Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Monday, August 13, 2012

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአረብሳት ላይ እንዲወርድ ተደረገ

የኢሳት ዜና:- ቴሌቭዝን የሳተላይት ስርጭት በኢትዮጵያ መንግስት መታወኩ ታወቀ። ይሄንን ተከትሎም፤ የአረብ ሳት የኤትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከሳተላይት ስርጭት አግዷል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሜኒሳቴር ባለስልጣናት፤ አረብ ሳት በኤርትራ ቴሌቭዥን ላይ የሚያካሂደውን የማወክ ተግባር የማስቆም ህጋዊና ተቆማዊ ሀላፊነት እንዳለበት አሳስቧል።

አረብ ሳት የኢትዮጵያ ቴሌቭዥንን ከአየር ከማውረድ ባሻገር የሄደበት ቀጣይ እርምጃ ስለመኖሩ አልታወቀም። የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከኧረብ ሳት ከመውለዱ በፊት የኤርትራ ቴሌቭን በሚታወክበት ወቅት ኢቲቪም እብሮ ሲታወክ ቆይቶል።

የህወሃት መከፋፈል ቀጥሎአል የብአዴን አመራር አካላት በአማራ ክልል ከማክሰኞ እለት እስከ ሃሙስ ድረስ ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርገዋል።

በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩን ጨምሮ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ስብሰባቸው ዋነኛ አጀንዳ የሆነው በእነ አቦይ ስበሃት ነጋ ለረጅም ጊዜ ሲመራ የነበረውን የህወሃት ድርጅትን አፍርሶ በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርጉት ትልቅ ትግል መሆኑን ከውስጣዊ ምንጮች የተገኘው ሪፖርት ያሳያል ።

Sunday, August 12, 2012

ባንኮች የውጭ ምንዛሪ መስጠት አዳግቷቸዋል

ከውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት ጋር በተያያዘ በአገሪቱ ውሰጥ የሚንቀሳቀሱ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ለሚፈልጉ ኩባንያዎች ሌተር ኦፍ ክሬዲት (L/C) መክፈት እንዳልቻሉ ታወቀ፡፡ በተለይ የአገሪቱ ትልቁ የንግድ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለደንበኞቹ ሌተር ኦፍ ክሬዲት መክፈት ሲያቆም፣ ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የአገሪቱ የሦስት ወራት የውጪ ንግድ ከመቀነሱ ጋር በተያያዘ ነው የሚል መልስ እየሰጠ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትርፍ በ40 በመቶ ቀነሰ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ያተፈረው ትርፍ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ40 በመቶ ቀነሰ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም የድሪምላይነር አውሮፕላንን መምጣት አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በቢሮአቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ እ.ኤ.አ በ2011/2012 የበጀት ዓመት አየር መንገዱ የተጣራ 730 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ ተናግረዋል፡፡ አየር መንገዱ እ.ኤ.አ በ2010/2011 በጀት ዓመት ያገኘው የተጣራ ትርፍ 1.23 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን፣ ይህ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተገኘው ትርፍ በ500 ሚሊዮን ብር ይበልጣል፡፡

በማሌዥያ ጫት ይዛ የተገኘችው ኢትዮጵያዊ ተከሰሰች

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የተከለከለ ዕጽ  በማዘዋወር የተጠረጠረችው ኢትዮጵያዊቷ የቤት እመቤት ጫት ይዛ በመገኘቷ ትናንትና በፍርድ ቤት ክስ እንደተመሰረተባት የተለያዩ የማሌዥያ የዜና አውታሮች ዘገቡ።

የ36 ዓመቷ ሙና መሃመድ ኢብራሂም፣ እ.ኤ.አ ሃሙስ ኦገስት 2/ 2012 የማሌዥያው  ኬ.ኤል ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ውስጥ  90 ኪሎግራም የሚመዝን ካቲኖን የተሰኘ እፅ ወይንም ጫት ይዛ በመገኘቷ በቁጥጥር ስር እንደዋለች ታውቋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በአርማጭሆ ወታደራዊ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሕአግ በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ልዩ ስሙ አዋሳ በተሰኘ አካባቢ ከመንግስት ልዩ ሃይል ታጣቂ ጋር ሐምሌ 28-2004 ዓ∙ም ባካሄደው ውጊያ 11 የመንግስት ቡድን ቅጥረኞችን በመግደልና 19 በማቁሰል አንፀባራቂ ድል ማግኘቱን ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

በእለቱ የግንባሩ  ሰራዊት የተለመደውን ታሪካዊ ጀብድ ሲያከናውን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ድጋፍና አቀባበልም እንዳደረገለት ገልጧል።

ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ የሚታየው ገንዘብ የማሸሽ እንቅስቃሴ ንግዱን እየጎዳ የኑሮውን ውድነትም እያባበሰው ነው ተባለ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በአንድ የግል ባንክ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኛ ለኢሳት እንደገለጡት፣ የተለያዩ የውጭ እና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ባለፉት ሁለት ወራት ከዚህ በፊት ታይቶ ባልታወቀ ሁኔታ ገንዘባቸውን አሽሽተዋል። ይህንኑ ተከትሎም ንግድ ባንክ ለመድሀኒትና መሰረታዊ ለሚባሉት የፍጆታ እቃዎች መግዢያ ካልሆነ በስተቀር ፣ ማንኛውም ነጋዴ ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዳይከፍት መመሪያ አስተላልፎአል። እገዳው በአገሪቱ የሚታየው የዶላር እጥረት እስከሚቀረፍ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚጸና ታውቋል።

ብሄራዊ ባንክም ሆነ ንግድ ባንክ እስካሁን ድረስ የሰጡት ይፋዊ የሆነ መግለጫ  ባይኖርም፣ የባንክ ሰራተኞች ግን ዶላር በገፍ ወደ ውጭ አገር እየተሸኘ መሆኑ ለችግሩ ዋነኛው መንስኤ ሆኗል ብለው እንደሚያምኑ የባንክ ሰራተኛው ገልጠዋል። የአቶ መለስ ዜናዊ የደህንነት ሁኔታ በውል አለመታወቅ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን ለማሸሻቸው ዋነኛ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነው ሰራተኛው ግምታቸውን ያሰፈሩት።

Friday, August 10, 2012

የአቶ መለስ መሰወር የስልጣን ሽኩቻና ፍርሀትን ጋርጧል ተባለ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ለረጅም ግዜ ከስልጣን መሰወር፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻ፤ በአፍሪካው ቀንድ ደግሞ፤ ፍርሀትን እንደፈጠረ ፋይናንሳል ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ዘገበ።

መንግስት አቶ መለስ ከሕመማቸው እያገገሙ እንደሆነ ቢናገርም፤ የአቶ መለስ ዜናዊ መሰወር ግን የጎሳ ፖለቲካን አደጋዎች እንዲያገጡ በሚያደርግና፤ ስርአቱን ለአደጋ በሚያጋልጥበት መለኩ ድብቅ የስልጣን ሽኩቻን ጭሯል ሲል ፋይናንሻል ታይምስ ዘግቧል።

በደሴ ከተማ ሙስሊሞች ከፌደራል ፖሊስ ጋር ተጋጩ

ኢሳት ዜና:-ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የጁመኣን ሶላት ጸሎት ለማድረስ ዛሬ በደሴ አረብገንዳ የተሰባሰቡ ሙስሊሞች ከፖሊስ ጋር ሲጋጩ ውለዋል።

በደሴና አካባቢዋ የሚገኙ ሙስሊሞች አረብገንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው መስጊድ ለመስገድ በሚሰባሰቡበት ወቅት፣ በስፍራው ሲጠባበቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በመስጊዱ ጸሎት ማድረስ አይቻልም በማለት መከልከላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተፈጠረው።

ገዢው ፓርቲ ህዝብን ያረጋጋሉ የተባሉ ካድሬዎችን ወደ ገጠር አሰማራ

ኢሳት ዜና:- ነሀሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ከፍተኛ የህዝብ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ገዢው ፓርቲ ህዝብን ለማሳመን ይችላሉ ብሎ የሚያስባቸውን ካድሬዎች ወደ ገጠር መላኩ ታውቓል።

የብአዴን ካድሬዎች በአማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች ህዝቡን እንዲያረጋጉ እንዲሁም የህዝቡን ስሜት እንዲያጠኑና ወደ ማእከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ተልከዋል። ካድሬዎቹ ህዝቡን ለማሳመን ምን ማለት እንዳለባቸው በትክክል እንደማያውቁ፣ ይልቁንም ራሳቸው ካድሬዎቹ በከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።