(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዳላስ የደስታ ሬስቶራንት ባለቤት የሆኑትን አቶ ያየህይራድ እና የኒን በማታ ተከትሎ
የገደላቸው ኢትዮጵያዊ ዴንቨር ከሚገኘው ዳግማዊት ግሸን ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ትምህርት ቤት የ2011 ኒሳን
መኪናውን እንዳቆመ ነው በፖሊስ የተደረሰበት። አብይ ግርማ ይባላል። ከዚህ በፊት ዴንቨር ነዋሪ ነበር። አትላንታ
ከተማም መምጣትን ያዘወትራል።
ዳላስ ከተማ ውስጥ ደግሞ በሊሞዚን መኪና ሹፌርነት ይሰራል። ከዚህ በፊት ዳላስ
በሚገኘው ደስታ ሬስቶራንት ውስጥ ከሰዎች ጋር ተጣልቶ ስለተፈነከተ፤ የጉዳት ካሳ በመጠየቅ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ
ሄዷል።
(ከላይ የጠቀስናቸው ጉዳዮች ሰፊ ትንታኔ የሚያስፈልጋቸው ስለሆኑ፤ ያንን ለጊዜው ትተን ዴንቨር ውስጥ በተያዘበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ በጥቂቱ እንግለጽላችሁ) የዴንቨር ፖሊስ ወደ አብይ መኪና በማምራት እንዲከፍትለት ሲጠይቀው፤ ልጁ መኪናውን አስነስቶ ለማምለጥ
ቢሞክርም… የዴንቨር ፖሊስ ቀደም ብሎ ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ስለነበር ከትንሽ የመኪና ማሯሯጥ በኋላ በቁጥጥር ስር
አውሎታል።
ከዚያም መኪናው ሲፈተሽ ያልተጠበቀ ነገር ተገኘ። 15 ሽጉጦችን ፖሊስ አገኘበት። ይህ ብቻ አይደለም…
ሊገድል ያሰባቸው ናቸው የተባሉ የ15 ሰዎች ዝርዝር አብሮ አለ። ከዚህም በተጨማሪ 20 ሺህ ዶላር በጥሬው በመኪናው
ውስጥ ይዞ ነው የተገኘው።
እነዚያ ሊገድላቸው ዝርዝራቸውን ይዞ የነበረው የ 15 ሰዎች ስም በፖሊስ ይፋ አልሆነም። ነገር ግን ይህ ከታወቀ ጊዜ አንስቶ የዴንቨር ነዋሪዎች በተለይም ድሮ አብይ ግርማን ያውቁት የነበሩት ሰዎች በጣም ተረብሸዋል። የዴንቨር ፖሊስ በአብይ ግርማ ላይ ጥብቅ የሆነ ምርመራ እያካሄደ ነው። ምናልባት ከዚህ በፊት የገደላቸው ሰዎች ካሉ፤ በመስቀለኛ ጥያቄዎች እያፋጠጡት ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ።
እነዚያ ሊገድላቸው ዝርዝራቸውን ይዞ የነበረው የ 15 ሰዎች ስም በፖሊስ ይፋ አልሆነም። ነገር ግን ይህ ከታወቀ ጊዜ አንስቶ የዴንቨር ነዋሪዎች በተለይም ድሮ አብይ ግርማን ያውቁት የነበሩት ሰዎች በጣም ተረብሸዋል። የዴንቨር ፖሊስ በአብይ ግርማ ላይ ጥብቅ የሆነ ምርመራ እያካሄደ ነው። ምናልባት ከዚህ በፊት የገደላቸው ሰዎች ካሉ፤ በመስቀለኛ ጥያቄዎች እያፋጠጡት ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ።
በሌላ በኩል ደግሞ የዳላስ ፖሊስ ይህንን ግለሰብ
እየፈለገው ነው። ወደ ዳላስ እንዲላክለትም ፈልጓል። የዴንቨር ፖሊስ በበኩሉ ገና የማጣራው ነገር አለ በማለት
ጉዳዩን እንደያዘው ይገኛል። ይህ በ እንዲህ እንዳለ፤ የደስታ ባለቤቶች የአቶ ያየህይራድ እና የወ/ሮ የኔነሽ የቀብር ስነ ስርዓት በከፍተኛ ድምቀት በትላንትናው እለት በዳላስ ከተማ ተፈጽሟል።
ማስታወሻ – በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው አብይ ግርማ መያዙን ለማብሰር ኢ.ኤም.ኤፍ የመጀመሪያው ነው። ሌሎች
ዜናውን ሲያቀርቡ የነበሩ የአሜሪካ ሚዲያዎች የግለሰቡን በቁጥጥር ስር መዋል ገና ባለመዘገባቸው በኛ ዜና ላይ
ጥርጣሬ ያደረባቸው ሰዎች ሊኖሩ ይቻላሉ።
በኢ.ኤም.ኤፍ. በኩል ግን አብይ ከመታሰሩ በፊት ስለነበረው ሁኔታ እና
እንዴት ሊያዝ እንደቻለ ጭምር ዝርዝር መረጃዎች ቢኖሩንም የግለሰቦችን መብት ለመጠበቅ ዝርዝሩን ከማውጣት
ተቆጥበናል። ግለሰቡ እንዲያዝ ለዴንቨር ፖሊስ መረጃ በመስጠት የተባበሩ ኢትዮጵያውያን የፈጸሙትን ተግባር በማመስገን
ወደ የዛሬው ዘገባችንን እናበቃለን።
No comments:
Post a Comment