BY ሪቻርድ ዳዉደን, (የሮያል አፍሪካን ሶሳይቲ ዳይሬክተር), ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ
መለስ ዜናዊ ለውጭ እንግዶች ሲናገሩ በጣም የተዋጣላቸው ናቸው፡፡ ለሚያስተዳድሯቸው ኢትዮጵያውያን ሲናገሩ ግን እጅግ አስቸጋሪና ገታራ ናቸው፡፡ ባለፈው ጊዜ በካምፕ ዴቭድ የG-8 ሀገራት ስብሰባ ላይ ከሚሳተፉ 4 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አንዱ ነበሩ፡፡ እርዳታ ሰጪዎች መለስን ይወዷቸዋል፡፡ እራሳቸውም ብዙ ያነበቡ፤ሀሳቦችን ሲገልፁ ቁጥሮችን የሚደረድሩና ትኩረት ማድረግ የሚችሉ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ለብዙ መቶ ዘመናት የኖረች ሀገር እንደመሆኗ እርሷን ማስተዳደር ከብሮክራሲያዊ ስራ የዘለለ ልዩ ጥበብ የሚጠይቅ አይደለም፡፡ እርዳታው ደግሞ ልክ የወንዝ ያክል በዓመት ወደ 4 ቢያንስ ዶላር ይጎርፋል፡፡ በዚያ ላይ መለስ በሶሚሊያና በሱዳን በኩል ባሰማሯቸው ወታደሮቻቸው የአሜሪካ ዘብ ናቸው፡፡ ከቀድሞ አጋራቸውና የቀጠናው አታራማሽ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ባለበት የሚቀጥል ጠላትነት አሏቸው፡፡
አንድ የመለስ ሁኔታ የጨነቀው የአሜሪካ ዲፕሎማት ሰውዬው “የሙባረክ አባዜ” አለባቸው ብለውኛል፡፡ “ለሙባረክ የግብጽን ሚና በቀጠናው ምን አንደሆነ እንጂ ግብጽ ውስጥ ምን (አደገኛ ሁኔታ) እየተካሄደ እንደሆነ ፈጽሞ ልንነግራቸው አንችልም፤ በኢትዮጵያም(አቶ መለስ ዘንድም) ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው፡፡ በምርጫ 1997 ዓ.ም ተቃዋሚዎች ዋና ከተማዋ አዲስ አበባን እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ማሸነፋቸውን ሲያውጁ መንግስት መሪዎቹን ከማሰሩም በላይ በሀገር ክህደት ነበር የከሰሳቸው፡፡ ግማሾቹ ታሰሩ፤ የቀሩት ሀገር ጥለዉ ተሰደዱ፡፡ አሁን ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ 99.6% ድምጽ በማሸነፍ ሰማዕታቱ ቀና ብለው ያዩት የቴሌቪዥንዋን ‹‹ ኢትዮጵያ ›› ነው የአንድ ፓርቲ ስርዓት በሀገሪቷ ዘርግቷል፡፡
ባለፈው ሁለት ሳምንት ከአቶ መለስ ጋር በነበረኝ ቃለ መጠይቅ አቶ መለስ በመላ ሀገሪቱ ካሉ መንደሮች ተቃዋሚዎች የተመረጡበትን አንዲት መንደር እንኳ እንደማያውቁ ነግረውኛል፡፡ አንዳንዶች ያልሰመረ አምባገነናዊ ልማታዊነት ነው ይሉታል፡፡ መንግስት የሚለውን ካደረክ ከመንግስት የመሬት የውሃና የአገልግሎት ድጋፍ ታገኛለህ፡፡ ካላደረክ ምንም ታጣለህ፡፡ በህገ መንግስቱ የተደነገጉት የፖለቲካ መብቶች በባለስልጣናት ትእዛዝ ሲጣሱ ይውላሉ፡፡ የሚዲያ ነፃነትማ አይነሳም፤ በቅርቡ በወጣው ህግ መሠረት አታሚ ህገ ወጥ ነው ብሎ ያሰባቸውን ይዘቶች ያለማተም መብቱ እንደሆነ ደንግጓል፡፡ የህትመት ሚዲያው ያበቃለት መሆኑ የሚገባችሁ በኢትዮጵያ ጋዜጣ ማተም የሚችለው ማሽን የተያዘው በመንግስት መሆኑን ስታውቁ ነው፡፡
በ1983 ዓ.ም ስልጣን በኃይል ከያዙ ጀምሮ የአቶ መለስ ትልቁ ስኬት በዝቅተኛ ግብር እንደዚሁም ከክፍያ ነጻ በሆነ መሬት የውጭ ባለሀብቶችን መሳባቸው ነው፡፡ የቻይና ሞዴል በመከተል ባለሀብቶችን በመሳብ ግብርናውንና ፋብሪካዎችን ለማልማት ይሞክራሉ፡፡ አቶ መለስ “ከዚህ በፊት በማርክሲዝም ፍቅር የነደዱ ናቸው በሚል እንተማ ነበር፤ አሁን ደግሞ የቤተሰብ ማንኪያ ለውጭ ባለሀብቶች በመሽጥ እንከሰሳለን፤ ማካካሻ መሆኑ ነው” ብለውኛል፡፡ መለስ ለአበባ እርሻና ለምግብ እህል ከ4 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለውጭና ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ስጥተዋል፡፡ የመብራት ሀይል እንዲያገኙም ግድብ እየገነቡ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ከተሰሩ ግድቦችም ከአካባቢ ጋር ተስማሚ እንዲሁም ብዙ የውሃ ትነት የሌለበት ነው ይላሉ፡፡
ነገር ግን ዞሮ ዞሮ ነፃ ገበያ አሟልተው ኢይፈቅዱም፤ ባንክና ቴሌኮም በመንግስት ሞኖፖል ስር ናቸው፡፡ ሁሉም መሬት የመንግስት ነው፤ ይህ በዚህ እንደሚቀጥል መለስ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ መለስ ‹‹እንከን የማይወጣለት ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብተናል? አልገነባንም፤ በእድገት ላይ ያለ ጉዳይ ነው፤እግራችን የሚሮጠውን ያክል እየሮጠ ነው? አዎ፤ ይህ በአዲስ አበባ ብቻ አይደለም፤ በጣም ኪስ ነው የሚባሉ ቦታዎችም ጭምር ነው፡፡ ካለፉት መንግስታት በተቀራኒ እጅግ አስቸጋሪ ቀጠና ውስጥ የተረጋጋች ሀገር ፈጥረናል፡፡ አሰራራችን የትኛውንም መንደር ይዳስሳል፤ ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ አልታየም፤ መንግስት ሩቅና አላስፈላጊ ነበር›› በማለት ይናጋራሉ፡፡
አቶ መለስ ከምዕራብ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ወቀሳ በተቃራኒ የፖሊሲያቸውን ትክክለኛነት በግትርነት ይከላከላሉ፡፡ እድገታችሁ ከአካባቢ ጋር የማይስማማና ሀገሬውን ከትውልድ ቀየው እንደአልባሌ ነገር (bullshit) በግድ የሚያፈናቅል ነው በሚል የኦክላንድ ተቋም ያወጣውን ሪፖርትም ሙሉ በሙሉ አይቀበሉም፡፡ አርብቶ አደሮች በአርብቶ አደር የሕይወት ዘዬ እንዲኖሩ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ ስነግራቸው ትክክል መሆኑን ቢያምኑም እንኳ አስቀድመው አፍቃሬ ምዕራብ እንደሆንኩ ነግረውኝ ነበር የጀመሩት፡፡ፖለቲካውም ተመሳሳይ ነው፡፡
በ1983 ዓ.ም ስልጣንን በኃይል የተቆጣጠሩት መለስ ከአናሳ ብሔር እንደመገኘታቸው የመውጫ ቀዳዳ የሚሆናቸውን የትኛውም ብሔር (ብሔረሰብ) የራሱን ነፃነት እንዲያውጅ የሚያስችላቸውን ህግ በህገ መንግስቱ ደነገጉ፡፡ የፖለቲካ ችግር በተከሰተ ቁጥር የትኛውም ብሔር ኢትዮጵያዊነት ማቆም እንደሚችል ይነገራል፤ ነገር ግን በየትኛውም ሁኔታ በህዝብ ድምጽ ተግባራዊ የሚደረግ አይደለም፡፡ አሁን በጋምቤላ ያለው ሁኔታ ኢህአዴግን ምድጃ ላይ ጥዶታል፡፡ በጋምቤላ መሬት ሁሉ ለግብርና አልሚዎች ተሰጥቷል፡፡ ሰዎች ከመሬት በሃይል ስለመፈናቀላቸው አቶ መለስ አያምኑም፡፡ መሬታቸውን የለቀቁት በፍቃዳቸው መሆኑን ለማስረዳት “የጋምቤላ ህዝብ መሬት ባለበት ነው የሰፈረው፤ ደግሞም እርግጠኛ ሁን፤ ከንግዲህ የጋምቤላ ወጣቶች ለማረስ እንጂ ለጥበቃ ወደ እርሻ አይሄዱም” ነበር ያሉኝ፡፡
መለስ የሚመሩት ፈጣን የመንግስት ካፒታሊዝም ይሰራ ይሆን? በቅርቡ አዲስ አበባ በተደረገው የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ስብሰባ ወቅት ትችት የመጣው አንደ ከዚህ ቀደሙ ከምዕራባውያን መያዶች አልነበረም፤ የኢትዮጵያ ዋነኛ አጋር ከሆነችው ቻይና ነው፡፡ የቻይና የኢንቨስትመንት ፎረም ተጠሪ የነበረው ጋዎ ዘይፕንግ “እኛ ያደረግነውን የግድ አታድርግ” በማለት አስጠንቅቋቸው ነበር፡፡ ጋዎ ዘይፕንግ “ሰብኣዊ ልማትን ያላገናዘበ የኢኮኖሚ እድገት አያስፈልግም፤ እኛ ከአየር መዛባትና፤ የሃብት ኢ-ፍትሃዊ ክፍፍል የተነሳ እየተሰቃየን ነው፤ እናንተ ይህ ችግር ገና አልገጠማችሁም፤ በመሆኑም ያልተነካካ ነጭ ወረቀት በጃችሁ አለ፤ ከማጨማለቃችሁ በፊት ጥሩ ነገር ሳሉበት፡፡” በማለት ምክር ብጤም ጨምሯቸዋል፡፡
በዚህ አይነት ሁኔታ የአፍሪካ መሪን በአደባባይ የወቀሰ የቻይና ባለስልጣን አለ? የውጭ ባለሃብቶችም ደስተኞች አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያን እድገት እየመሩ ቢሆንም አሁን ግን በሚገኘው ትርፍ ላይ ከመንግስት ሁሉን ፈላጊነት ጋር ግብግብ መግጠም ግድ ብሏቸዋል፡፡ የአበባ እርሻ ላይ የተሰማሩ ኩባኒያዎች ምርታቸውን ለማጓጓዝ የመንግስት ንብረት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውጭ እንዳይጠቀሙ በድንገት ተነገራቸው፡፡ ይህ ከሚያመርቱበት ማሳ እስከ አዲስ አበባ እና ከዚያ ወደ እውሮፓ መጫንን ይጨምራል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የአበባ እርሻዎች የአንዱ ባለቤት የሆነ ሰው በጭንቀት ተውጦ “ኢትዮጵያ እስካሁን እንዲህ አይነት ኩባኒያ የላትም” ቢለኝም ይህንን ተግባራዊ ያላደረገ ተቋም እንደሚቀማ ታውቋል፡፡ መንግስት የውጭ ኢንቨስትመንትን ወደ ሀገር ውስጥ ከሰበ በኋላ አሁን ግን እየተጫናቸው ትርፋቸውንም መቀማት ይፈልጋል፡፡
መለስ የኢኮኖሚ እድገት የማይፈታው ችግር
ከየአቅጣጫው እያዋጣቸው ነው፡፡ የዋጋ ንረቱ በ50% እየጋለበ ነው፡፡ ያናገርኳቸው ኢትዮጵያዉያን የኑሮ ውድነቱ በህይወት ዘመናቸው ብዙ የማያውቁት መሆኑን ነግረውኛል፡፡ ዋነኛ የኢትዮጵያውያን ምግብ የሆነው ጤፍ ዋጋ በ4 እጥፍ በመጨመሩ ድሆች ሕይወትን የማይኖሩባት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎች ስራ በሌለበት ተመራቂዎችን ያመርታሉ፡፡ በቅርቡ ያነጋገርኳት አንዲት ተመራቂ መቶ አካባቢ ሆነው ከተማሩ ጓደኞቿ አስሮቹ ብቻ ስራ ላይ እንዳሉ ነግራኛለች፡፡ የመንግስት ተስፋ ግን ኢኮኖሚው በፍጥነት ያድጋል የሚል ነው፡፡ ቀጣዩ የሀብት ምንጭ ማዕድን መሆኑን ተስፋ ያረገው መንግስት ነዳጅ ሊወጣ እንደሚችል አቶ መለስ በቅርቡ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
ነገር ግን በቅርቡ ይህ ሊገጥመው ይችላል፤ አብዛኛው የከተማ ድሃ በምግብ እህል ላይ ባለው የዋጋ ንረት፤ ተመርቀው ስራ በማያገኙት የከተማ ወጣቶች፤ ነገሩ…. የአረቡ ዓለም መነሳሳት የኢትዮጵያውያንን ትኩረት አግኝቶ ነበር፡፡ ይህን በኢትዮጵያም መከሰቱ አይቀሬ ነዉ--ተመልከቱ!
Source: http://www.ethiomedia.com/2012_report/fenote_forty_four.pdf, ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ, page 3
No comments:
Post a Comment