Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Friday, October 19, 2012

ቂል የያዘው ሰይፍ

(ፕሮፌሰር መስፍን):-
Sibhat Nega
በቅርቡ አቶ ስብሐት በአደረገው ቃለ መጠይቅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመው ወያኔ ዱሮም አስቦበት ወንበሩን ከአማርኛ ተናጋሪዎችና ከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድ ነበር ብሎአል፤ ልብ ላለው አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለት ያለው  ነው፤ ከፊት ለፊት የተሰነዘረው አማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኙን ለመምተር ነው፤ ቂል የሚያደርገው አማራ የሚባል ጎሣ ቢኖርም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአማርኛ ተናጋሪዎች ታጥሮ ትግሬንና ኦሮሞን፣ ወላይታንና ጉራጌን፣ ሌሎችንም የማይነካ መስሎት ከባድ ስሕትት ላይ መውደቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ እሱን የሚያህል ሰው የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ አለማወቁ ያሳዝናል፡፡

የቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ዕውቅና እንዲያገኝ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ



የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት መንፈሳዊ ጉዳዮችን የምትከታተልበት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱንና ለተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያለው ግንኙነትና እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል ረቂቅ ሕጉ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ 
 
በትናንትናው ዕለት የተጀመረውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ 31ኛ መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ የቤተክህነቱ የሕዝብ ግንኙነት መምርያ ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ፣ ‹‹ቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አላት፡፡ መንፈሳዊ ቦታ በመሆኗ ግን እስር ቤት የላትም፡፡ ፖሊስም የላትም፡፡ ፍርድ ቤቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው መንፈሳዊ ተግባራትን ነው፤›› ብለው፣ የተጋጩ ሰዎችን በእርቅና በስምምነት እንዲፈቱ ማድረግ ነው፣ ከመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ውጭ የሆነ ጉዳይ ካጋጠመ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከመሀይምነት ባልተላቀቁ ሰዎች ብዛት ከዓለማችን ሶስተኛ ናት ተባለ

Ethiopia

ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ)፤ ከመሀይምነት የተላቀቁ ሰዎች ብዛትን በተመለከተ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ኢትዮጵያ ከዓለማችን በርካታ አገራት ከመጨረሻ ሶስተኛ መሆኗን ይፋ አደረገ።
 
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ከሶስተኛ አለም አገራት ውስጥ አጥንቶ ይፋ ባደረገው በዚህ ጥናት፤ በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ፤ 28 በመቶው ብቻ ፊደል የቆጠሩና መጻፍና ማንበብ የሚችሉ ናቸው ብሎ፤ ከዓለም አገራት መጨረሻ ከተቀመጡት ከማሊና ደቡብ ሱዳን ቀጥሎ፤ ኢትዮጵያ ከመጨረሻ ሶስተኛ ናት ብሏል።

በዚህ ጥናት መሰረት፤ ህዝቦቻቸውን በበቂ ሁኔታ በማስተማር ከህዝብ ቁጥራቸው 99.9 በመቶ በማስተማር ኩባ አንደኛ፤ ህንድ 74.1 በመቶ የተማረ ህዝብ በመያዝ 2ኛ ስትሆን፤ በኢትዮጵያ 28 ከመቶ ብቻ ከአጠቃላዩ ህዝብ ውስጥ ከመሀይምነት የተላቀቀ ነው። ኢትዮጵያ ከ184 አገራት ውስጥ 182ኛ ሆና ነው በ3ኛ ደረጃ የተፈረጀችው።

በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል

ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት  በወለደች በማግስቱ  ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ።

Saturday, October 13, 2012

ሟቹ ጠቅላይ ሚንስትር ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ባህር ዳር ላይ የጀምረውት የነበረው የሬዲዮ ጣቢያ ግንባታ ተቋረጠ

Radio station

መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ በቆየባቸዉ አመታት ያከናውናቸው የነበሩት በርካታ ጉዳዮችን ለፓርቲውም ሆነ ለሚንስትሮች ምክር ቤትም ወይም ለይስሙላ ፓርላማ እንደማያሳውቅ ምንጮች አጋለጡ::ምንጭ አክሱማዊት በፌስቡክ እንዳወረሰችን


ኢትዮጵያ አገራችንን ለ21 አመታት የገዛው ዘረኛውና አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ ትላልቅ ውሳኔዎችን በዙሪያው ላሰባሰባቸው የካቢኔ ምንስትሮችም ሆነ ለፓርላማው ሳያሳውቅ በራሱ ፈቃድ ብቻ ያስተላልፍና ያስፈጽም እንደነበረ ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ ከነበሩ ሚንስተሮች የተገኘ መረጃ አጋለጠ።

መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት ለማንም ሳያማክር በግል ሥልጣኑ አስጀምሮት ከነበሩ ፕሮጄክቶች አንዱ ለኤርትራ ተቃዋሚዎች ይሰጥ የነበረው የፋይናንስና የማቴሪያል እርዳታ እንደነበረ የገለጹ ምንጮች የርሱን መሞት ተከትሎ ተቃዋሚዎቹ ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው ገልጸዋል።

በጋምቤላ የሚንቀሳቀሰው የናይሎቲክ ህዝቦች ንቅናቄ፤ ሰሞኑን ከኢትዮጲያ መንግስት ወታደሮች ጋር መጋጨቱ ተገለጸ

ኢሳት ዜና:-የኢሳት ተባባሪ ዘጋቢ ጋዜጠኛ አግዋ ጊሎ፤ የጋምቤላ ምንጮችን በመጥቀስ እንዳመለከተው፤ በቅርቡ በተካሔደው ግጭት አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ሲገደል፤ ሶስት ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል።

Sunday, October 7, 2012

ከፖለቲካ ፍጥጫው በስተጀርባ (ከእየሩሳሌም አርአያ)

Journalist Araya
በገዢው ሰፈር ጎራ ለይቶ ከተለኮሰው የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ ጀርባ አገር እና ህዝብን የሚጎዳ አደገኛ ተግባር በግልጽ እና በስውር እየተካሄደ እንዳለ ከተለያዩ የፓርቲው ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

በተለይ በብአዴን እና በህወሃት ቱባ አመራሮች መካከል ስር ሰዶ የቆየው እና የአቶ መለስን ህልፈት ተከትሎ ያገረሸው የውስጥ ሽኩቻ ሁለት ቡድኖች የሃይል አሰላለፋቸውን ለማጠናከር«ይረዱናል » የሚሏቸውን የሌሎች ፓርቲ ሹማምንት እና የመከላከያ የጦር አዛዦች ከጎን የማሰለፉን ተግባር ቀጥለውበታል።ለግንዛቤ እንዲረዳ የሃይል አሰላለፉን በጥቂቱ በመዳሰስ ወደ ዋናው ነጥብ እናምራ ።

ከበረከት እና ዓዜብ ጎን በመሰለፍ ቀዳሚ የሆኑት አቶ ተፈራ ዋልዋ እና አዲሱ ለገሰ ናቸው።አቶ አዲሱ በይፋ ከሚታወቀው የአየር መንገድ የቦርድ ሃላፊነታቸው ባሻገር ኮተቤ መስመር በሚገኘው እና «የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ማኔጅመንት ት/ቤት »ተብሎ በተከፈተው ተቋም ዋና ሃላፊ እና ለባለስልጣናት እንዲሁም ካድሬዎች መምህር ጭምር ናቸው ። ከመለስ መታመም ወዲህ የህወሃት ካድሬ ላልሆኑ በአቶ አዲሱ እየተሰጠ ያለው ፖለቲካዊ ትምህርት ሳይሆን የበረከትን አቋም የሚያቀነቅን እና ህወሃትን የሚያጥላላ ቅስቀሳ ሆኖአል ።

Saturday, October 6, 2012

የ21ኛው ክፍለ ዘመን ይሁዲ: ከማተቤ መለሰ ተሰማ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ፡ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ እንደ ያኔው ናዚ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።

ይህ የጥፋት ዘመቻ በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን በእቅድ ተነድፎ እየተከናወነ ያለ መሆኑን የህዋሀቱ አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ የአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝን የኢስሙላ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ሹመት አስመልክቶ ገዛ ተጋሩ ከተባለ ፓለቶክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፡ ስልጣንን ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታይና ከአማራ ነጥቀነዋል አላማችንም የኸው ነበር ሲሉ ሰነምግባር ባልገራው አንደበታቸው በድፍረት መናገራቸው የወያኔ ጉዞ ከየት ወዴትነት ማሳየት ከሚችሉ ኩነቶች እንደ አንዱ ሊወሰድ የሚገባው ነው።

Thursday, October 4, 2012

በሰሜን ሸዋ የሚገኙ መምህራን በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት እየታደኑ ነው

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሸዋ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ መንግስት አንድ ለአምስት በሚለው አደረጃጀቱ የግንባሩ አባላት ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም ያላቸውን መምህራን እያዋከበ ነው።

የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ መምህራን የአመለካከት ችግር አለባቸው፣ ከሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር  ትሰራላችሁ፣ የራሳችሁን የፖለቲካ አመለካከት ታራምዳላችሁ እየተባሉ ወከባና ማስፋራሪያ ሲደርስባቸው መቆየቱን መምህራን ይናገራሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሀይለማርያም ማሞ ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ በቁጥር ሰ/ሸ/ዞ/ፖ/መ/1012/04 በቀን 28/10/2004 ዓም በጻፈው ደብዳቤ ላይ  ብርሃኔ አሰብአለሁ ደረሰ፣  ባይሌ ደርሰህ ምህረቴ እና  አሰፋ ወንድሙ መከተ የተባሉት መምህራን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሲያራምዱ በመገኘታቸው እየታደኑ መሆኑን ገልጿል።

Tuesday, October 2, 2012

ኢህአዴግ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ እና የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጆችን ለማሰር መሰናዶ እያደረገ መሆኑን ምንጮቻችን ገለጹ

Temesgen Desalegn and his main editors
ኢሳት ዜና:-የደህንነት ሰዎችም በድጋሚ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ውሎና አዳር መከታተል መጀመራቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው የዓይን እማኞች ገልጸውልናል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን እንደገለጠው በዛሬው እለት የደህንነት ሰዎች በአካባቢው ባይታዩም እስካለፈው ቅዳሜ ድረስ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ሲከታተሉት እንደነበር ገልጧል። የኢሳት ዘጋቢ ከጋዜጠኛ ተመስገን ጋር ቃለምልልስ በሚያደርግበት ወቅት ስልኩ በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲቸገር መዋሉን  ገልጧል።