ዘንድሮ ወያኔን እና ወያኔን አፍቃሪያን ምን ነካቸው ያሰኛል በከፍተኛ አመራሮች ላይ ክፉኛ የሞት ጥላ ጥላውን
አድርቶባቸዋል።በዚህ ወር ብቻ ሶስት ታላላቅ ወያኔ እና ወያኔ አፍቃሪያንን በሞት ጥላ ተነጥቀናል። የቀድሞው የአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ፣በአዲስ አበባ በአሁን ሰአት
በከፍተኛ ደረጃ እየተናፈሰ ያለው ወቅታዊ ወሬ ከመለስ ዜናዊ ሞት ባሻገር የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ መሞት
እንደሆነ ተገልጾአል ።
ለረጅም ዘመን በበሽታ ሲሰቃይ የከረመው አንድርያስ እሸቴ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ
አማካሪ በመሆን ሲያገለግል ነበር ። በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት መሰረተ ድንጋይ ሲጣል የአፍሪካ የሰበአዊ መብቶች
ጥሰትን የሚያስታውሰውን ማእከል ለመገንባት ጊዜአዊ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ነበር ። በተለይም እንድርያስ
እሸቴ በሃገር ውስጥ የሚታሙበት እና የሚጠሉበት ዋነኛ ጉዳይ ቢኖር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መሪ በነበሩበት
ወቅት ሃላፊነታቸውን ያለትወጡ ከመሆኑም በላይ ለብዙ ተማሪዎች ሰለባ የመሆናቸው ምክንያት በዋናነት ይጠቀሳል ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በግቢው ውስጥ የሰበአዊ መብት እና የትምህርት መሟላት ጥቅማጥቅሞችን በሚጠይቁ ሰአት
፣ወታደር ፣ፖሊስ ሰራዊት እና ሌሎች ደህንነቶችን በማስገባት ተማሪዎችን በማሳፈን እና ወደ ዘብጥያ በማስጋዝ ሚና
ሲጫወቱ ብዙ ተማሪዎችም የሞት ጽዋን እንዲቀምሱ ከፍተና ገቢራዊ የሆነ ሚና ተጫውተዋል ።
በሌላም በኩል ሜ.ጀነራል
ሃየሎም አርአያን ሞት ተከትሎ ለግድያው ዋነና አቀነባባሪ እና ተጠያቂ ናቸው ሲሉ የወያኔ አመራር አባላቶች
ሲኮንኗቸው ፣ይህንን ፍራቻ ከህዝቡ እና ከሌሎች የወያኔ አባላቶች ለማራቅ ሲባል ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ መስሪያቤት
በአማካሪነት እንዲዛወሩ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚንስትሩን በአማካሪነት ሲመሩ የቆዩት የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ወዳጆች
እነዚህ ናቸው ።‹‹‹‹…አማካሪ ፋሲል ናሆም፣ አማካሪ ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ፣ አማካሪ ሬድዋን ሁሴን፡፡
No comments:
Post a Comment