ዜና / News: የኢትዮጵያው ጠ/ሚ፤ አቶ መለስ ዜናዊ በተወለዱ በ57 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት
ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሁለት ወራት ከተሰወሩ በኋላ ነው ዛሬ፤ ማክሰኞ፤ ነሀሴ 15 ቀን መሞታቸው
የተዘገበው።
ኢሳት ሀምሌ 23 ቀን፤ የአለምአቀፉን የቀውስ አጥኚ ቡድን (አይ.ሲ.ጂ) ውስጣዊ ምንጮችን ጠቅሶ የአቶ መለስን ሞት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ መለስን ሞት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት፤ በይፋ የአቶ መለስን ሞት ዘግበዋል። አልጀዚራን ጨምሮ፤ ሌሎች ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሀንም ዜናውን እየዘገቡት ይገኛሉ።
No comments:
Post a Comment