማይኖር መነገሩን በመጥቀስ የኢትዮጵያን አጀንዳ እንደዘጉት የደቸ-ቨለ ሪፖርት ያስረዳል።

አቶ መለስ መሞታቸውን ተከትሎ ወደ መድረክ መውጣት ጀመሩት አቶ ስብሀት በቅርቡ ከ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ስለ ጥምር መንግስት ባላቸው ሀሳብ ጉዳይ ለቀረበላቸው ጥያቄ፦<እነዚህ ጥምር መንግስት የሚሉ ተቃዋሚዎች በህጋዊነት መቀጠል አለባቸው?ወይስ የለባቸውም?”በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከምርጫ ቦርድ ጋር እነጋገርበታለሁ”ማለታቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment