Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, August 29, 2012

የአቶ መለስ እና የአቡነ ጳውሎስ ህልፈት ለዋልድባ ገዳም መነኮሳት ሌላ መከራ ይዞ መምጣቱን መነኮሳቱ ተናገሩ::

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ያነጋገራቸው የዋልድባ ገዳም መነኮሳት እንደተናገሩት አቶ መለስ ዜናዊ እና አቡነጰ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ ጀምሮ በመኖካሳቱ ላይ የሚደርሰው እንግልት ጨምሯል።

የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ወታደሮችን ልከው መነኮሳቱን እያሳደዱ መገኘታቸው፣ ከ13 በላይ መነኮሳት ከገዳሙ ወጥተው እንዲሸሸጉ ግድ ማለቱን ኢሳት ያነጋገራቸው አባት ገልጠዋል

የታጣቂዎችን እንግልት በመሸሽ ከተሰደዱት መካከል አባ ወልደ ጊዮርጊስ ገብረማርያም፣ አባ ገብረማርያም ገብረዮሀንስ፣ አባ ገብረህይወት ተክለማርያም፣ አባ ገብረስላሴ ዋለለኝ፣ አባ ገብረማርያም ወልደ ሳሙኤል፣ አባ ሀይለ እየሱስ አሸኔ፣ አባ ሀይለእየሱስ ወልደ ሳሙኤል፣ መናኝ ሀይለማርያም ወልደ ሳሙኤል፣ መናኝ ገብረጊዮርጊስ ወልደ ሳሙኤል፣ አባ ገብረስላሴ ዋለልኝ፣ መናኝ ታዲዮስ እና ሌሎች እናቶችም ይገኙበታል።

No comments:

Post a Comment