ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ከፍተኛ የአመራር አባላት የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ እና ዶ/ር ታደሰ ብሩ ከኢሳት ጋር
ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት፣ ንቅናቄው በስልጣን ላይ ያለውን ሀይል አስገድዶ ከተቻለ ወደ ድርድር ካልተቻለም
ለማስወገድ፣ ፈጣን የሆነ ውጤታማ ስራ የሚሰራበትን ዝግጅት እያደረገ ነው።
ገዢው ፓርቲ ህልውናውንም
አገሪቱንም ከጥፋት ለመከላከል በአፋጣኝ የፖለቲካ ለውጥ በማድረግ ሁሉም በእኩል የሚሳተፉበት የሽግግር ጊዜ
አስተዳደር እንዲመሰረት የግንቦት7 መሪዎች አሳስበው፣ ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊው መስዋትነት ተከፍሎ ለውጥ ይመጣል
ሲሉ ተናገረዋል።
ድርጅታቸው ባለፉት አራት አመታት ጊዜያዊ የመንግስት የስልጣን ሽግግር አይነት ቅርጽ
ይዞ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ያወሱት አመራሩ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ አገዛዙ ከስልጣን ቢወገድ የስልጣን ክፍተት ይፈጠራል
የሚለውን ስጋት እንደቀረፈ ተናግረዋል።
ንቅናቄው፣ የኢትዮጵያ ድርጅቶችን ወደ ትብብር በማምጣት፣ በሚዲያ በኩል ያለውን ያገዛዙን የሚዲያ ሞኖፖሊ በመስበር እና ሁለንተናዊ ድርጅታዊ ጥንካሬ በመስራት በኩል ከፍተኛ ስራዎችን መስራቱን ገልጧል። ከድርጅቱ አመራሮች ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለምልልስ በቅርቡ እናቀርባለን።
No comments:
Post a Comment