Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, August 29, 2012

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በልዩ ትእዛዝ ተፈታ::

ኢሳት ዜና:- ማክሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2004 ዓ.ም፡- የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍትህ ሚኒስትር ፕሬዝዳንት ልዩ ትዕዛዝ በፌዴራል ዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ተቋርጦ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲፈታ በተወሰነው መሰረት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተፈትቷል።

ምንጮቻችን እንደገለጹልን በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ተኛ ወንጀል ችሎት በዐቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ የጋዜጠኛውን የዋስትና መብት የማያስነፍገው ሆኖ ሳለ ዐቃቤ ህግ በማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን ይከራከርልኝ ስላለ ብቻ የችሎቱ ዳኛ ማጽደቃቸው እና የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መታሰር፣ እንዲሁም በዕለቱ ችሎት የገዢው ፓርቲ ደጋፊ የሆነው የኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ባለቤት ሳምሶም ማሞ እና የትዳር አጋሩ የተከሰሱበት የንግድ ፈቃድ ሳያድሱ የመስራት ወንጀል በፍትህ ሚንስትር ዲኤታ ውሳኔ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ መሰናበቱ የፍትህ ሥርዓቱን በሀገር ዓቀፍና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ያጋለጠና ያሳጣ ጉዳይ ሆኖ በመንግሥት ላይ ኪሳራ አምጥቷል፡፡


ሃሙስ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ክሱን ለመከላከል ሄዶ በዚያው የዋስትና መብቱ ተነፍጎ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የገባው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ፣ ለሁለት ቀናት በጨለማ ክፍል የታሰረ ሲሆን ከቅዳሜ ጀምሮ በቤተሰቡና በሥራ ባልደረቦቹ እንዲጎበኝ ተፈቅዶለት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ትላንት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ኃላፊ ጽ/ቤት የሥራ ባልደረቦቹ ማመልከቻ ያስገቡ ሲሆን፣  ዛሬ የውሳኔውን ግልባጭ ተቀብለው ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ለማለት ሲዘጋጁ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መዝገብ በትላንትናው ዕለት በፕሬዝዳንቱ ልዩ ትዕዛዝ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማምራቱንና በዛሬው ዕለትም ክሱ ተቋርጦ እንደሚፈታ ተነግሯቸው ነበር። በዚህም መሰረት ጋዜጠኛ ተመስገን ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተፈትቷል።

No comments:

Post a Comment