Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, May 28, 2012

ከግንቦት እስከ ግንቦት

By ተመስገን ደሳለኝ
የካቲት 11/1967 ደደቢት በረሃ
‹‹የትግራይ ህዝብ በብሔራዊ ጭቆና ውስጥ ነው። እናም የግድ ከዚህ ብሔራዊ ጭቆና እና ብዝበዛ ነፃ የሚያወጣው ብሔራዊ ድርጅት ያስፈልገዋል››  (ይህንን መልዕክት የምናገኘው ህወሓት በ1967ዓ.ም የካቲት 11 ቀን ወደ በረሃ ለትግል ሲወጣ ያወጣው ማኒፌስቶን በግርድፉ ከትግርኛ ወደ አማርኛ ስንመልሰው ነው) ግንቦት 20/1983 አዲስ አበባ ‹‹ጀግናው  የኢህአዴግ ሰራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ተቆጣጥሮታል።

ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት፡፡
›› (በዘመቻ ወጋገን አዲስ አበባ ሙሉ  በሙሉ በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር መውደቋን የኢህአዴግ ታጋይ ያበሰረበት ዜና) 

ግንቦት 10/2004 ዋሽንግተን-አሜሪካ
“Meles zenawi is a dictator! Free
Eskinder Nega and all political prisoners!
We need freedom more than food! Meles
has committed crimes against humanity!
We need freedom! Freedom! Freedom!
Freedom!››
(መለስ ዜናዊ አምባገነን ናቸው፤ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፤ ምግብ ያለነፃነት ዋጋ የለውም፤ መለስ በሰው ልጆች ላይ ወንጀል ፈፅመዋል፤ ነፃነታችንን እንፈልጋለን፤ ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት!) (ይህ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ
በዋሽንግተን ዲሲ አዘጋጅተውት በነበረው አለም አቀፍ ስብሰባ ላይ በአዳራሹ ውስጥ በመገኘት የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ንግግርን በማቋረጥ ያሰማው የተቃውሞ ድምፅ ነው) …ለአስራ ሰባት አመት በትግል፤ ያሳለፈው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ከነገ በስቲያ (ግንቦት 20/2004ዓ.ም) ድፍን ሃያ አንድ አመት ይሞላዋል። 

ግንባሩ ከተመሰረተበት ከ1981ዓ.ም ጀምሮ የሚመራው ዛሬም በስልጣን ላይ ባሉት ሊቀመንበር መለስ ዜናዊ ሲሆኑ፣ የመንግስት ስልጣን ከያዘም በኋላ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ራሳቸው መለስ ናቸው።  ይህ ሁኔታም ድርጅቱን ለሁለት መሰረታዊ ትችቶች ዳርጎታል። የመጀመሪያው የፓርቲ (የውስጥ) ዴሞክራሲ ያለመኖሩ ማረጋገጫ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ድርጅቱ ምንም እንኳ ሰባት ሚሊዮን አባላት ያሉት ቢሆንም አቶ መለስን ለመተካት አንድም ብቁ ሰው እንደሌለው ወይም ማፍራት ያለመቻሉን የሚያሳይ በመሆኑ ነው። 

የመከኑ ተስፋዎች… 
እንደ 17 አመቱ የትግል ታሪክ ትርክት ከሆነ ኢህአዴግ ለስልጣን የበቃው መራራ ትግል በማድረግ እና ከ60-70 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ህይወት በመገበር ነው። ህም ሆኖ ወደ ስልጣን በመጣበት ሰሞን በርካታ መልካም ነገሮች ከመኖራቸው አንፃር፣ የተከፈለውን መስዋዕትነት ያህል ባይሆንም ብዙ ተስፋ የተጣለባችው ወሳኝ ጉዳዮች ነበሩ፡፡ እናም የዘንድሮውን ግንቦት ሃያ በማሰመልከት ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱን መዘን በሃያ አንድ ዓመት ውስጥ የት እንደደረሱ እንፈትሻለን፡፡ ነፃ ፕሬስ፣ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እና የሰብአዊ መብት አያያዝ፡፡

ነፃ ፕሬስ
በሀገሪቱ ታሪክ የነፃ-ፕሬስ በአዋጅ  የተፈቀደው በኢህአዴግ ዘመን ለመሆኑ መስካሪ አያስፈልግም። በእርግጥ በአፄ ምኒልክ ዘመን በአንድ ግሪካዊ ባለቤትነት በየሳምንቱ 200 ኮፒ ያህል የሚታተም ‹‹አእምሮ›› የተባለ ጋዜጣ የሀገሪቱ የመጀመሪያው የፕሬስ ውጤት መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዓመታዊ መጽሔት በህዳር 2002 ዓ.ም እትሙ በ1915 ዓ.ም. በምፅዋ ከተማ እየተዘጋጀ የሚታተም ‹‹መለከተ ሰላም››ን ጨምሮ በግሪካውያን ‹‹ኢትዮ አለም›› እና በብላታ ጌታ ኀሩይ ወልደስላሴ ‹‹ኮከበ ጽባህ›› የሚባሉ ጋዜጦች ይዘጋጁ እንደነበር ገልጿአል።

ከ16 ዓመት በኋላ ደግሞ በ1917 ዓ.ም. ‹‹ብርሃንና ሰላም›› የተባለ ጋዜጣ በንጉሰ ነገስቱ ትዕዛዝ  መንግስት ልሳን ሆኖ መታተም ጀመረ። ከዚህ በኋላም እነሆ ዛሬም ድረስ የመንግስት ‹‹አንደበት›› ሆኖ እያገለገለ ያለው ‹‹አዲስ ዘመን›› ጋዜጣ በ1933ዓ.ም ተቋቋመ። በ1935ዓ.ም ‹‹ኢትዮጵያን ሄራልድ›› የህትመት ስራን ተቀላቀለ፡፡ እንደ ብሮድካስት ዘገባ በአፄው ዘመን ‹‹የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፣ ሰንደቅ አላማችን፣ ኅብረት፣ አክሎቲዲያኖ፣ አልአለም እና በሬሳ›› የተሰኙ ጋዜጦችም በተጨማሪነት ለመታተም ችለዋል። ከመጽሔት ደግሞ በንግስቲቱ ስም የተሰየመችው ‹‹መነን›› መጽሔት  የመጀመሪያዋ ነች።

ንጉሱ ወድቀው ወታደራዊው የመንግስቱ ኃ/ማርያም መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ (ውስጥ ውስጡን የኢህአፓ እንደሆነች የሚነገርላት) በጨረታ ማስታወቂያ ስር የምትታተመው ‹‹ጎህ›› መጽሔት ለሁለት አመት ያህል ብቻ ብቅ ብላ፣ ከእነ‹‹እናት ድርጅቷ›› ኢህአፓ ጋር በወታደራዊ ኃይል  ምድረ ገጽ እንድትጠፋ ከመደረጓ ውጭ፤ በአዋጅ የፕሬስ ነፃነት ከመገደቡም አልፎ ቅድመ ምርምራ በይፋ ስራ ላይ ውሎ ስለነበር ደርግ ከነፃ ፕሬስ ጋር ምንም አይነት ‹‹ፅዋ›› አልነበረውም። …ኢህአዴግ የእርስ በእርስ ጦርነቱን በአሸናፊነት ተወጥቶ በ1983 ወርሃ ግንቦት ወደ ስልጣን ሲመጣ የነፃ ፕሬስ ህልውናን በአዋጅ በማረጋገጡ የመጀመሪያ ሆና የተመዘገበችውን የእስክንድር ነጋን ‹‹ኢትዮጲስ›› ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነፃ ጋዜጦች እና መጽሔቶች ከአዲስ አበባ አንስቶ በሁሉም የክልል አውራ ጎዳናዎች ተጥለቀለቁ። 

የብሮድካስት ምንጭ ‹‹በ1985ዓ.ም በሀገሪቱ 118 ጋዜጦች እና መጽሔቶች ተመዝግበው ስራ የጀመሩ ሲሆን፤ ይኸው አሀዝ በ1990ዓ.ም.554 ደርሶአል›› ይላል። በ2000ዓ.ም. በሀገሪቱ የነበረው መጽሔት እና ጋዜጣ ቁጥር ከአንድ ሺ በላይ ደርሶ እንደነበረም አረጋግጧል። ‹‹የኢትዮጵያ ብሮድካስት ለስልጣን ዓመታዊ መጽሔት›› በሚል የታተመው የኤጀንሲው ልሳን በዚህ ዕትሙ አንድ አስቂኝ ጥያቄም ይዟል። እንዲህ የሚል ‹‹የህትመት ውጤቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። በ2000 ዓ.ም.ተመዝግበው የነበሩት ከአንድ ሺህ በላይ ደርሰው እንደነበር ቢያውቁ እውነት ላይ-መስል ይችላል፡፡ ግን ነው! ከዚህ ላይ ሊቀርብ የሚገባው ጥያቄ ግን ይህን ያህል ቁጥር የነበራቸው  ጋዜጦችና መጽሔቶች አሁን ከወዴት ገቡ? የሚል ይሆናል›› ቀልዱ የሚገባን ደግሞ በኢትዮጵያ ለህትመትም ሆነ ለኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ፍቃድ የሚሰጠውም ሆነ የሚከለክለው ይኸው መስሪያ ቤት መሆኑን ስናውቅ ነው።

 ልክ ከፕሬስ ህልውና ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ‹‹የገጠርና ግብርና ሚንስቴር›› ወይም የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር›› መስሪያ ቤትን ይመስል ‹‹ሚዲያዎቹ የት ገቡ?›› ሲል መጠየቁ ነው ቀልዱን መራር ቀልድ የሚያደርገው። እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ማንሳት ይቻላል። ምሳሌ በመጀመሪያስ ጋዜጦቹ እንዲህ በብዛት እንዲታተሙ ለምን ፍቃድ መስጠት አስፈለገ? በእርግጥ የዚህ ጥያቄ መልስ አዙሮ አዙሮ ‹‹ምዕራባውያንን ለማስደሰት›› የሚል ምላሽ ላይ ቢያደርሰንም፤ በዚህ መሀል ግን የኢህአዴግ የተደበቀ ‹‹ቀጭን የማሳደድ እና የማጥፋት ፍላጐት›› እንደነበረ መካድ አይቻልም። ሆኖም ምንም እንኳ አመራሮቹም ሆኑ ታጋዮቹ በሶሻሊዝም እና ማርክሲዝም አስተሳሰብ የተቀኙ ቢሆኑም ከቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዢዎች የተለዩ እንደሆኑ የማሳየቱ ፍላጐት አልነበራቸውም ልንል አንችልም። 

እናም የግንባሩን መሪዎች የእነዚህ ውጤት ነው በወቅቱ ያአለአንዳች ማንገራገር የነፃ ፕሬስ ህልውናን በአዋጅ እንዲፈቅዱ ያስገደዳው። ነገር ግን ፕሬሱ በስራ ላይ በዋለ ማግስት ከመንግስት ጋር መላተም ጀመረ። ለዚህም እንደመነሻ የሆነው የተሸነፈው የሀገሪቱ ሰራዊት ‹‹የደርግ ወታደር›› ተብሎ መበተኑ፣ በርካታ ሰራተኞች ያሉአቸው መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች እንዲፈርሱ እና ሰራተኞቹም ያለአንዳች ካሳ መበተናቸው፣ የብሔር ፖለቲካ መጦዝ፣ እንዲሁም የኤርትራ መገንጠል እና ሀገሪቱ ያለወደብ መቅረት… በነፃው ፕሬስ በስፋት የሚተችበት መሆኑ ነው ገዥውን ፓርቲ ‹‹ሆደባሻ›› ያደረገው። በአናቱም በእነዚህ ጋዜጦች እና መፅሄቶች የሚስተናገዱት ጽሑፎች የንባብ ባህል ከመፍጠርም አልፈው በህብረተሰቡ ውስጥ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ እየሆኑ መሄዳቸውም ለአዲሱ መንግስት ምቾት እንደነሳው ፍንጮች መታየት የጀመሩት ገና በጠዋቱ ነው። 

ከዚህ ጎን ለጎንም ያለፉት ስርዓቶች ትተው ያለፉት የ‹‹ፖለቲካን በሩቁ›› አመለካከት ቀስ በቀስ ደብዘዝ ጀመረ። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እና አመራሮችም የመንግስት ዋነኛ የአደባባይ ነቃፊ ለመሆን ቻሉ። በተጨማሪም የመንግስት ሚዲያ ሙሉ በሙሉ ‹‹የፕሮፓጋንዳ ማሽን›› በመሆኑ እነዚህ ጋዜጦች እና መጽሔቶች አማራጭ የመረጃ ምንጭ ተደርገው የተሻለ ተአማኒነት ግኘታቸው ከቀን ወደ ቀን ኢህአዴግን እያስቆጣው ሄደ። የእነዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ነው በምርጫ 97 ሀገራዊ መነቃቃት ፈጥሮ በህዝብ ተሳትፎ በአፍሪካ አቻ ያልተገኘለት ምርጫ ሊካሄድ የበቃው።  እንደሚታወቀውም የምርጫው ውጤት ወደተቃዋሚዎች ማጋደሉን ተከትሎ ግንባሩ ወደ እውነተኛ ማንነቱ ተመልሶ በቀጥታ ብትር እና በተለያዩ አፋኝ አዋጆች ጭምር ‹‹ነፃ ሚዲያ›› ወደመቃብር ተገፋ።

እንግዲህ ከግንቦት ሃያ ፍሬዎች አንዱ የሆነው ነፃ ፕሬስ ዛሬ ሙሉ በሙሉ የለም ሊባል የሚችልበት ደረጃ ላይ ለመድረስ በቀናት የሚቆጠሩ እድሜዎች ብቻ መቅረቱን አስተውለን፣ በቅርቡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በ‹‹ስታንዳርድ ውል›› ስም በስራ ላይ ለማዋል ደፋ ቀና እያለበት ያለውን ‹‹የቅድመ ምርመራ ህግ›› ስንደምርበት ነው ከሃያ አንድ አመት በኋላ፣ ያውም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ደምና አጥንታቸውን ከስክሰው ወደ ገረሰሱት ስርዓት መመለሳችንን የምንረዳው-ግንቦት ሃያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት፡፡

 የመድበለ ፓርቲ ስርዓት 
ይህ ደግሞ ሌላኛው የግንቦት ሃያ ፍሬ ነው። ምክንያቱም ለ17 አመት የነበረውን የአንድ ብቸኛ ፓርቲ ስርዓት ገርስሶ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በተግባር የታየው ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣበት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት ነውና።

ግንቦት 20/1983ዓ.ም ኢሠፓ የተሰኘው የመንግስቱ ኃ/ማርያም ፓርቲ ከስልጣን ከወረደ በኋላ ኢህአዴግ ራሱን በኢሠፓ ቦታ ተክቶ ብቻውን ስልጣን አልያዘም። ይልቁንም ሁሉንም በኢትዮጵያ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች (ከኢህአፓ እና መኢሶን በስተቀር) በአዋጅ ሰብስቦ ስልጣን አካፈለ እንጂ፤ ያውም በምርጫ ሳይሆን በዕደላ። በዚህም መሰረት በ1983ዓ.ም መጨረሻ ‹‹ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ምክር ቤት ተወካዮች›› የሚባል በአጠቃላይ 87 የውክልና ቦታ /መቀመጫ/ ያለው መንግስት ተቋቋመ። ከዚህ ውስጥም ኢህአዴግ 32 (37%) ወንበር ብቻ ወስዶ የተቀረውን ኦነግን ጨምሮ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች አከፋፈለ። (አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አንድ፣ የሰራተኞች ማህበር ሶስት ወንበር እንዲያገኙ ተደርገዋል)።

ይህንንም ተከትሎ የትግሉ ዋነኛ የስንቅና ትጥቅ ምንጭ የነበሩት ምዕራባውያን ‹‹በኢትዮጵያ መድበለ ፓርቲ ስርዓት እውን የሚሆንበት መደላድል ተፈጠረ›› ሲሉ ከማድነቅም አልፈው የሽግግር መንግስቱን በሙሉ አቅማቸው መርዳት ጀመሩ። ይህ ደግሞ ድርጅቱ ታግሎ ያመጣው መልካም ነገር በመሆኑ የሚመሰገንበት ነው። / ምንም እንኳን ምስጋናው ዘላቂ ባይሆንም/ የሆነ ሆኖ በቀጣዮቹ አመት በሚታዩ እና በማይታዩ መሰናክሎች በሽግግር መንግስቱ ውስጥ በርካታ ወንበር የነበራቸውን ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማፈናቀል ተጀመረ። ከዚህ በኋላም የአራቱ አመት የሽግግር ዘመን አልፎ፣ ህገ መንግስቱ ፀድቆ እና ሀገሪቱ የምትመራው በፓርላሜንታዊ ስርዓት መሆኑ በህገ መንግስቱ ከተገለፀ በኋላ ፓርላማው 547 ወንበር እንዳለው ተደንግጐ የ1987ዓ.ም ምርጫ ተካሄደ።

የዚህ ምርጫ ውጤት ምን ሆነ? የሚለውን ካየን፣ ውጤቱ ይህ ነው፡- ኢህአዴግ 493፣ አጋር ፓርቲዎች እና ተቃዋሚዎች 40 ወንበሮች ሲያገኙ ቀሪዎቹ አስራ አራት ወንበሮች በግል ተወዳዳሪዎች ተያዙና በጥቂቱም ቢሆን የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ለመኖሩ ምልክት ሆኑ። በምርጫ 92 ደግሞ ኢህአዴግ 481 ወንበር ሲያገኝ፤ አጋር ፓርቲዎች 40 ወንበር ተቃዋሚዎች እና የግል ተወዳዳሪዎች በድምሩ 13 ወንበር አገኙ። በእርግጥ ለተቃዋሚዎች ደካማ ውጤት፤ ደካማ አደረጃጀታቸው እንደ ምክንያት በስፋት ይቀርብ እንደነበር አስታውሳለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትር መለስም ‹‹ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ ከአገኘን ግማሽ መንገድ ድረስ ሄደን እንቀበለዋለን›› ሲሉ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ድክመት አዘኔታቸውን የገለፁበት ጊዜ ነበር-ያ ጊዜ። 

በአናቱም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ቁጥር መብዛት እና እርስ በእርስ ያላቸው ንቁርያ የድክመታቸው አንዱ ምክንያት ተደርጎ በተንታኞች የሚቀርብበት ዘመንም ነበር-ያ ዘመን። በዚህ ሁኔታም ምርጫ 97 ደረሰ። በዋዜማው በ1996 ክረምት በተደረገው የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ ሊቀመንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ‹‹ቀጣዩ ምርጫ እንከን የለሽ ይሆናል›› ሲሉ ቃል ገቡ። ይህንም ተከትሎ አንድም የህዝቡን ‹‹ወይ ተባበሩ፤ አሊያም ተሰባበሩ››ን ግፊት፣ ሁለትም የታላላቅ ሰዎች ሽምግልና ታክሎበት በወቅቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራ የነበሩት መኢአድ እና ኢዴፓ ዘግይተው የተቀላቀሉትን ቀስተደመና እና ኢዴሊን ጨምረው ‹‹ቅንጅት ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ››ን ሲመሰርቱ፤ ራሳቸውን በዘውግ ከልለው የቆዩት የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት እና የኦሮሞ ኮንግረስ ፓርቲም መቀመጫቸውን በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ካደረጉ ሌሎች 12 ድርጅቶች ጋር የጋራ ህብረት በመፍጠር ‹‹የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ህብረት (ኢዴኃሕ)››ን መስርተው በተቃውሞ ጎራ ያለው ቡድን ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዲሆን አደረጉት።

በዚህ እና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች አብዛኛው የፖለቲካ ተንታኞች ምርጫ 97 የኢትዮጵያውያኖች የፖለቲካ ንቃተ ህሊና የተሻለ ደረጃ የደረሰበት እንደነበር ይስማማሉ። በዚህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው መራጭ በተሳተፈበት ምርጫም ኢህአዴግ ያልጠበቀው ሽንፈት ደረሰበት። ይህንን ሁኔታም አቶ በረከት ስምኦን ‹‹የሁለት ምርጫዎች ወግ›› በሚል ርዕስ ባሳተሙት መፅሐፋቸው ላይ ውጤቱን ‹‹የብራ መብረቅ›› ሲሉ ምን ያህል ከባድ ሽንፈት እንደደረሰባቸው ገልፀውታል። ይሁንና ይህንን ምርጫ ተከትሎ ድርጅታቸው በመድብለ ፓርቲ ስርዓትም ሆነ በምርጫ ፖለቲካ ላይ መአት እጆቹን ለቅጣት አነሳ። እናም የምርጫውን ግርግር ታክኮ የተነሳውን ሁከት እንደምክንያት በማድረግ ሁሉንም የቅንጅት አመራር ጨምሮ ከ40 እስከ 50 ሺህ የሚገመቱ ዜጎችን ‹‹የተቃዋሚ ተባባሪ እና የጎዳና ላይ ነውጠኛ›› በሚል የእመቃ እርምጃ ወሰደባቸው።

ከዚሁም ጋር መራጮች በምርጫው ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲኖራቸው፣ ሀገራዊ ንቃተ ህሊና እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት ጋዜጦች ህትመታቸው እንዲቆም ሲደረግ፤ አሳታሚዎቹ እና ጋዜጠኞቹ ‹‹የአመፁ ጠንሳሽ›› ተብለው ለ20 ወር እስር ተዳረጉና ፋይሉ ተዘጋ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ‹‹ሀገራዊ ድብት›› የሰፈነው። በዚህ ድብት ውስጥም ነው ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ አውራ ፓርቲ እንደሆነ ያወጀበት ምርጫ 2002 የተካሄደው። በዚህም የፓርላማው መቀመጫ የአንድ ፓርቲ ብቻ ሆነ። እንግዲህ ይህ ነው ሌላኛው ወደ ግንቦት ሃያ ሺ ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ሶስት ለመመለሱ ማረጋገጫ የሚሆነው። እናም እዚህም ጋር እንዲህ ልንል እንችላለን ‹‹ሌላ ፋይል ተዘጋ››፤ መድበለ ፓርቲ ስርዓት ጠፍቶ አውራ ፓርቲ ነገሰ፡፡

 ሰብዓዊ መብት 
ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣበት ዕለት ጀምሮ አንዳችም ‹‹ተስፋ የሚሰጥ›› ነገር ያልታየበት ነው-የሰብዓዊ መብት አያያዙ። በመጀመሪያዎቹ ጥቂት አመታት በመድብለ ፓርቲ ስርዓት ላይ በጎ ጅማሬዎች እንደነበሩ ከላይ ተነጋግረናል። ነገር ግን የሰብዓዊ መብት አያያዙ በ1969ዓ.ም ሆነ በ1983ዓ.ም ወይም በ2004ዓ.ም አንዳች ልዩነት የለውም። ደርግ ለሰብዓዊ መብት ቅንጣት ታኽል ደንታ የለውም። ኢህአዴግም የለውም። በዚህ መካከል ልዩነት የለም። ምንአልባትም በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የተደረገው ጦርነት ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር በተገናኘ ብቻ ቢሆን ኖሮ ሁለቱም በጋራ ይሰለፋሉ እንጂ ወደ ጦርነቱ አይገቡም ነበር ማለት በሚያስደፍር ሁናቴ ነው ተመሳሳይነታቸው። ሁለቱም ስርዓቶች ሰብዓዊ መብትን ሲጥሱ ለየትኛውም የሀገሪቱ ህግ አይጨነቁም። ከዚህ በተጨማሪም ይህን አይነቱን ወንጀል ሲፈጽሙ ከጊዜ ልዩነት ውጭ የሚጠቀሙበት መንገድ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ለንፅፅር ይርዳ ዘንድ በሁለቱም ስርዓት ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተደረጉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንደምሳሌ እንይ።

ሚያዚያ 23/1969-ደርግ
‹‹…የ1969 ዓ.ምቱ የላባደር ቀን (ሜይ ዴይ) እንደማንኛውም ተራ ቀን እንዲያልፍ ተወስኖ ነበር። የኢላአማ በይነ ቀጠና ኮሚቴ በዚህ ውሳኔ ላይ ያለውን ቅሬታ አሰምቶ ትናንሽ ቡድኖችን በቀበሌ ደረጃ አዘጋጅቶ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ሃሳብ አቀረበ። ይህ የኢላአማ ሃሳብ በአዲስ አበባ በይነ ቀጠና ኮሚቴ ተቀባይነት አገኘና ለሰልፍ የሚደረጉ ዝግጅቶች መካሄድ ጀመሩ። …ሰልፉ ከመደረጉ ከሶስት ወይም ከአራት ሰአት በፊት የኢህአፓ የአዲስ አበባ በይነ ቀጠና ኮሚቴ አገዛዙ ስለተቃውሞ ሰልፎቹ ዝርዝር መረጃዎች እንዳገኘ የሚገልፅ መረጃ ደረሰው…. በዚህ ዕለት አገዛዙ በመቶዎች የሚቆጠሩ በሚገባ የታጠቁ የደህንነት ሰራተኞችን አሰማራ። የደህንነት ሰራተኞቹ የደንብ ልብስ የለበሱም ያለበሱም ነበሩበት። 

በአንዳንድ ስፍራዎች የተቃውሞ ሰልፎቹ ተጀምረው ጥቂት ደቂቃዎች እንዳለፉ ከአካባቢያቸው ጋር የተመሳሰሉ ወታደሮች ከአብዮት ጥበቃ አባላት ጋር በመሆን ተኩስ ከፈቱ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ወደቁ። አንዳንድ ቤተሰቦች በአንዲት ቅጽበት ብቻ ሁለት ወይም ሶስት ልጆቻቸውን አጥተዋል። በዚያው ፍጅቱ በተፈፀመበት ዕለት ማታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሬሳዎች ወደ ዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ሬሳ ማቆያ ክፍል ተላኩ። … ታዳጊ የሆኑ ወጣቶች፣ ገና ሃያ ዓመት ያልደፈኑ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አረጋውያን፣ ፀጉራቸውን በአጭሩ የተቆረጡ፣ በወቅቱ አፍሮ የተባለ የፀጉር አቆራረጥና ሌሎችም ጉንጉን እየተባለ በሚጠራው ዓይነት ሐገራዊ የፀጉር አሰራር የተሰሩ ሴት ልጆች ሬሳ በየስፍራው ተዘርግቷል። አንዳንዶቹ ሱሪ ታጥቀዋል። ሌሎቹም ቀሚስ አጥልቀዋል።

አብዛኞቹ አስክሬኖቹ በጥይት ተበጣጥቀውና የአንዳንዶቹም ፊት ጨርሶ ስለተበላሸ ማንነታቸውን እንኳን ለመለየት ያስቸግር ነበር›› (የተሰመረበትን ልብ ይበሉ) (ያ ትውልድ ቅጽ ሶስት መፅሀፍ፤ ክፍሉ ታደሰ) 
ታህሳስ 26/1985-ኢህአዴግ
 ‹‹በ24/04/85 ማታ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ መሆናቸው በዜና ማሰራጫዎች እንደተሰማ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ወደ ኤርትራ ታዛቢዎችን ለመላክ የወሰኑትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ውይይት ጀመሩ። …የመጨረሻው የሰልፈኞች ረድፍ ከግቢው እንደወጣ ታጣቂ ኃይሎች ወዲያውኑ የዩኒቨርስቲውን በር ዘጉት። ወዲያውኑ ሰልፈኞቹን ከብበው የነበሩ የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች ተኩስ ከፈቱ። …ይበልጥ የሚዘገንነው ተራ ልብስ ለብሰው ተማሪ መስለው በዩኒቨርስቲው ውስጥ የተሰማሩት ታጣቂ ቡድኖች ነበሩ። 

በዚህም የተነሳ በጠመንጃ በሽጉጥ፣ በጩቤና በዱላ ሰላማዊ ተማሪዎች፣ ሴቶችና ዓይነ ስውራን ሳይቀሩ፣ በሚዘገንንና ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ ተጨፈጨፉ። በሥራቸው ምክንያት በግቢው ውስጥ የተገኙ ወንዶችና ሴቶች መምሕራን፣ ሌሎች ሰራተኞችም የጭካኔው ጭፍጨፋ ደርሶባቸዋል። ከዚህ በኋላ የተፈጸመው ደግሞ የጭካኔውን እቅድና ኢሰብዓዊ መሠረት ያመለክታል።
1. በከባድ ሁኔታ በጥይት፣ በጩቤና በዱላ ተደብድበው የተጎዱና በጣም የሚደሙ ወጣቶች የሕክምና እርዳታ ወደሚያገኙበት እንዳይወሰዱ ተከለከሉ።
 2. አምቡላንሶች ገብተው ቁስለኞቹን ወደ ሐኪም ቤት እንዳይወስዱ ታገዱ። 3. ከገቡም በኋላ ቁስለኞቹን ይዘው እንዳይወጡ ታገዱ። 
4. ተኩስ በተከፈተበትና አምቡላንሶች እንዲወጡ በተፈቀደበት መሀከል ቢያንስ የሁለት ሰዓቶች ያህል ልዩነት ነበረ።
…መንፈሱ ይህ ከሆነ መንግስት የተማሪዎቹን የሰላማዊ ሰልፍ እቅድ ገና ከውጥኑ ያውቀው ነበር። ግልጽ ማስረጃውም መንግስት ከባድ ኃይል አዘጋጅቶ መጠበቁ ነው። ዋናው ጥያቄም የሚነሳው እዚህ ላይ ነው። አንደኛ፤ ያ ተዘጋጅቶ ይጠብቅ የነበረው ኃይል ተማሪዎቹ ከዩኒቨርስቲው ግቢ እንዳይወጡ ለምን አላገዳቸውም ነበር?...›› (የተሰመረበትን ልብ ይበሉ) (በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባኤ /ኢሰመጉ/ የተማሪዎቹን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ካወጣው መግለጫ የተወሰደ) 1997 እና 1998-ኢህአዴግ ኢሰመጉ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 6 2005 ዓ.ም. ‹‹No Human Rights=No Democracy›› በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ‹‹በሰኔ ወር አጋማሽ መንግስት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው የአፈና እርምጃ ብዙዎች ሲገደሉ ከአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጐች ለእስር ተዳርገዋል›› ሲል በዛው ዓመት በጥር ወር ‹‹Human rights are not respected=There is no democracy›› በሚል ርዕስ ያወጣው መግለጫ ደግሞ ‹‹የመንግስት ሃይሎች ሰላማዊ ሰልፈኞቹን ለማስቆም ባደረጉት ሙከራ ሰላሳ አራት ሰዎች ተገድለው ስልሳ ሁለት የሚሆኑ ሲቆስሉ ሌሎች ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ዜጐች በተለያዩ ቦታዎች ለእስር ተዳርገዋል›› በማለት የወቅቱን ሁኔታ ያትታል።

ከዚህ በተጨማሪም በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ዘርዝሮ ኢህአዴግ እና ሰብዓዊ መብት እንደማይተዋወቁ መሞገት ይቻላል። ሆኖም የቦታ ውስንነት ስላለ የኦጋዴን፣ የሲዳማ፣ የጋምቤላ፣ የኦሮሚያ፣ የጎራፈርዳ እንዲሁም በልማት ስም ያለአንዳች ካሳ እና ምትክ ቤት የሚፈናቀሉ ዜጎችን እንደማሳያ ልንወስድ እንችላለን። የሆነ ሆኖ ከነገ በስቲያ የሚከበረው የ‹‹ግንቦት ሃያ›› 21ኛ አመት በነፃ ፕሬስ፣ በመድብለ ፓርቲ ስርዓት እና በሰብዓዊ መብት አያያዝ ሃያ አንድ አመት ወደኋላ ተጉዘን ከመሆኑም ባሻገር ህወሓት ‹‹በትግራይ ያለውን ጭቆና አስወግዳለሁ›› ሲል እንደተመሰረተው ሁሉ አብዛኛው የህወሓት መስራቾች ‹‹ህወሓት ጨቋኝ ነው›› ሲሉ ሌላ የትግራይ ህዝብን ከጭቆና ነፃ የሚያወጣ ድርጅት መስርተው፣ በትግል ላይ መሆናቸውን ስናይ ነው ህወሓትን እዚህ ለማድረስ የተሰዉት ሰማዕታት በሀገርም ሆነ በቤተሰቦቻቸው ዘንድ በዚህ በዓል በድል ሳይሆን በሀዘን እና በፀፀት ሊታወሱ ግድ ያለው።

‹‹ለህዝብ ጥቅም ሲባል…›› ኢህአዴግ እንደተቆጣጠረው የሰማነው የመንግስት ሚዲያም እንዲህ የአንድ ፓርቲ አገልጋይ መሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሌላ ችንካር ነው። እናም መለስ በ1983 ዓ.ም. የሰኔ ኮንፈረንስ አንገታቸውን በኩራት ቀና አድርገው በተስፋ የተሞላ ዲስኩር እንዳሰሙት ሁሉ በዚህ ዘመን ስለዛሬይቱም ሆነ የወደፊቷ ኢትዮጵያ አንገታቸውን ቀና አድርገው የሚናገሩበት ጀምበር እየጠለቀች ነው። ባለፈው ሳምንት በኃያላን ሀገራት መሪዎች ፊት ለፊት ሆነው ንግግራቸውን እያሰሙ ሳለ የመብረቅን ያህል አስደንጋጭ በሆነ ድምፅ እንዳቋረጣቸው ‹‹የነፃነት ድምፅ›› አይነት ብዙ ድምፆች ከየቦታቸው እየተሰሙ ነውና። ...ለዚህም መሰለኝ ‹‹እውነተኛው ግንቦት ሃያ ከወዴት ነህ?›› ሲል የሚጠይቅ የበዛው፡፡

Sunday, May 27, 2012

ትምህርት ቤቶች ከመደበኛው የመዘጊያ ዕለታቸው አንድ ወር ከ 15 ቀደም ብለው እንዲዘጉ ትዕዛዝ ተላለፈ

ኢሳት ዜና:-
መምህራን ለ ኢሳት እንደገለጹት፤በአዲስ አበባ እና በዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ የመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች የሁለተኛ መንፈቅ ትምህርት ክፍለ ጊዜን ከያዙት መርሃ- ግብር ቀደም ብለው እንዲያጠናቅቁና ትምህርት ቤቶቹ እንዲዘጉ ኢህአዴግ መመሪያ አውርዷል።

የኢህአዴግን ድንገተኛ ውሳኔ በመቃወም ከወረዳ እና ከዞን ትምህርት ቢሮዎች ጋር ለመነጋገር የሞከሩ ትምህርት ቤቶች ተቀባይነት አላገኙም ያሉን አንድ ርዕሰ መምህር ፣ ተማሪዎች በሁለተኛው መንፈቅ የትምህርት ጊዜ ሊሸፍኑት ይገባ የነበረውን የትምህርት መርሃ ግብር እንዲዘሉትና ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ ቦነስ ውጤት በአስቸኳይ ለተማሪዎች እየሰጡነ እንዲሸኟቸው መታዘዛቸውን ገልጸዋል፡፡

ከደመወዝ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ከኢህአዴግ መንግሥት ጋር ሆድና ጀርባ የሆኑት መምህራን ከወራት በፊት በመቱት የሥራ ማቆም አድማ የበቀል እርምጃ እየተወሰደባቸው እንዳለ ለዘጋቢያችን የተናገሩ አንድ የአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት መምህር ፤ የሥራ ማቆም አድማውን አስተባብራችኋል የተባሉ መምህራን እየተቀጡና ከሥራ እየተፈናቀሉ ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ መምህሩ ገለፃ ከመምህራኑ የሥራ ማቆም አድማ በኋላ በሁሉም ትምህርት ቤቶች አካባቢ በርካታ ፖሊሶች፣ ሲቪል ፖሊሶች እና የደህንነት ሠራተኞች ዘወትር በሥራ ሰዓት በብዛት መሰማራት ጀምረዋል።

“ ተራ የተማሪዎች ጸብ ሳይቀር በደህንነት ሠራተኞችና በሲቭል ፖሊሶች ክትትል ስለሚደረግበት ለተማሪዎቻችንና ለእራሳችንም ህይወት ጭምር ሰግተናል” ሲሉም  በየትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የሚታየው ውጥረት እየተባባሰ መሆኑን አመላክተዋል።

መንግስት የትምህርቱን መርሃ-ግብር ሳናጠናቅቅ ተማሪዎቻችንን እንድንበትን የፈለገበውም ፤ የተቃውሞው ሁኔታ ተማሪዎችን አካቶ ያገረሻል ከሚል ሥጋት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት በመምህራኑ ዘንድ  እንዳለ አክለው ገልጸዋል፡፡

በሌላ ዜና  የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር የአመራር ለውጥ አድርጓል።  ሰሞኑን በተደረገው ምርጫ ላይ የተሳተፉ የመምህራን ማህበር የትምህርተ ቤት ተወካዮች ለነባሩ አመራር የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበው እንደነበርም ታውቋል።

መምህራኑ መንግስት ባደረገው የእርከን ማሻሻያ፣ በመምህራን ላይ እየደረሰ ባለው ወከባ እና የተባረሩ መመህራንን ወደ ስራ በመመለስ በኩል እየተደረገ ባለው ትግል ማህበሩ ጥረት አላደረገም በማለት የተቃውሞው ንግግሮችን አድርገዋል።

በግንቦት 20 የሚነሱ ያልተመለሱ ጥያቄዎች

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ደርግን ከሥልጣን ያስወገደበትንና ሥልጣን የያዘበትን 21ኛ ዓመት በአንድ ላይ ነገ ያከብራል፡፡ ኢሕአዴግ ግንቦት ሃያን ባከበረ ቁጥር ‹‹የዘንድሮውን በዓል ለየት የሚያደርገው›› የሚል ቃላት በመጠቀም በዓሉን በጐ ከሚላቸው ሌሎች ክስተቶች ጋር ማያያዙ የተለመደ ነው፡፡ ነገ የሚከበረው የግንቦት ሃያ በዓልም የዓባይ ግድብ ግንባታ በተጀመረ ማግስት መከበሩ በዓሉን ለየት እንደሚያደርገው እየተገለጸ ነው፡፡

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ አገሪቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የዴሞክራሲ ዕድገት እየስመዘገበች መሆኗን መንግሥት ሲገልጽ፣ ገለልተኛና ተቃዋሚ ወገኖች በበኩላቸው ግንቦት 20 ያልመለሳቸው በርካታ የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡

በርካታ ችግሮች በሚታዩባትና በሚደመጡባት አንድ አገር ውስጥ አንድ ፓርቲ የሁሉንም ዜጐች ይሁንታ አግኝቶ ለሃያ አንድ ዓመት ማስተዳደር መቻሉ እንቆቅልሽ የሚሆንባቸው ታዛቢዎች፣ ኢሕአዴግ ለዚህን ያህል ጊዜ ሥልጣን ላይ የተቀመጠው ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዳይካሄድ የመወዳደሪያውን ሜዳ ያጠበበው በመሆኑ ነው ብለው ያምናሉ፡፡

ደርግን ከሥልጣን በማስወገድ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ያስጠበቀና የእኩልነት ጥያቄ መመለስ የቻለ መሆኑን የሚገልጸው ኢሕአዴግ በበኩሉ፣ በየጊዜው በሚካሄድ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሥልጣን መያዙን ይገልጻል፡፡ በተለይም ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት ማስመዝገቡን፣ በሒደትም ሕዝቡን ከድህነት አረንቋ እያወጣ መምጣቱን ገዢው ፓርቲ በልበ ሙሉነት ይገልጻል፡፡ በዴሞክራሲውም ረገድ መልካም አስተዳደርን በማስፈንና ሰብዓዊ መብትን በማስጠበቅ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውን ይጠቅሳል፡፡

የኢሕአዴግን ሃያ አንድ የሥልጣን ዓመታት የሚገመገሙ የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ እየሠራቸው ያሉ ሥራዎች በበጐ መልኩ የሚገለጹ ቢሆንም፣ አብዛኛው ኅብረተሰብ የኢኮኖሚ ዕድገቱ ተጠቃሚ አለመሆኑን ይገልጻሉ፡፡ የአገሪቱን የዴሞክራሲ ዕድገት ሲገመግሙም በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡ የዜጐች መብቶች ቀስ በቀስ በአዋጆች፣ በመመርያዎችና በደንቦች እየተሸረሸሩ መምጣታቸውን ያስረዳሉ፡፡ ሙስናም የሥርዓቱ ዓይነተኛ መገለጫ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

ሕወሓት/ኢሕአዴግ የትጥቅ ትግሉን ሲያካሂድ በነበረበት ወቅት ምን ዓይነት ዓላማዎችን አንግቦ ነበር? በ1983 ዓ.ም. ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የትኞቹን የሕዝብ ጥያቄዎች ለመመለስ ቻለ? በዴሞክራሲ ግንባታ፣ በሰብዓዊ መብት አጠባበቅ፣ በመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መበትን በተመለከተ ድርጅቱ በረሃ ወቅት በነበረበትና ከሃያ ዓመት በኋላ የያዘው አቋም ምንድን ነው? የሚሉት ጉዳዮች አሁንም በበርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ናቸው፡፡

የሕወሓት የተምታታ አስተሳሰብ
ኢሕአዴግ አገሪቱን ባስተዳደረባቸው ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡ መብቶች አልተከበሩም፣ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት እንዳይፈጠርም ገዢው ፓርቲ እንቅፋት ሆኗል የሚል እምነት ያላቸው ከሕወሓት አሥራ አንድ መሥራቾች አንዱ የሆኑት አቶ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ ችግሩን ሕወሓት ሲመሠረት ጀምሮ ከነበረው የተምታታ ርዕዮተ ዓለምና ከድርጅቱ የውስጥ ዴሞክራሲ ጋር ያያይዙታል፡፡

ሕወሓት ለትጥቅ ትግል ሲነሳ የትግራይ ሪፐብሊክን መገንባት የሚል የጠባብነት መንገድ መከተሉን የሚናገሩት አቶ አስገደ፣ በትጥቅ ትግሉ ወቅት በድርጅቱ የሚታዩትን ችግሮች በውስጥ ዴሞክራሲ የመፍታት ችግር እንደነበረም ያስታውሳሉ፡፡

‹‹ሕወሓት የተምታታ አስተሳሰብ ነበረው፤ በአንድ በኩል ማርክሲዝም ሌኒንዝም፣ ማኦኢዝም መመሪያችን ነው ይል ነበር፡፡ ቆየት ብሎ ደግሞ የማኦን አስተሳሰብ ተወና የስታሊንን አቋም ያዘ፡፡ የኮሙዩኒስት ሥርዓት ሲፈረካከስ ደግሞ ቀይ የኮሙዩኒስት ካባ ለብሰን ልንሄድ አንችልም አሁን የካፒታሊዝምን ካባ ለብሰን ቀስ በቀስ ዓላማችንን ማሳካት እንችላለን፤›› በማለት ሕወሓት በየጊዜው አቋሙን ይቀያይር እንደነበር የሚናገሩት እኚሁ አንጋፋው የሕወሓት ታጋይ፣ በወቅቱ የነበረው የሕወሓት አስተሳሰብ ከሕወሓት አስተሳሰብ ውጪ የነበሩ ኢሕአፓን የመሳሰሉ ኃይሎች ከትግራይ እንዲወጡ ያደረገ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ይነሱ የነበሩ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎችንም በውይይት ከመፍታት ይልቅ ሌላ ትርጉም በመስጠት በኃይል ይፈታ እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት የትግራይ ሪፐብሊክን ለመመሥረት ለአሥራ አምስት ዓመታት ያህል ሲታገል የነበረው ሕወሓት ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል ድረስ፣ የዜጐች አጠቃላይ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይጠበቁ›› የሚሉ ዓላማዎችን አንግቦ ሲንቀሳቀስ የቆየ ቢሆንም፣ ማሌሊት በ1977 እስከተመሠረተበት ጊዜ ድረስ ‹‹የትግራይ ሪፐብሊካን መገንባት›› የሚለው አስተሳሰብ ስህተት ነበር የሚል ጉዳይ በኮንፈረንስም ሆነ በሕወሓት ልሳኖች ተነስቶ አያውቅም ነበር፡፡ ማሌሊት በተመሠረተበት ጊዜም ‹‹የጠባብነት ዝንባሌ ነበር›› ተብሎ ነው የታለፈው፡፡

በሽግግር መንግሥቱ ማግስት
በ1983 ዓ.ም. ደርግን የገረሰሰው ኢሕአዴግ ‹‹ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች የተሳተፉበት የሽግግር መንግሥት መሥርቻለሁ›› የሚለውን የገዢውን ፓርቲ ሐሳብ አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ባይቀበሉትም፣ የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በ1987 ዓ.ም. ከፀደቀ በኋላ በተወሰነ ደረጃ ዜጐች ሕገ መንግሥቱ የሚፈቅድላቸውን መብት ማጣጣም ጀምረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ በወቅቱ የወጡትን አዋጆች መሠረት በማድረግም በርካታ የፕሬስ ውጤቶች ይታተሙ ነበር፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ፈቃድ ተሰጥቷቸው መንቀሳቀስ መጀመራቸው በበጐ ጐኑ የሚገለጽ ተግባር ነበር፡፡ የኢሕአዴግ ተፎካካሪ እንሆናለን ብለው የተመሠረቱት እነኚህ ፓርቲዎች ግን ብዙም ሳይቆዩ እየተጠናከሩ በመሄድ ፋንታ እየተዳከሙ መጡ፡፡

አቶ አስገደ እንደሚሉት ብዙኅን ፓርቲዎች እየተፈለፈሉ በሄዱ ቁጥር ስጋት ያደረበት ኢሕአዴግ በየክልሎቹ በኢሕአዴግ ሳንባ የሚተነፈሱ ፓርቲዎች መመሥረት ጀመረ፡፡ ለመአሕድ - ብአዴን፣ ለኦነግ - ኦሕዴድ የፈጠረው ኢሕአዴግ ተቀናቃኞቹን እያፈነ እንቅስቃሴያቸውን በማጥበብ ተቀባይነት እንዳያገኙ አደረጋቸው፡፡ ‹‹በጋዜጠኞች ላይ በሚመሠረት ክስና የእስር ቅጣት ምክንያትም ከስልሳና ከሰባ በላይ የነበሩ ጋዜጦች ቀስ በቀስ እየከሰሙ መጡ፤ የነፃ ፕሬስ ነፃነት ጠፋ፤ የሰብዓዊ መብት ጥበቃም ተጣሰ፤›› ይላሉ፡፡

የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ አስተሳሰብ ብቻ በኢትዮጵያ እንዲኖር በአሁኑ ጊዜ በገጠርና በከተማ አንድ ለአምስት የሚል አደረጃጀት ኢሕአዴግ እየተገበረ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አስገደ፣ ግንቦት 20 ይዞት የመጣው ሙስና፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ብልሹ አስተዳደር ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡

‹‹የትምህርት ነፃነት የሚባል ነገር የለም፡፡ አንድ አስተማሪ የሚለካው በሙያው ሳይሆን የሕወሓት/ኢሕአዴግ አባል በመሆኑ ነው፡፡ ግንቦት 20 ሲከበር የሕግ የበላይነት አልመጣም፡፡ የሕግ ባለሙያዎች የማይከበሩባት፣ ሕግ ተምረው ሌላ ሥልጠና እንዲወስዱ የሚደረጉባት አገር ናት፤›› የሚሉት አቶ አስገደ፣ አምስት ዓመት ተምሮ የወጣን አንድ የሕግ ምሁር በየክልሉ የሁለት ዓመት ሥልጠና በመስጠት የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አስተሳሰብ እንዲጠመቅ በሚደረግበት ሁኔታ ፍትሕ ይኖራል ብሎ መገመት እንደሚያስቸግር ይናገራሉ፡፡ በኢኮኖሚ ረገድም ኑሮ ውድነት ከአቅም በላይ በመሆኑ በልቶ የሚያድር ሕዝብ በጣም አነስተኛ መሆኑን፣ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቆ የወጣው ባለሙያም ለእሱ የሚመጥን ፕሮጀክቶች ስላልተከፈቱለት ለሥራ አጥነት መዳረጉን ይገልጻሉ፡፡

በኢሕአዴግና በደርግ መካከል ያለው ልዩነት ሲገልጹም፣ ‹‹ደርግ በግልጽ ይገድላል፡፡ ኢሕአዴግ ግን በጣም አደገኛ ነው፡፡ በአየር ላይ ዴሞክራሲ አለ በማለት በቴሌቪዥን ሕዝቡን ያደነቁረዋል፡፡ ነገር ግን የፕሬስ ነፃነት ለይስሙላ ነው፣ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ለይስሙላ ነው፣ ምርጫ ለይስሙላ ነው፤›› ይላሉ፡፡

የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ ሙሼ ሰሙ በበኩላቸው፣ የኢሕአዴግ የ21 ዓመታት የሥልጣን ዘመን ያመጣቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጦች በተለየ መልኩ ነው የሚቃኙት፡፡ ኢሕአዴግ በ1983 ደርግን ከሥልጣን ሲያስወግድ አገሪቱን በሥርዓቱ ተቀብሎ ለማስተዳደር የተዘጋጀ አካል ስላልነበረ እንደ አገር ፈርሳለች የሚል አመለካከት እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሙሼ፣ አገሪቱ እንደተፈራው ሳትፈራርስ አነሰም በዛ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ወጥቶ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት መተግበሩ በበጐነት የሚገለጽ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ኢሕአዴግ በትጥቅ ትግል አሸንፎ እንጂ የሕዝብ ውክልና አግኝቶ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ሥልጣን አለመያዙ በወቅቱ የነበረ አንዱ መሠረታዊ ችግር መሆኑን የገለጹት አቶ ሙሼ፣ እንደ ጐበዝ አለቃ የተጠራሩት የሽግግር መንግሥቱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሲቀርፁ የዜጐችን ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላስገቡ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

‹‹በወቅቱ የተሻለ አቅም የነበረው ፓርቲ ኢሕአዴግ ነው፡፡ ለዚህም ነው የራሱን ፕሮግራም በሕገ መንግሥቱ እንዲካተት ያደረገው፡፡ የሌሎች ኃይሎች ውክልና አልነበረበትም፤›› ይላሉ፡፡

እርሳቸው እንደሚሉት ሕገ መንግሥቱ የተዘጋጀው ራሱን መልሶ ለመፈተሽ በሚያስችል መንገድ አይደለም፡፡ በመሆኑም ባለፉት 20 ዓመታት ሲደረግ የነበረው ጥረት ሕገ መንግሥቱ የሚፈቅዳቸውን መብቶች ለማግኘት የሚደረግ እንጂ፣ በሕገ መንግሥቱ እንዲሻሻሉ የሚፈለጉ ጉዳዮችን እንዲሻሻሉ የሚችሉበትን መንገድ ለማስተካከል አልነበረም፡፡

‹‹ሕገ መነግሥቱን ማሻሻል ይቅርና በሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈሩ ነገሮችን እንኳን መተርጐም አልተቻለም፡፡ በፖሊሲ፣ በመመርያና በደንብ ተቀፍድደዋል፤ የፕሬስ ሕግና የሽብርተኝነት ሕግ ለዚህ ዓይነተኛ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ኢሕአዴግ ዴሞክራሲን በመተግበር ረገድ ኋላቀርና ቁርጠኝነት የጐደለው ነው፤›› በማለት የኢሕአዴግን የሃያ አንድ ዓመታት ጉዞ ይገልጹታል፡፡

ሕዝብ የሚፈልገው የመልካም አስተዳደር ጥያቄም ኢሕአዴግ ከሚከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ጋር እንደማይሄድ አቶ ሙሼ ይገልጻሉ፡፡ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ የአገር ጥቅምንና የብዙኅንን ጥቅም ለማስጠበቅ በሚል የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት የሚያበረታታ ርዕዮተ ዓለም መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሙሼ፣ ገዢው ፓርቲ በሕዝብ ጥቅምና በልማት ስም የዜጐችን መብት እንዲጥስ በር እንደተከፈለት ያስረዳሉ፡፡

‹‹ሰዎች ከልማት ውጪ ሌላ ነገር የላቸውም? ዳቦ ከመብላት ውጪ ብዙ ሊሟሉላቸው የሚፈልጉት ነገር አለ፡፡ የኢሕአዴግ አካሄድ የግለሰቦችን መብት የሚጥስና ወደ መንጠቅ የሚያመራ ነው፤›› ይላሉ፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመንግሥት ሚዲያ ቀርበው በሚፈልጉት አጀንዳ ላይ ሐሳባቸውን እንዳይገልጹ መደረጉም ሌላው ችግር መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ኢሕአዴግ ለራሱ ወቅታዊ ጉዳይ ሲል ተቃዋሚ ፓርቲዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲሳተፉ ማድረጉ ለተቃዋሚዎች የሚዲያ ዕድልን ሰጥቷል ሊያስብለው እንደማይችል የሚናገሩት አቶ ሙሼ፣ ከሃያ አንድ ዓመት በኋላም ዴሞክራሲ በእንጭጭ ደረጃ የሚገኝ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

ኢኮኖሚውስ አድጓል?
አቶ ሙሼ እንደሚሉት በኢኮኖሚው ረገድ በጐ የሚባሉ እንቅስቃሴዎች ታይተዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ አመርቂ ሥራዎችን መሥራቱን የሚናገሩት የኢዴፓው ሊቀመንበር መንግሥት በመንገድ ግንባታ፣ በትምህርት፣ በቴሌኮሙኒኬሽንና በጤናው ዘርፍ እየሠራው ያለው ሥራ በበጐነቱ የሚጠቀስ ቢሆንም፣ የአንድ አገር ኢኮኖሚ በመሠረተ ልማት መስፋፋት ብቻ ሊገለጽ እንደማይቻል ያስረዳሉ፡፡

‹‹ይህች አገር ምርታማነቷን ልታረጋግጥ የምትችልበት ሁኔታ መኖር አለበት፤ አቅርቦት ዝቅተኛ ከሆነ ግሽበት ስለሚመታ በዚህ በኩል መንግሥት እየሠራ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ኢኮኖሚ ደረጃ ለማምጣት የአቅርቦት ኢኮኖሚው በውድድር ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል፤›› የሚሉት አቶ ሙሼ፣ በአሁኑ ጊዜ ሥልጣን ላይ ያለው ኢሕአዴግ በሚከተለው ሶሻሊስታዊ አመለካከቱ የሚፈልገውን ወገንና የኢኮኖሚ ሴክተር ለይቶ በማውጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉ የሚፈለገውን የኢኮኖሚ ዕድገት ሊያስገኝ አለመቻሉን ይገልጻሉ፡፡ መንግሥት ብዙ ድምፅ አለው ብሎ ለሚያስበው አርሶ አደሩና በአነስተኛና ጥቃቅን ዘርፍ ለተሰማራው የኅብረተሰብ ክፍል የሚሰጠው የተለየ ድጋፍ ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ መሆኑንም ይገልጻሉ፡፡

‹‹ተገቢ ያልሆነ ተፅዕኖ በማድረግ አንዱን ማኅበረሰብ ለመጥቀም ሌላኛውን ማኅበረሰብ መጐዳት የለበትም፤›› ሲሉ ኢሕአዴግን ይተቻሉ፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን ትችቶች ግን ኢሕአዴግ አይቀበላቸውም፡፡ ባለፈው ረቡዕ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄድት የኢሕአዴግ የሕዝብና የውጭ ግንኙነት መምርያ ኃላፊ አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው፣ በትጥቅ ትግሉ የተሰው ሰማዕታት ኢሕአዴግ ባለፉት 21 ዓመታት የሠራቸውን ሥራዎች ቀና ብለው የማየት ዕድል ቢያገኙ ይደሰታሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ ሴኮቱሬ ገለጻ፣ በአገሪቱ ዴሞክራሲ ሰፍኖ ዜጐች የፈለጉትን አስተሳሰብ በነፃ የማራመድ መበት ተረጋግጦ፣ የተለያዩ ጋዜጦች በየመንገዱ የሚነበቡበትና ሐሳቦች በነፃነት የሚንሸራሸሩበት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተደራጅተው አለን የሚሉት ሐሳብ በነፃነት የሚስተናገድበት ሥርዓት በመፈጠሩ ለነፃነት ሲታገሉ የተሰው ሰማዕታት የተገኘውን ለውጥ የማየት ዕድል ቢያገኙ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡

ኢሕአዴግ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ ሌሎች በትጥቅ ትግል ያሸነፉ የፖለቲካ ኃይሎች እንደሚያደርጉት እኔ አሸናፊ ነኝ በማለት ሥልጣን ለብቻው ከመያዝ ይልቅ፣ የፖለቲካ ኃይሎችን አሰባስቦ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ማድረጉ ሊደርስ የሚችለውን ችግር ማስቀረቱን የሚገልጹት አቶ ሴኮቱሬ፣ ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት የተካሄዱት አገሪቱን ከድህነት የማውጣት፣ የሰብዓዊ መብቶችና የዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማጠናከር የወተሰዱ የፖሊሲ ዕርምጃዎች ነገሮች ቀስ በቀስ እንዲለወጡ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ እርሳቸውም እንደ አቶ አስገደ ሁሉ ሕወሓት/ኢሕአዴግ የተምታታ አስተሳሰብ የነበረው መሆኑን አልደበቁም፡፡ ‹‹[1983 ዓ.ም.] ዘመኑ ኮሙዩኒዝም እየወደቀ ካፒታሊዝም እየገነነ የመጣበት ወቅት ነበር፡፡ ከዚህም በላይ ካፒታሊዝም ብቸኛ አማራጭ ተደርጐ የሚወሰድበት ዘመን ነበር፡፡ የእኛ አመጣጥ ከኮሙዩኒዝም ሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለም በመሆኑ፣ ይህን የሚከተሉ በውስጣችን የነበሩበትና ከዚህም አልፎ አደረጃጀት የነበረበት ሁኔታ ነበር የነበረው፡፡ በዚህም የተነሳ የአስተሳሰብ ጥራት ላይ ችግር ነበረብን፤›› ብለዋል፡፡

ኢሕአዴግ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ አገሪቱ በፈጣን የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ውስጥ ብትገኝም ድህነትና ኋላቀርነት፣ የኑሮ ውድነት፣ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚታየው በአቋራጭ የመክበር አስተሳሰብና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሥርዓቱን የሚፈታተኑ ፈተናዎች መሆኑን አምኗል፡፡ እነዚህ ችግሮች ዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደር በማስፈን እንደሚፈቱ ፅኑ እምነት እንዳለው የገለጸው ኢሕአዴግ፣ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ትኩረት ሰጥቶ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

ኢሕአዴግ የፖለቲካ ሥነ ምኅዳሩን በማጥበብና የተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ በማወክ ይተቻል፡፡ ተቃውሞ ማሰማት ወንጀል እየሆነ ነው የሚሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ ሰላማዊ ትግሉን እየኮላሸው ነው ይላሉ፡፡ ኢሕአዴግ ደግሞ ሕገ መንግሥቱን አክብረው የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለማስተዋወቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍ በዚሁ መግለጫው አስታውቋል፡፡ በጋራ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አማካይነት የተጀመረውን ምክክር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

የኢሕአዴግ ያለፉት 21 ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በርካታ ውጣ ውረዶች የታዩበት ሲሆን፣ ኢሕአዴግ እየተፈተነ ያለው ልማትን በማምጣት ብቻ ሳይሆን ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብትን ማስከበር ባለመቻሉ ነው እየተባለም ነው፡፡ የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥማት ለማርካት ብዙ መሥራት ይጠበቅብኛል ብሎ ቃል ቢገባም፣ ከዚህ በፊት የገባኸውን ቃል አላከበርክም ብለው የሚወቅሱት በርካቶች ናቸው፡፡ ኢሕአዴግ ሃያ አንደኛ ዓመት የሥልጣን በዓሉን ሲያከብር ያልተመለሱ በርካታ ጥያቄዎችን እያሰበ መሆን አለበት የሚሉም እንዲሁ ይበዛሉ፡፡   
 
  Source: Ethiopian reporter

Saturday, May 26, 2012

ልምሰል የሞላለት

















ልምሰል የሞላለት
አዎ "ልምሰል የሞላለት ! "
በልቸ ጠጥቸ ስለኖርኩ በድሎት i
መብቴ ተገፎ አጥቼ ነጻነት ፤
በስደት ሃበሳ ስኖር ስንከራተት፤
የደላኝ ይመስላል ! አኗኗሬን ሲቃኙት፤
የደላኝ ይመስላል ! ተክለ ቁመናየን መላብሴን ሲያዩት፤
የደላኝ ይመስላል! ስናገር ሲያደምጡኝ የምኖር በስኬት !
ታዲያሳ. . . !
በአደባባይ ልሳቅ ከቶ ምን አለበት ፤
በደስታ ልምነሽነሽ ልምሰል የሞላለት ፤
ኑሮ ግብግቡን አስተውለው ሲያዩት፤
ድብብቆሽ ኑሮ፤ አለፋውን ስቅየት ፤
የመንገዱን ርቀት ፤ የሰው ልጅን ክፋት፤
ሲታዘቡት ውለው ሲያሰላስሉ ቢያድሩት፤
ምስለኔያችን ከፍቶ ሲደሰኩት ኩሸት፤
ሰብዕና ጠፍቶ ሰው ሁሉ ሲራኮት፤
ወገኔ ዝም ብሏል ቤቱ እስኪደርስበት፤
ደፋር ይናገራል እሱ ምናለበት ፤
"
እድል እጣቸው ነው የተፈጠሩበት"
"
ለምን መጡ" ይላል መድገፉ ጠፍቶት፤
ይለናል ጎረምሳው መደገፉ ጠፍቶት ፤
ድምጽ ማሰማቱ ፤ውሃ ማቅረብ ገዶት ፤
እናም. . .
ስላየሁ በአይኖቸ ይህን መሳይ ትንግርት፤
ስላየሁ ህይዎቱን የዳፋ ቀማሹ የመሪሩን ስደት፤
ያስታግሰው እንደሁ የንዳድ ቃጠሎ የብሽቀቴን ብርታት፤
ድብቅ ሽሽግ ብየ . . .ሲለኝ አለቅሳለሁ ለመረረው ህይዎት፤
አዎ … እውነት ብለሃል ወንድም አደም
ይህ ነው የእውነቱ ገጽታ የዚህች አለም . . .
"
በጨለውማ ተስፋ ፤ጥርሴ ጧፍ ከሆነ ፤
የህይዎቴን ግርዶሽ ገላልጦት ካደረ፤
ምናለ ልሳቀው ባንች ሆየ ቅኝት ፤
ልንከትከት በዜማ ልምሰል የሞላለት !"
                     ©  ©  ©
        ወዳጀ አደም ሁሴን ዘራፍ አስባልከኝ እኮ ፡) ! ግጥም ደስ ይላል . . . የላክልኝ ግጥም ውስጤን ነካችውና ከተጋደምኩበት ይህችኑ ቋጠርኩልህ ! ስንኝ መገጣጠሙን በትክክል አሳክቸዋለሁ ባልልም ስሜቴን ካስረዳልኝ ይበቃል! ገጣሚ አይደለሁ እንዳንተ ! ለሁሉም ይህችም ላንተ ትሆን ዘንድ ፈቅጃለሁ !
ነቢዩ ሲራክ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መቀጠሉን ገለጠ

ኢሳት ዜና:-
አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የ2012 አዲስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ረገጣዎች በዝርዝር አቅርቧል። 

በአረቡ አለም የታየውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የመለስ መንግስት አምና በመጋቢት እና በሚያዚያ ወራት 250 የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ እና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አባላት መታሰራቸውን፣ በሰኔ ወር ደግሞ ውብሸት ታየ፣ ርእዮት አለሙመ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሄርና ደጄኔ ተፈራ መታሰራቸውን ገልጧል።

በሀምሌ ወር የስዊድን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብየና ጆሀን ፔርሰን ፣ በነሀሴና መስከረም ደግሞ በቀለ ገርባና ኦልባና ሊሌሳ ፣ አንዱአለም አራጌ፣ እስክንድር ነጋና ሌሎችም መታሰራቸውን ገልጠዋል።  በህዳር ወር 107 የተቃዋሚ ደርጅቶች መሪዎችና ጋዜጠኞች በሽብርተኝነት መከሰሳቸውን እንዲሁም አልጀዚራ፣ የአሜሪካ ድምጽ፣ ኢሳት ቴሌቪዥን፣ አዲስ ነገርና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዌብሳይት መታፈናቸውን ድርጅቱ ገልጧል።

በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድብደባ እና እንግልት በዝርዝር አብራርቷል። በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በሶማሊያ፣ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ያለፍላጎታቸው መፈናቀላቸውን አትቷል።

አምነስቲ በዚህ አመት ሪፖርቱ የምእራባዊያን መንግስታትን ክፉኛ ወቅሷል፡፡ የምእራባዊያን መንግስታት   በተለያዩ አገራት ሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ አይተው እንዳላዩ ሆነው ማለፋቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲጨምር እንዳደረገው ጠቅሷል።

በአዲስ አበባ አትክልት ተራ ፤ፖሊሶች ከነጋዴዎች እና ከነዋሪዎች ጋር ተጋጩ

ኢሳት ዜና:-
ትናንት ፣ መጋቢት 16፣ 2004ዓም በአትክልት ተራ ፖሊሶች አንድ አትክልት ሻጭን መደብደባቸውን ተከትሎ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ በማሰማቸው ፖሊሶች ወደ ሀይል እርምጃ አምርተዋል።

በተከራይ እና አከራይ  መካከል የተነሳን ውዝግብ ሳቢያ  በጉሊት ሽያጭ የሚተዳደር ሰኢድ ኡመካ የተባለ ወጣት በፖሊሶች በመደብደቡ፤ የአፍሪካ አንድነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞአቸውን በጩኸት አሰምተዋል። 

ጩኸቱ ወደተካረረ ፍጥጫ አምርቶ ግጭት ማስከተሉን የገለጹት የዜናው ምንጮች፤ ነዋሪዎች ከፖሊሶች ጋር በፈጠሩት በዚሁ ግብግብ ፖሊሶችን ጨምሮ የአካባቢው ነጋዴዎች እና ሸማቾች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ከ15 ያላነሱ ሰዎችም ለእስር እንደተዳረጉ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በመርካቶ በንግድ ሥራ ውስጥ ከተሰማሩት ወገኖች መካከል 75 በመቶ ያህሉ ሕገወጥ ናቸው በሚል አዲስ ዘመቻ ለመክፈት መዘጋጀቱን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ባለሥልጣኑ በጥናት ደርሼበታለሁ ባለው መሰረት በመርካቶ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩ ነጋዴዎች ቁጥር 25 በመቶ ብቻ ሲሆኑ የተቀሩት 75 በመቶ ያህሉ ንግድ ፈቃድ የሌላቸውና ግብርም የማይከፍሉ ናቸው ብሏል፡፡

ጥናቱ አያይዞም በሃገሪቱ ካለው አጠቃላይ የገንዘብ ልውውጥ ግማሸ ያህሉን የሚይዘው የመርካቶ አካባቢ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ ከዚሁ ጥናት ጋር በተያያዘም ባለሥልጣኑ “የመርካቶ ፕሮጀክት” በሚል በመርካቶ አካባቢ ሁለት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና አሰር የታክስ ማዕከላትን ከፍቷል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የተጠየቁ አንድ በመርካቶ አካባቢ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ እንደተናገሩት በአካባቢው ንግድ ፈቃድ አላወጡም የሚባሉት መንገድ ላይ ከፖሊስ ጋር ግብግብ ገጥመው የእለት ግርሳቸውን የሚሸፍኑ አነስተኛና ጥቃቅን ነጋዴዎች ሁሉ ተቆጥረው መሆኑን አስታውሰው እነዚህ ወገኖች ግብር ክፈሉ ብሎ ማሳደድ ደሃው ሕዝብ ትንሸ ነገር ሰርቶ እንኳን እንዳያድር ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም በማለት የባለስልጣኑን እርምጃ ተቃውመዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ባለፈው ዓመት ከ51 ቢሊየን ብር በላይ ግብር መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ዘንድሮ 76 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ቢያቅድም ባለፉት አስር ወራት ብቻ መሰብሰብ የቻለው 59 ቢሊየን ብር ገደማ መሆኑ ጋር ሲነጻጸር በቀሪ ሁለት ወራት ዕቅዱን የማሳካቱ ነገር ጥያቄ ምልክት ውስጥ ያለ ነው፡፡የመርካቶ ፕሮጀክት የባለሥልጣኑን እጅግ የተጋነነ የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ሊጠቅመው ይችላል ተብሏል::

ባለሥልጣነ  አምና በደረጃ “ሐ” ሥር ያሉ አነስተኛ ነጋዴዎችን በተመለከተ አጠናሁት ባለው ጥናት መሰረት ደረጃቸውን በድንገት በማሳደጉ አነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ላይ የተሰማሩ ወገኖች ጭምር በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ግብር እንዲከፍሉ መጠየቃቸው ከፍተኛ ተቃውሞን ቀስቅሶበት እንደነበር ያታወሳል፡፡

በተጨማሪም አምስት ሺ ብር የማይሞላ ካፒታል ያላቸው ወገኖች ጭምር ካሸ ሬጅስተር የተባለውን ማሸን ከብር ስምንት ሺ በላይ አውጥተው እንዲገዙ መጠየቃቸውም እንዲሁ ተመሳሳይ ተቃውሞን አስነስቶበት ነበር፡፡ባለሥልጣኑ ገቢን ለማሳደግ ብቻ የያዘው ሩጫ ከበርካታ ነጋዴዎች ጋር እያላተመው እንደሚገኝም ይታወቃል፡፡

Friday, May 25, 2012

VOA Reporter Detained in Ethiopia

A Voice of America reporter has been detained in the Ethiopian capital while trying to cover a demonstration Friday. Witnesses to the arrest said that reporter Peter Heinlein and his translator Simegineh Yekoye were detained while seeking to interview protesters during a Muslim demonstration following Friday prayers in Addis Ababa.
Another Western reporter said there was a heavy police presence at the demonstration and that he also was stopped by police and told to leave the area. 
Tom Rhodes, East Africa spokesman for the Committee to Protect Journalists (CPJ), said he understood that Heinlein was accused of acting "unprofessionally and illegally." Rhodes said a government spokesman accused Heinlein, who is married to a Danish diplomat, of improperly using a diplomatic vehicle and refusing to show media accreditation.

Rhodes added that the accusations seemed at odds with Heinlein's reputation as a highly professional journalist who has worked for VOA since 1988."However, I would add that Peter Heinlein is a veteran reporter, an experienced and professional broadcaster, so personally I find it rather hard to believe that someone like Heinlein would be reporting unprofessionally," Rhodes said.

In a formal statement from its headquarters in Washington, VOA said, "The safety and welfare of our reporters is our utmost concern and we are working to gather more information about Mr. Heinlein’s status." The statement said VOA is in touch with the U.S. Department of State seeking more information and that it is urging "Ethiopian authorities to allow Mr. Heinlein to carry out his journalistic responsibilities without interference.”
Heinlein reported last week on rising tensions between the government and Ethiopia's Muslim minority, which has held a series of demonstrations to protest what the community sees as government interference in Islamic affairs. The CPJ quoted Minister of Government Communications Bereket Simon saying officials wanted to speak to Heinlein about his "unobjective" reporting on the Muslim issue. Bereket did not say whether Heinlein has been formally arrested or charged.

Thursday, May 24, 2012

በጋምቤላና በቤንሻንጉል የፀጥታና የማስፈጸም ችግሮች ለፕሮጀክቶች እንቅፋት ሆነዋል

By Ethiopian Reporter
በአቶ አዲሱ ለገሰ የሚመራው የፌዴራል መንግሥት ልዑካን ቡድን በጋምቤላና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ባካሄደው የመስክ ግምገማ፣ የመንደር ማሰባሰብ ሥራዎች ችግር እየገጠማቸው መሆኑን አረጋገጠ፡፡ 

አቶ አዲሱና የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ በርኸ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ድረስ በሁለቱ ክልሎች ስብሰባዎችንና የመስክ ጉብኝቶችን አካሂዶ ባለፈው እሑድ ተመልሷል፡፡

በዚህ ወቅት በቤንሻንጉል ክልል በዋናነት ፕሮጀክቶችን በማስፈጸም በኩል ደካማ የሥራ አፈጻጸም ሲያሳይ፣ በጋምቤላ ክልል ደግሞ ቀደም ሲል የተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ ፕሮጀክቶች የተፈለገውን ያህል መራመድ እንዳይቻሉ ማድረጉ ተጠቅሷል፡፡ የፌዴራል መንግሥት በ2004 ዓ.ም. የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች እንዲሳኩ ለማድረግ ለሁሉም  ለክልሎች የሚከፋፈል 15 ቢሊዮን ብር መድቧል፡፡ 

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 294 ሚሊዮን ብር ሲደርሰው፣ በዚህ ገንዘብ በዋናነት ተበታትነው የሚገኙ የክልሉን ነዋሪዎች በመንደር ማሰባሰብ፣ ውኃ፣ ጤናና የትምህርት ተቋማትን የማሟላት ሥራ የመሥራት ዕቅድ ተይዟል፡፡ ነገር ግን የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ አንድ ወር ብቻ እየቀረው ክልሉ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ የተጠቀመው ከ30 በመቶ እንደማይበልጥ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ባምባሲ አካባቢ በሚገኘው በጀማፃና በጋሪቡ መተማ አካባቢ የሚካሄደውን የመንደር መሰባሰብና የመስኖ ፕሮጀክቶች ከጎበኘ በኋላ የሥራ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆኑን ደምድሟል፡፡

የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ አህመድ ናስርን ጨምሮ የክልሉ ሴክተር መሥርያ ቤቶች በተገኙበት በአሶሳ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ክልሉ ደካማ አፈጻጸም ማሳየቱ ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዕድገት ወደኋላ የቀሩ ክልሎችን እንዲደግፉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ የተሰጣቸው የትምህርት ሚኒስቴር፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መሥርያ ቤቶች የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንዳልሰጡ መጠቆሙን መረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ ስብሰባ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ያለፉት ስህተቶች ታርመውና ሥራው ተካክሶ እንዲሠራ መመርያ ተሰጥቷል፡፡

በጋምቤላ ክልል ኦደግሞ የኦቦቦ መንደር ማሰባሰብና የላሬ ወረዳ መንደር ማሰባሰብ ሥራዎች ተጎብኝተዋል፡፡ በእነዚህ ጣቢያዎች የማስፈጸም አቅም ማነስ ቢኖርም፣ ለሥራው አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን ዋነኛው ተጠቃሽ ምክንያት የሆነው በ2004 ዓ.ም. በክልሉ ውስጥ የተፈጸሙ ሁለት ግድያዎች ናቸው፡፡ በርካታ ሰዎች ያለቁባቸው እነዚህ ግድያዎች የክልሉ አስፈጻሚ መሥርያ ቤቶች በሚፈልጉት ፍጥነት ሥራቸው ላይ እንዳያተኩሩ አድርገዋል ተብሏል፡፡

“የፀጥታ መደፍረስ አጋጥሟል” ሲሉ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጋት ሉዎክ የሥራ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ የሆነበትን ምክንያት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የፀጥታ ችግር በማጋጠሙ የክልሉ ባለሥልጣናት አብዛኛው ጊዜያቸውን በዚሁ ጉዳይ ላይ አጥፍተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ክልሉ በጠየቀው መሠረት የፌዴራል መንግሥት ዘርፈ ብዙ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አቶ ጋት ሉዎክ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

መንግሥት በ2007 ዓ.ም. የሚጠናቀቀውን የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦችን ለማሳካት ዕቅድ መንደፉ ይታወሳል፡፡ ዕቅዱን ለማስፈጸም ከተያዙ አቅጣጫዎች መካከል በዕድገት ወደኋላ የቀሩ ክልሎች መሠረት ልማትን ለማሟላት አመቺ ባለመሆኑ ነዋሪዎች ተሰባስበው በመንደር እንዲቋቋሙ ማድረግ አማራጭ ሆኗል፡፡

 በዚህም ውኃ፣ ትምህርት፣ ጤናና የመንገድ መሠረተ ልማት ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡  አቶ አዲሱ በዕድገት ወደኋላ የቀሩ ክልሎችን ለመደገፍ የተቋቋመውን ቦርድ የሚመሩ ሲሆን፣ አቶ ፀጋዬ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ ናቸው፡፡

የአንድ ለአምስት ፖለቲካዊ አደረጃጀት ወደ መንግስት መ/ቤቶች እየዘለቀ ነው

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፌዴራል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞቹን አንድ ለአምስት በሚል አደረጃጀት በማዋቀር በሥራ ሰዓት ጭምር ስብሰባዎችን በማካሄድ ሠራተኛው እርስ በርስ እንዳይተማመን የማድረግ አሠራር ተግባራዊ በማድረጉ በሥራ ዋስትናቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡን አንዳንድ ሠራተኞች አስታውቀዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የልማት ሠራዊት ለመገንባት በሚል ሠራተኛው አንድ ለአምስት እንዲደራጅና በየዕለቱ ከ30 ደቂቃ ላላነሰ ግዜ በቀኑ ውስጥ ባጋጠሙ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በሚል ሰበብ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ሰማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሠራተኞች ተናግረዋል፡፡

በስብሰባዎቹ ላይ ለየት ያለ ኀሳብ ማቅረብ እንደማይቻል፣ከቀረበም “የአመለካከት ችግር አለብህ ወይም አለብሽ” የሚል ዛቻና ማሸማቀቅ የተለመደ ክስተት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ሠራተኞቹ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ አገራችንን በሙያችን ለማገልገል አስበን የተቀጠርን ቢሆንም ሳንወድ በግድ እንድንደራጅ ተደርጎ በየቀኑ የሚደረገው ስብሰባ ውጤት ለአለቆች የሚላክበት ሁኔታ መፈጠሩ የሥራ ዋስትናችንን አደጋ ላይ እንዲወድቅ ምክንያት ሆኗል ብለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ሰራተኞች ከተጠረጠሩ የማባረረ ሥልጣን እንዳለው የጠቆሙት ሰራተኞቹ በአሁኑ ሰዓት ግን በፖለቲካ አመለካከት ብቻ ሰራተኞች ከሥራ የሚባረሩበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዚህ ዓመት ብቻ ከ300 በላይ ሰራተኞች መባረራቸውንም በምሳሌነት አንስተዋል፡፡

በአቶ ጁነዲን ሳዶ የሚመራው የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ይህን ዓይነቱ አሰራር“የልማት ሠራዊት ” በሚል ስያሜ የሚጠራው ሲሆን በሁሉም የመንግስት መ/ቤቶች ተግባራዊ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በ2002 ዓ.ም በተካሄደው አገራዊ ምርጫ ይህ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ኢህአዴግን የ99 በመቶ ባለድል ካደረገው ወዲህ አደረጃጀቱ ለምርጫ ብቻ ሳይሆን ለልማትም መጠቀም አለብን በሚል አደረጃጀቱ ወደ መንግስት መ/ቤቶች ለማውረድ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ኢህአዴግ የ2002ን ምርጫ ለማስፈጸም ባወጣው የስትራቴጂ ወረቀት ላይ ፡“ …ከኢትዮጽያ ሕዝብ ውስጥ ከግማሸ በላይ የሚሆነው ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች በመሆኑ የመራጩ ቁጥር ከ30 ሚሊየን በላይ ሊሆን እንደማይችል ይገመታል፡፡ከዚህ ውስጥ ቢያንስ አራት ሚሊየን ያህሉ የድርጅታችን አባል ነው፡፡

እያንዳንዱ አባል በቀላሉ ሊቀርባቸውና ሊያሳምናቸው የሚችል ቢያንስ አራት ወዳጆችና ዘመዶች አሉት ብንል እነዚህ ተደማምረው 20 ሚሊየን ይሆናሉ፡፡በእነዚህ ብቻ ቢያንስ 2/3 ኛውን ድምጽ ማግኘት ይቻላል…”ሲል የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ጠቀሜታ ገልጧል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በመንግስት መ/ቤቶች ለማስረጽ እየተሞከረ ያለው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት በሕዝብ ሐብትና ንብረት የኢህአዴግ ቀጣይ የምርጫ ድጋፍ ማሰባሰቢያ፣ አዳዲስ አባላትና ደጋፊዎችን የመመልመያ ስትራቴጂ እንጂ የልማት ጥማት አለመሆኑን አንዳንድ ወገኖች ከወዲሁ ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ኢህአዴግ በምርጫ 2002 በ99 ነጥብ 6 በመቶ ማሸነፉን መግለጹ በአለም አቀፍ ደረጃ መሳለቂያ እንዳደረገው ይታወሳል።

Wednesday, May 23, 2012

ሚኒስትሩን የዘለፈችው ሙስሊም ወጣት፤ በደህንነቶች በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ

ኢሳት ዜና:- ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩን ስብሰባ ላይ የዘለፈችው ሙስሊም ወጣት፤ በደህንነቶች በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ።ይህ አሳዛኝ ዜና ይፋ የሆነው፤የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ  አካል የሆነው “ድምፃችን ይሰማ” ኮሚቴ ፦አሳዛኝ የግፍ ዜና”በሚል ርዕስ ያሰራጨው መረጃ  ነው።

በቅርቡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሙስሊሞችን ጥያቄ በተመለከተ ከየክፍለ-ከተማው ሰዎችን በመምረጥ ስብሰባ አካሂዶ እንደነበር ያወሳው ኮሚቴው፤በዚሁ ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ክፍለ-ከተማ ሁለት ወንዶች እና ፍርዶስ የተባለች ወጣት  ሴት መሳተፋቸውን አመልክቷል።

ስብሰባውን ሲመሩ የነበሩት ሚኒስትሩ ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም  ብዙሀኑን ሙስሊም ያስተባብሩ ዘንድ በተመረጡት የኮሚቴ አባላት ላይ አስፀያፊ እና ድንበር ዘለል ንግግሮችን ሲደጋግሙ መደመጣቸውን የጠቀሰው ኮሚቴው፤የሰውዬውን ዘለፋና ስድብ መሸከም ያቃታት እህት ፍርዶስ የእልህ ሲቃ እየተናነቃት ሚኒስትሩን ዘልፋ የስብሰባ አዳራሹን ለቅቃ መውጣቷን አብራርቷል።

ከአዳራሹ ወጥታ በ አቅራቢያው ወዳቆመቻት ቶዮታ ቪትዝ የግል መኪናዋ በመግባት ወደመጣችበት ለመመለስ መንቀሳቀስ እንደጀመረች በሁለት ላንድክሩዘር መኪኖች የሞሉ ደህንነቶች ተከትለው በማስቆም እሷንም፤መኪናዋንም ይዘው መሰወራቸውን ኮሚቴው አጋልጧል። “ከዚያም እህታችን ፍርዶስን  በሚያሰቅቅ እና በሚዘገንን መልኩ በኤሌክትሪክ “ሾክ”እያደረጉ አቃጠሏት” ያለው ኮሚቴው፤በዚህም ምክንያት ወጣት ፍርዶስ ወዲያውኑ መናገርም፤መንቀሳቀስም ማቆሟን ገልጿል።

እንደ ድምፃችን ይሰማ መግለጫ፦ደህንነቶቹ በፍርዶስ ላይ የተጠቀሰውን የጭካኔ ድርጊት ከፈፀሙባት በሁዋላ  ከነ መኪናዋ መኖሪያ ቤቷ በሯ ላይ ጥለዋት ሄደዋል። በሁኔታው ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የወደቁት የፍርዶስ ቤተሰቦች ልጃቸውን ለመታደግ  ሩጫ መጀመራቸውን የጠቀሰው ኮሚቴው፤ሆኖም የደረሰባት ጉዳት እጅግ ከባድ በመሆኑ ጥራታቸው ሁሉ ከንቱ መቅረቱን ነው ያመለከተው።

በሆነው ነገር ልባቸው በሀዘን የደማው የፍርዶስ አባት  የልጃቸውን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ለህክምና  ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ይዘዋት ቢሄዱም፤ ደህንነቶቹ ባደረሱባት የኤሌክትሪክ ቃጠሎ በርካታ አካሎቿ ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ወጣት ፍርዶስ እስከወዲያኛው ተሰናብታለች። የከፋው አሳዛኝ ነገር  የወጣት ፍርዶስ ህይወት ማለፉን ተከትሎ ወላጅ እናቷ  በደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸው ነው ይላል ኮሚቴው።

ወላጅ እናቷን አፍነው የወሰዷቸውም የፈፀሙት አሰቃቂ ግፍ እንዳይሰማባቸው ለማድረግ በማሰብ ነው ብሎ እንደሚያምን የድምጻችን ይሰማ ኮሚቴ ገልጿል። መምህር የኔሰው ገብሬ ፦”ፍትህ በሌለበት አገር መኖር አልፈልግም”በማለት ራሱን ማቃጠሉን ተከትሎ የደህንነት አባሎች ፦”መረጃ እንዳትሰጥ”በሚል እህቱን በመኖሪያ ቤቷ አፍነው ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

ወጣት ፍርዶስ እሷን እና ጓደኞቿን  እላፊ እየተናገሯቸው የነበሩትን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩን በንዴት  በመዝለፏ ሳቢያ  በኤሌትሪክ ሾክ እየተደረገች እንድትሞት መደረጉን የሰሙ እትዮጵያውያን፤ሰሞኑን ጋዜጠኛ አበበ ገላው ፦ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን የተቃወማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለ ስብሰባ ላይ ቢሆን ኖሮ ምን ሊያደርጉት ይችሉ እንደነበር መገመቱ ቀላል ነው ብለዋል። 

ኢሳት የሟቹዋን ቤተሰቦች ለማነጋገር አደረገው ጥረት አልተሳካለትም። የኢትዮጵያ መንግስትም በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው አስተያየት የለም።