ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ነባር ታጋይ የሆኑት አቶ አስገደ ገብረስላሴ ለአቶ መለስ ዜናዊ ወታደራዊ ትምህርት እንደሰጡዋቸው ይናገራሉ::
የአቶ መለስ ዜናዊን የ21 አመታት አስተዳዳር እንዴት ይገመግሙታል ተብለው የተጠየቁት አቶ አስገደ ፣ በርካታ ችግሮች መታየታቸውን አልሸሸጉም::
አቶ
መለስ ስልጣን ለቀው ያሳለፉትን አመራር ለመገምገም እድል አግኝተው ቢሆን ኖሮ ይመርጡ እንደነበር ተናግረው፣
ስልጣኑን የተረከበው አካልም የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ይመክራሉ::
የግንቦት 7 ከፍተኛ የአመራር አካል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የአቶ መለስ ዜናዊ ዜናዊ ስራዎች በተጨባጭ መመዘን እንዳለባቸው እና ሀዘኑም ምስጋናውም ከዚያ ጋር መታየት እንዳለበት ይገልጣሉ::
በኢትዮጵያ የተሻለ ስርአት ለመገንባት ፖለቲካው ሊለወጥ እንደሚገባ አቶ አንዳርጋቸው ይናገራሉ::
No comments:
Post a Comment