Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Wednesday, July 11, 2012

በኢህአዴግ ውስጥ የጐላ ልዩነት እየተፈጠረ ነው


ከስድስት ወራት በላይ የስቆጠረውን ሀገር አቀፍ የሙስሊሞች ተቃውሞና ከዋልድባ ገዳምና የስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በኢህአዴግ ውስጥ የጐላ ልዩነት እየተፈጠረ መምጣቱን ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለገዢው አብዮታዊ ግንባር ኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን እንዳመለከቱት ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣናቱን በሀይማኖት ዙሪያ በተደጋጋሚ በማወያየት ላይ ይገኛል፡፡


ምንጮቻችን አንድ ተወያይን ጠቅሰው እንደዘገቡት በውይይቱም ሆነ በመወያያ ሰነዱ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት የሰፈረው ነጥብ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባቱን ተሳታፊዎቹ በቀና ልቡና እንዲረዱ የሚያግባባና የሚማፀን ነው፡፡ “ውይይቶቹ አስፈላጊ የሆኑት ከዝቅተኛ የፓርቲ አደረጃጀትና መዋቅር ጀምሮ ያሉ አባላት ‹መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ገብቷል› የሚል አቋም በመውሰዳቸው ነው፡፡” የሚሉት ተሳታፊው ፓርቲው ውይይቱም በተለያዩ ደረጃዎች ማካሄዱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

እንደ ምንጮቻችን ማብራሪያ እነዚህ አይነት ውይይቶች በተለያየ ጊዜ የተደረጉ ሲሆን ከተወሰኑ የተቃውሞ አስተያየቶች ውጪ አወያዮቹም ሆነ ተሳታፊዎች አንድ አይነት ቋንቋ ተነጋግረው የመውጣት አዝማሚያ አሳይተዋል፡፡ ተነጣጥለው ሲወያዩ ግን በሙስሊሞች የወቅቱ ጥያቄና በዋልድባ ገዳም መደፈር ጉዳይ ላይ መንግስት እየተከተለ ያለውን አቋም አምርረው የሚተቹ አባላት መበራከታቸው በፓርቲው ውስጥ የጐላ ልዩነት በመፍጠር ላይ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አመልክተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment