Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, August 10, 2012

በደሴ ከተማ ሙስሊሞች ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተጋጩ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የጁመኣን ሶላት ጸሎት ለማድረስ ዛሬ በደሴ አረብገንዳ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ ውለዋል።

በደሴና አካባቢዋ የሚገኙ ሙስሊሞች አረብገንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ለመስገድ በሚሰባሰቡበት ወቅት፣ በስፍራው ሲጠባበቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በመስጊዱ ጸሎት ማድረስ አይቻልም በማለት መከልከላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተፈጠረው።


ፖሊሶቹ ” ሁላችሁም በአካባቢያችሁ በሚገኙ መስጊዶች መስገድ ትችላላችሁ፣ ወደ ዚህ ቦታ የምትመጡት ግን ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ ለማራመድ ነው በማለት” ሲያስታዉቁ፣ ሙስሊሞች በበኩላቸው ” ብላችሁ ብላችሁ የምንሰግድበትን መስጊድ እናንተው ትመርጡልን ጀመር” በማለት ውዝግቡ ተጀምሯል።

ፖሊሶቹ በምእመኑ ላይ እርምጃ መውሰድ ሲጀምሩ፣ ምእመኑም በፖሊሶች ላይ ድንጋይ በመወርወር የአጸፋ እርምጃ ወስዳል።

በዚሁ ውዝግብ ከ5 ያላነሱ ፖሊሶች ሲቆስሉ ከምእመኑ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ በርካታ ወጣቶች በፖሊስ መኪኖች ተጭነው ተወስደወዋል፣ ጉዳት የደረሰባቸውም በርካታ መሆናቸው ታውቋል።

ዘገባውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ፖሊሶች መንገዶችን በማጠር በአካባቢው የሚዘዋወረውን ሙስሊም ሁሉ እየያዙ በማሰር ላይ ናቸው። በርካታ የንግድ ድርጅቶች የተዘጉ ሲሆን፣ በከተማውም ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።

በአዲስ አበባም ቁጥሩ ከ 500 ሺ እስከ 800 ሺ የሚጠጋ ህዝብ ዛሬ በአንዋር መስኪድ ተካሂዷል። መሪዎቹ እንዲፈቱም በድምጽ ጠይቋል። በጅማ ፣ በሻሸመኔ ሶስት መሲኪዶች  እንዲሁ ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጓል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ወርቅነህ ገበየሁ ከሁለት ቀናት በፊት ፦ “ህብረተሰቡ ተረባርቦ ይሄንን ተቃውሞ የማያስቆም ከሆነ፤ የከፋ ነገር ይመጣል!” በማለት ማስጠንቀቃቸውን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment