Source:Fetehe.com
- አንድ ተፈናቃይም ታርዶ ተገኝቷል
ወጣቱ ተገድሎ የተገኘው ሚያዚያ 8/2004 ዓ.ም.ጥዋት ሲሆን በገጀራ ታርዶ ማንነቱ እንዳይታወቅም ተቃጥሎ ሳር ተርከፍክፎበት እንደነበረ ፓርቲው አስታውቋል። ወጣቱ ከጉራፈርዳ ወረዳ ተፈናቅሎ በሬዎቹን በመያዝ ወደ ኮይ ሄዶ ከዘመድ ጋር ይኖር እንደነበረና የቀብር ሥነ-ስርዓቱ በኦቶዋ ቀበሌ ቁጥር አንድ መስጊድ ውስጥ እንደተፈፀመ መኢአድ ጨምሮ ገልጿል።
- አንድ ተፈናቃይም ታርዶ ተገኝቷል
‹‹በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንቺ ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ ሚያዚያ 6/2004 ዓ.ም. ለሚያዚያ 7 አጥቢያ ከጉራፈርዳ ተፈናቅለው ከአካባቢው የተሰደዱ ሰባት የአማራ ብሄር ተወላጅ ቤቶች በካድሬ ተቃጥለዋል›› ሲል መኢአድ ለፍትህ ገለፀ።
መኢአድ በጉራፈርዳ ወረዳ አዲስ ዓለም ማርያም ሰፈር በስተጀርባ ገርጂ ከሚባለው አካባቢ ተፈናቅለው የተሰደዱ የአማራ ተወላጆች የሆኑ ሰባት ቤቶች ከነሙሉ ዕቃዎቻቸው በካድሬዎች በእሳት መጋየታቸውን የዓይን እማኞች ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ መግለጻቸውን ተናግሯል፡፡
ቤታቸው የተቃጠለባቸው አባወራዎች ብዙዎቹ ተሰደው አዲስ አበባ የሚገኙ እንደሆኑና ቤተሰቦቻቸው ግን እዛው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ በየዘመድ ቤቱ በጥገኝነት እንደሚኖሩ ፓርቲው አስረድቷል። መኢአድ የአካባቢው ተወላጆች የሆኑት ምኒጦች አሁንም ለአማራ ተወላጆች ፍቅር ያላቸው መሆኑንና ጥላቻው፣ በደሉና ግፉ እየተፈፀመ ያለው በካድሬዎች መሆኑን የመረጃ ምንጮቹ መናገራቸውን ገልጿል። የወረዳው ባለስልጣናት ግን መጋቢት 29/2004 ዓ.ም. የአማራ ተወላጆ የሆኑ ነዋሪዎችን ሰብስበው ‹‹እስከአሁን ከአካባቢያችን እንዲወጡ ያደረግነው 3000 ሰዎችን ብቻ ነው።
በዕቅዳችን መሰረት 22000 ሰዎችን እናስወጣለን፣ እስካሁን የሰራነው ግን ከአቀድነው በጣም በጣም ትንሹን ብቻ ነው።›› በማለት እንደነገሯቸው ምንጮቹ መግለጻቸውን መኢአድ ጠቅሷል። በተያያዘ ዜናም ኢድሪስ ዓለሙ የተባለ ወጣት ከጉራፈርዳ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ኮይ በምትባል ቀበሌ ተገድሎ መገኘቱን መኢአድ ገልጿል።
ወጣቱ ተገድሎ የተገኘው ሚያዚያ 8/2004 ዓ.ም.ጥዋት ሲሆን በገጀራ ታርዶ ማንነቱ እንዳይታወቅም ተቃጥሎ ሳር ተርከፍክፎበት እንደነበረ ፓርቲው አስታውቋል። ወጣቱ ከጉራፈርዳ ወረዳ ተፈናቅሎ በሬዎቹን በመያዝ ወደ ኮይ ሄዶ ከዘመድ ጋር ይኖር እንደነበረና የቀብር ሥነ-ስርዓቱ በኦቶዋ ቀበሌ ቁጥር አንድ መስጊድ ውስጥ እንደተፈፀመ መኢአድ ጨምሮ ገልጿል።
No comments:
Post a Comment