Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, September 4, 2012

አቶ ሀይለማርያም ግልገል ጊቤ ሦስት በታሰበው ጊዜ አይጠናቀቅም አሉ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በቀጣዮቹ ዓመታት የሀይል እጥረት ያጋጥማል የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለ ከአንድ ዓመት በሁዋላ ይጠናቀቃል ተብሎ እቅድ የተያዘለት የግልገል ጊቤ  ሀይል ማመንጫ ግንባታ በተባለው ጊዜ እንደማይጠናቀቅ  አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።

በመስከረም 2006 ዓ.ም. ይጠናቀቃል ተብሎ ዕቅድ የተያዘለት የግልገል ጊቤ ሦስት ኃይል ማመንጫ ግንባታ በወቅቱ እንደማይጠናቀቅ በመረጋገጡ፣ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ያስችላል የተባለ አዲስ ስትራቴጂ ተነደፈ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ይተካሉ ተብለው የሚጠበቁት  አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ እንደተናገሩት፣ ግልገል ጊቤ  ቁጥር ሦስት በመስከረም 2006 ዓ.ም. አይጠናቀቅም፡፡


በመሆኑም አገሪቱን ሊያጋጥማት የሚችለውን የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ስትራቴጂዎች መነደፋቸውን ጠቆሙት አቶ ሀይለማርያም፤ የመጀመርያው  ስትራቴጂ የስኳር ፋብሪካዎች ተረፈ ምርት የሆነው ሞላሰስ ወደ ኢነርጂ  ተለውጦ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ መስመር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ  ሲሆን፤ሁለተኛው ደግሞ ከአዲስ አበባ ከተማ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አዳማ  ከተማ ቀደም ሲል ከተገነባው በተጨማሪ  ሁለተኛውን  የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ መገንባት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ባለሙያዎች በ አሁኑ ጊዜ  የኃይል እጥረት ሊያጋጥም የሚችለው በ2005 ዓ.ም. ይሆን? ወይስ  በ2006 ዓ.ም. የሚለውን በማጥናት ላይ  ሲሆኑ፤ጥናታቸውን  በዚህ ሳምንት ውስጥ ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በደቡብ ክልል በዳውሮና በወላይታ ዞኖች አዋሳኝ ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው እና  ሲጠናቀቅ  1 ሺህ 870 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው የግልገል ጊቤ ቁጥር 3 ሀይል ማመንጫ  በ አካባቢ ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተሰነዘረበት እንደሚገኝ ይታወቃል።

ከአንድ ዓመት በሁዋላ፤ማለትም በመስከረም 2006 ዓመተ-ምህረት  እንደሚጠናቀቅ ዕቅድ የተያዘለት የዚህ የፕሮጀክት ግንባታ በአሁኑ ወቅት  የተጠናቀቀው  ገና 62 በመቶ  ያህሉ ነው።አቶ ኃይለ ማርያም  አዲስ ስትራቴጅ ተነድፎ በ አፋጣኝ ተግባራዊ እንዲሆን ተወሰነው  ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይጠናቀቃል ተብሎ ባለመገመቱ ነው  ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ  ግን  ከአቶ ሀይለማርያ ለየት ያለ ሀሳብ ነው የሰነዘሩት። እንደ አቶ ምስክር ገለፃ ፤የግልገል ጊቤ ሦስት ፕሮጀክት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ርብርብ እየተካሄደ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የአገሪቱ ኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም 2,178 ሜጋ ዋት መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ።

የአገሪቱን የኤሌክትሪክ ማመንጨት አቅም ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት ለማድረስ ተብለው በአምስት ዓመቱ የትዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከተያዙት  ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው በ ዓባይ ወንዝ ላይ ይገነባል የተባለውና ከ 6 ሺህ ሜጋ ዋት በላይ ያመነጫል ተብሎ የተነገረለት የህዳሴው ግድብ ነው።

የአምስት ዓመቱ ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ሁለተኛ ዓመቱን ሊያጠናቅቅ ወራቶች በቀሩበት በአሁ ጊዜ የህዳሴው ግድብ ግንባታ ገና ከ 9 በመቶ በላይ አለመነቃነቁ፤በብዙሀን ኢትዮጵያውያን ዘንድ የግድቡ ግንባታ አይደለም በ አምስት በ አስር ኣመትስ ያልቃል ወይ?’የሚል ጥያቄ እያስነሳ ነው። በሌላ በኩል የህዳሴውን ግድብ በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአቶ መለስ ዜናዊ ስም ሊሰየም መሆኑን የሪፖርተር ዘገባ ይጠቁማል።

No comments:

Post a Comment