Source: www.assenna.com
በአሳለፍነው ሳምንት ጀመሮ በኤርትራው መንግስት ኢሳያስ አፈወርቂ ላይ እየተወራ ያለው የሞት ሁኔታ በእጅጉ
ከመስፋቱም በላይ በዛሬው እለት ለንባብ ይበቃ አሰና ዌብሳይት የመሪያቸውን ሞት አስመልክቶ ዝርዝር መረጃ ይዞ የወጣ
ሲሆን ይበልጡኑ ሃተታውን ያደረገው በውስጥ ለውስጥ የሚደረገውን ሹመት ሃገሪቱን ሊጎዳት እንደሚችል እና ከአሁን
በሁዋላ ግልጽ ከህዝቡ ጋር በምርጫ ማድረግ አለባቸው እንጂ በአሁን ሰአት በጊዜአዊ አስተዳደር በሆኑት ጀነራል
ስብሃት ኤፍሬም መመራትም የለባትም ሃገሪቱ ነጻ መውጣት አለባት ሲሉ በሌላም በኩል አጠቃላይ ጊዜአዊ አስተዳደር
ሆነው ስብሃት ኤፍሬም እያሰተዳደሩ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን ፕረዚዳን ኢሳያስ አፈወርቂን ተክተው ይሰሩ የነበሩትን ጀነራል ተክለ ማንጁስን ወደ ዘብጥያ መውረዳቸውን ሪፖርቱ አክሎአል ።
በተያያዘ ዜና የኤርትራ ብሄራዊ ባንክ እና ሌሎችም በመንግስት የሚተዳደሩ ባንኮች በወታደራዊ አሰተዳደር በታንክ
እየተጠበቁ መሆኑን ዜናው ሲያብራራ ፣ለረጂም ዘመናት በእራት ግዞት ከነበሩት አስራ አመስት ባለስልጣናት በህይወት
የተረፉት ጥቂቶቹ በህክምና አገልግሎት ላይ መሆናቸውን ዘግቦአል ። ጉዳዩን በሚስጥር የያዘውን የኤርትራን መንግስት
ሚስጥሩን ከምትደብቁት ለኤርትራ ህዝብ አሳውቁት በማለት የገለጸው ሪፖርቱ መሞታቸውን በግልጽ የታወቀ መሆኑን እና
ሚንስትሮች መደበቃቸው አግባብ አለመሆኑን ይጠቁማል ።
የማለዳ ታይምስ ዝግጅት ክፍል ያነጋገራቸው ምሁራኖች ሲገልጹ
ኢሳያስ አፈወርቂ ከሞቱ እና ጊዜአዊ አስተዳደሩ ይህንን ከፈጸሙ በሃገራቸው ለሚፈጸመው ጉዳይ የሃገር የውስጥ
መከላከያ ጥበቃ ሚንስትሩን መጠበቅ እና አገሪቱን ከከፋ ችግር ማዳንን እና በደህንነት ህዝቡን መጠበቅ እና የውስጥ
ጥበቃውን ካጠናከረ በሁዋላ መግለጽ አለበት ሲሉ ጠቁመዋል ።ይህ ደግሞ ከሌሎች የአደጉ አገሮች ጋር ለሚኖረው ሰላማዊ
ግንኙነት የሚጠቅመው መሆኑንም አክለው ገልጸዋል ።
No comments:
Post a Comment