Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, July 14, 2012

እነ አቶ አንዱአለም አራጌ ተፈረደባቸው

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ በተከሰሱት ላይ ከ8 አመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ፍርድ አስተላለፈ በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ከተላለፈባቸው መካከል በእስር ላይ የሚገኙና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ይገኙበታል።

አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሲፈረድባቸው፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ እስክንድር ነጋ፣ ውቤ ሮቤ እና ኦባንግ ሜቶ እያንዳንዳቸው በ18 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።


የሽዋስ ይሁን አለም፣ ዘለሌ ጸጋስላሴ፣አበበ በለው እና አበበ ገላው የ15 አመት ጽኑ እስራት እንዲሁም ምትኩ ዳምጤ እና መስፍን አማን እያንዳንዳቸው በ14 አመት ጽኑ እስራት ሲቀጡ ዮሃንስ ተረፈ በ13 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። ለግንቦት ሰባት ቡድን የሙያ ድጋፍ በማድረግ ጥፋተኛ ናቸው የተባሉት አብይ ተክለማርያምና መስፍን ነጋሽ ደግሞ እያንዳንዳቸው በስምንት አመት ፅኑ እስራት ተወስኖባቸዋል።

ውሳኔውን አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ( ሲፒጄ)፣ እንዲሁም ፍሪደም ናው እንዲሁም ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች አውግዘውታል። የሲፒጄው አፍሪካ ተወካይ ሙሀመድ ኬታ ” ፍርዱ የኢትዮጵያ እድገትና መረጋጋት ህዝቡን በሀይል በማፈን የተገኘ መሆኑን” የሚያመለክት ነው ብለውታል።

የፍሪደም ናው  ሃለፊ የሆኑት ፓትሪክ ግሪፊስ በእስክንድር ነጋና በሌሎችም ላይ የተላለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያ 
መንግስት የጸረ ሽብር ህጉን በመጠቀም ተቃውሞዎችንና ጠንካራ ትችቶችን ለማፈን እያዋለው መሆኑን ያሳያል 
ብለዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውንም ተቃውሞ ለማፈን መቁረጡን 
የሚያሳይ ፍ 
የፍርድ ቤቱ ሂደት አለማቀፍ ደረጃውን ያልጠበቀ መሆኑን የገለጠው አምነስቲ፣ በእስር ላይ የሚገኙት እስረኞች
እንደገና ፍርዳቸው መታየትና ከእስር መለቀቅ ነበረባቸው ሲል አምነስቲ አክሎአል።
 
 
በዛሬው ችሎት የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ” ከአንዴም ሁለት ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶብኛል እና እድሜ ልኩን የምታሰረው ከሞት ከተነሳሁ በሁዋላ ነው ወይ? “ሲሉ ተሳልቀዋል።

አቶ አንዳርጋቸው በአገሪቱዋ የፍትህ ስርአት መጥፋቱንም ያሰምሩበታል:: ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ከሬዲዮ ኔዘርላንድስ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ ፍርዱ አስገራሚ ይሆን የነበረው ነጻ ቢለኝ ነበር፣ ድሮም የምታገለው እንዲህ አይነቱን የፍትህ ስርአት ለመለወጥ ነበር፣ የአሁኑ የፍርድ ውሳኔ፣ የምታገልለት አላማ ጠንካራ እና ፍትሀዊ መሆኑን በድጋሜ ያረጋገጠ ነው፤ ከዚህ ቀደም እድሜ ልክ ተፈርዶብኛል፣ ይህኛውን ሰማይ ቤት እንድታሰረው አስበው የወሰኑት ሳይሆን አይቀርም” ብሎአል

No comments:

Post a Comment