ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ
እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
የጠ/ሚኒስትር
መለስ ዜናዊ ሞት በይፋ ከተነገረ በኃላ የመጀመሪያ በሆነው የመንግስት መግለጫ የቀብር አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ
መቋቋሙን፣ከዛሬ ጀምሮ እስከቀብር ቀን የሚዘልቅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን መታወጁን፣የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ
እንዲውለበለብ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ
ብሔራዊ ኮሚቴው የቀብሩን ቀንና ሥነሥርዓት በተመለከተ በቀጣይ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁመው ጠ/ሚኒስትሩ አቶ
ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
አቶ በረከት ጠ/ሚኒስትሩ የት አገር እንደታከሙ፣የት አገር እንደሞቱ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡
No comments:
Post a Comment