Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, October 4, 2012

በሰሜን ሸዋ የሚገኙ መምህራን በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት እየታደኑ ነው

መስከረም ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሸዋ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት፣ የኢህአዴግ መንግስት አንድ ለአምስት በሚለው አደረጃጀቱ የግንባሩ አባላት ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም ያላቸውን መምህራን እያዋከበ ነው።

የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፈቃደኛ አልሆኑም የተባሉ መምህራን የአመለካከት ችግር አለባቸው፣ ከሌሎች የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ጋር  ትሰራላችሁ፣ የራሳችሁን የፖለቲካ አመለካከት ታራምዳላችሁ እየተባሉ ወከባና ማስፋራሪያ ሲደርስባቸው መቆየቱን መምህራን ይናገራሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሀይለማርያም ማሞ ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ በቁጥር ሰ/ሸ/ዞ/ፖ/መ/1012/04 በቀን 28/10/2004 ዓም በጻፈው ደብዳቤ ላይ  ብርሃኔ አሰብአለሁ ደረሰ፣  ባይሌ ደርሰህ ምህረቴ እና  አሰፋ ወንድሙ መከተ የተባሉት መምህራን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሲያራምዱ በመገኘታቸው እየታደኑ መሆኑን ገልጿል።


” በትምህርት ቤታችሁ ውስጥ የትምህርቱን ስራ የሚያደናቅፉ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ፖሊስ መምሪያችን ያረጋገጠ ሲሆን” በማለት የሚያትተው ደብዳቤ በማያያዝም፣ ” ከዚህ በፊት በትምህርት ቤታችሁ የሚገኙ መምህራን 1ኛ ብርሀኔ አስባለሁ ደርሰህ ፣ 2ኛ ባይሌ ደርሰህ ምህረቴ 3ኛ አሰፋ ወንድሙ መከተ የተባሉት ከወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ከትምህርት ቤታቸው በአገኘነው መረጃና ከመኖሪያ ቤታቸው በአገኘነው ልዩ ልዩ ዶክመንቶች ቀድም ሲሉ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩና በመጨረሻም ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመገናኘት በትምህርት ቤቱ ውስጥ የራሳቸውን የፖለቲካ አመለካከት ሲያራምዱ እንደነበር ፖሊስ በተለያዩ መረጃዎች አረጋግጧል።

 በመሆኑም የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ከዚህ መሰል ተግባር እንዲቆጠብ እያሳሰብን ከላይ የተዘረዘሩት የትምህርት ቤቱ መምህራን ላይ ፖሊስ በመከታተል ላይ ሲሆን በተገኙ ጊዜ ለህግ ቀርበው የሚጠየቁ መሆኑን እንገልጻለን” ብሎአል።

መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት፣ የማደኛ ትእዛዝ የወጣባቸው መምህራን እስካሁን ድረስ የደረሱበት አልታወቀም። ከእነዚህ መምህራን ጋር ቅርበት የነበራቸው መምህራን በአንድ ለአምስት አደረጃጀት በታቀፉ ሌሎች መምህራን ክትትልና ስለለ እየተካሄደባቸው ነው።

መምህራኑ ” በአንድ ለአምስት አደረጃጀት የመናገር መብታችንን በመገደብ በአገራችን ሰርተን መኖር እንዳንችል የኢህአዴግ መንግስት የተቃዋሚ ድርጅቶችን አላማ ትደግፋላችሁ በሚል በተደጋጋሚ ጫና በመፍጠርና በማስፈራራት ሰብአዊና ዲሞክራሲአያዊ መብታችን እየተጣሰ ከፍተኛ በደል እየተፈጸመብን ነው። እባካችሁ ብሶታችንን የሰብአዊ መብትን እናስከብራለን ለሚሉ አለማቀፍ ወገኖችና ለኢትዮጵያ ህዝብ አሰሙልን ” ብለዋል።

ሙሉውን ደብዳቤ ኢሳት በድረገጹ ላይ የሚያወጣው በመሆኑ ድረገጻችንን እንደትጎበኙ እንጋብዛለን
በዚሁ ዞን በሸዋ ሮቢት ትምህርት ቤት ደግሞ በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ መምህራን ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸውን መምህራን ተናግረዋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ  ንጉስ ግደይ የተባለ መምህር ስብሰባ ረግጠህ ወጥተሀል ተብሎ ከስራ እንዲታደግ መደረጉን መምህራን ተናግረዋል ። የመምህሩን እግድ በመቃወም መምህራን ጥያቄዎችን እያቀረቡ መሆኑም ታውቋል። See ESAT Ethiopian News Oct. 03, 2012 


No comments:

Post a Comment