Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Tuesday, August 21, 2012

የአቶ መለስ ዜናዊን ዜና እረፍት ተከትሎ በመላው አገሪቱ ውጥረት ነግሷል

በአዲስ አበባ በርካታ ሰዎች ከእየ አካባቢያቸው ተሰባስበው የሚሆነውን በኢትዮጵያ ሬዲዮና እና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚከታተሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ህዝቡን የማረጋጋት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ገድል በማወጅና እና በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ በማቅረብ ላይ ናቸው።

በመንግስታዊ ድርጅቶች እና ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ መውለብለብ ጀምሯል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በየቦታው ፣ በሰፈሮች ውስጥ ሳይቀር ተበታትነው ይታያሉ።


በቀበሌዎችና ወረዳዎች ውስጥ የመደናገጥ ሁኔታ ይታያል፣ አግልግሎት በአግባቡ እየሰጡ አይደለም። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንኮች ገንዘባቸውን በሚያወጡ ሰዎች ተጨናንቀዋል። ሁሉም ባንኮች ከውስጥና ከውጭ ጠባቂዎችን አጠናክረው ከፍተኛ ፍተሻ በማድረግ ስራቸውን ለመስራት እየሞከሩ ነው።

በትናንት ምሽት ላይ 1600 ብር የነበረው ነጭ ጤፍ በዛሬው እለት 200 ብር ጨምሮ 1800 ብር ገብቷል። ህዝቡ የሚመጣው አይታወቅም በማለት እየገዛ ነው። በመላ አገሪቱ ከሀዘን ይልቅ የፍርሀት ድባብ እና ዝምታ ነግሷል።

ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ ቤተመንግስት አካባቢ ከፍተኛ ጥበቃ እየተካሄደ ነው። ሁሉም የአየር መንገዱ ሰራተኞች ከአካባቢው እንዲርቁ ተደርጎ የአቶ መለስ አስከሬን በሼክ ሙሀመድ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ታጅቦ ባለፈው ቅዳሜ መግባቱን ለማወቅ ተችሎአል። 

አውሮፕላኑ ካረፈ በሁዋላ አስከሬኑ በሽፍን መኪና ወደ ቤተመንግስት መወሰዱን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ውድ ተመልካቾቻችንና አድማጮቻችን አዳደስ መረጃውን እየተከታተልን እናቀርባለን

No comments:

Post a Comment