Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Saturday, July 14, 2012

ሰበር ዜና በአዋሊያ ግጭት ተቀሰቀሰ

ኢሳት ሰበር ዜና 
ዓርብ ሐምሌ 6 ቀን 2004 ዓ.ም፡- በኢህአዴግ መንግሥትና በኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ የተፈጠረው መቃቃር ወደ አጠቃላይ አካላዊ ግጭት አመራ፡፡ ዛሬ ከምሽቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በአወሊያ መስኪድ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለእሁድ አጠቃላይ የአንድነትና የድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ ዝግጅት በማድረግ ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ቅጥር ጊቢውን ጥሶ በመግባት ሙስሊም ማህበረሰቡን በቆመጥ በአስለቃሽ ጭስ በመደብደብና መሳሪያ ወደ ላይ እና ወደ ሰው በመተኮስ ጉዳት በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

እነ አቶ አንዱአለም አራጌ ተፈረደባቸው

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በእነ አንዱአለም አራጌ የክስ መዝገብ በተከሰሱት ላይ ከ8 አመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ፍርድ አስተላለፈ በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ከተላለፈባቸው መካከል በእስር ላይ የሚገኙና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ይገኙበታል።

አቶ አንዱአለም አራጌ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ሲፈረድባቸው፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ እስክንድር ነጋ፣ ውቤ ሮቤ እና ኦባንግ ሜቶ እያንዳንዳቸው በ18 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

በሲዳማ ዞን ያለው ውጥረት እየተባባሰ ነው

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በቅርቡ ከሲዳማ ዞን እጣ ፈንታ እንዲሁም አጠቃላይ የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተነሳው ውጥረት መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ ባለፈው ሳምንት የግንቦት7 አባላት ናቸው ተብለው የተረጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ዘጋቢያችን የገለጠ ሲሆን፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑት አቶ በረከትንና አቶ አባይ ጸሀየን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ፓርቲዎች በችግሩ ዙሪያ በአዋሳ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ለነጻነትና ለፍትህ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደንቦባ ናቲ ለኢሳት እንደተናገሩት የሲዳማ ሽማግሌዎችና የአካባቢው ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ሲሆን ተቃውሞው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል:: አቶ ደንቦባ እንዳሉት የሲዳማ የኢህአዴግ አባላት በብዛት አባልነታቸውን እየሰረዙ ነው::

Source:  ኢሳት ዜና

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤“ሰላማዊ ትግሉም እየተበላሸ እና ወደ አላስፈላጊ ጫፍ እየተገፋ ነው” አለ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
የአመራር አባሉ በጥይት ተደብድቦ የተገደለበት  የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤“ሰላማዊ ትግሉም እየተበላሸ እና ወደ አላስፈላጊ ጫፍ እየተገፋ ነው” አለ። ”የዳኝነት ሥርዓቱም  ቅጥ ባጣ መልኩ በኢህአዴግ  አመራር የሚሽከረከር አሻንጉሊት ሆኗል” ሲልም  መኢአድ የፍትህ ስርዓቱን አጥብቆ ኮንኗል።

ድርጅቱ ትናንት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤  በርካታ አመራሮቹና አባላቱ   ያለምንም ጥፋታቸው በኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች  ሰብዓዊ ክብራቸው እየተገፈፈ እና ዲሞክራሲያዊ መብታቸው እየተጨፈለቀ እንደሚገኝ  አመልክቷል። በተለይ በ አማራ ክልል የተለያዩ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አመራሮቹ  በግፍ እየተያዙ ወደ ወህኒ እየተወረወሩ መሆናቸውን የጠቀሰው መኢአድ፤ በሽብርተኝነት ህግ ሽፋን እየተፈፀመ ባለው ግፍ  ሰላማዊ ትግሉ እየተበላሸ እና ወደ ጠርዝ እየተገፋ እንደሆነ ገልጿል ።

Wednesday, July 11, 2012

ለአስቸኳይ ልዩ ስብሰባ የተጠራው ፓርላማ የቴሌን ህግ አጸደቀ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
99 ነጥብ ስድስት በመቶ በአንድ ድርጅት አባላት የተሞላው ፓርላማ ለአስቸኳይ ልዩ ጉባኤ የተጠራው አዲሱንና አወዛጋቢውን የቴሌ ህግ ለማጽደቅ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል። ዘጋቢያችን እንዳለው በጥሪው ላይ አስቸኳይና ልዩ የተባለው ፓርላማው ካለፈው ሰኔ ሰላሳ ቀን ጀምሮ እንደተዘጋ በመቆጠሩ ነው።

የፍትህ ዋና አዘጋጅ ደህንነት አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በሳምንታዊው ፍትህ የአማርኛ ጋዜጣና በዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የግል እንቅስቃሴ ላይ የደህንነት ኃይሎች የሁለት ቀናት የሃያ አራት ሰዓታት ግልጽ ክትትል ማድረጋቸውን ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡ በጋዜጣው የኢሜል አድራሻም ከአልሸባብ ለዋና አዘጋጁ የተላከ የሚያስመስል ቁጥር 2 የፈጠራ ደብዳቤ ከሰሞኑ ተልኳል፡፡

ቅዳሜ ሰኔ 30 ቀን እና እሁድ ሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጋዜጠኛ ተመስጌን ራሳቸውን በግልጽ ባቀረቡ የደህንነት ሰዎች ሙሉ ክትትል ሥር የዋለ ሲሆን ተከራይቶ በሚኖርበት ቤት ዙሪያ፣ በመመገቢያ ሥፍራው፣ በቢሮው አቅራቢያ፣ በቤተሰቦቹ መኖሪያ ቤት ዙሪያ እና በሚንቀሳቀስበት ሁሉ እየተፈራረቁ  በመከታተል አእምሮው እረፍት እንዲያጣና እንዲጨናነቅ ጫና ለመፍጠር ሞከራውል በማለት ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

በጭቆናና በክፋት ያደገ አእምሮ አደገኛ እንደሆነ በባለሞያ ተገለፀ

እንክብካቤ እየተደረገለት ያላደገ በጭቆናና በክፋት ያደገ በተዛባ አያያዝ ያደገ አእምሮ ለራሱ ለህብረተሰቡና ለአገርም ጐጂ እንደሚሆን ተገለፀ፡፡ ይህን የገለፁት ታዋቂው የህክምና ባለሞያ ዶ/ር መስፍን አርአያ ናቸው፡፡ ዶ/ር መስፍን ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያት ማህበር ከፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ጋር በመተባበር “ትውልዱን ከሱስ እናድን” በሚል በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት ኤጀንሲ ባዘጋጀው ኪነጥበባዊ ምሽት ላይ ነው፡፡

በኢህአዴግ ውስጥ የጐላ ልዩነት እየተፈጠረ ነው


ከስድስት ወራት በላይ የስቆጠረውን ሀገር አቀፍ የሙስሊሞች ተቃውሞና ከዋልድባ ገዳምና የስኳር ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ በኢህአዴግ ውስጥ የጐላ ልዩነት እየተፈጠረ መምጣቱን ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለገዢው አብዮታዊ ግንባር ኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን እንዳመለከቱት ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ፓርቲው ከፍተኛ ባለስልጣናቱን በሀይማኖት ዙሪያ በተደጋጋሚ በማወያየት ላይ ይገኛል፡፡

ግራ የተጋባው ፓርላማ ነገ ለልዩ ስብሰባ ተጠራ

ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት የመዝጊያው ጊዜ እስከዛሬ ድረስ ባልተለመደ ሁኔታ የተራዘመው ፓርላማ ፣ ነገ ረቡእ ለልዩ ስብሰባ ተጠርቷል። በነገው ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ ይገኙ እንደሆን ለምንጫችን ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ፣ “እስካሁን ድረስ ይገኛሉ የሚል ፍንጭ አለመሰማቱን፣ ይሁን እንጅ ይገኛሉ ብለው እንደማያስቡ” ተናግረዋል።

የኦሮሞ ነጸናት ግንባር በቶሮንቶ የተሳካ ስብሰባ አደረገ

ኢሳት ዜና:- ሐምሌ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
በብርጋዲየር ጄ/ል ከማል ገልቹ የሚመራው የአሮሞ ነጸናት ግንባር ባለፈው ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ጁላይ 6 ቀን 2012 በቶሮንቶ ካናዳ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አድረገ። 

በዚህ በቶሮንቶ አካባቢ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆችና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት የግማሽ ቀን ስብሰባ ላይ፤ የድርጅቱ የበላይ አመራር አካላት፡ ማለትም ብርጋዲየር ጄነራል ሀይሉ ጎንፋ ከአስመራ በስልክ፡ ዶ/ር ኑሮ ደደፎና የድርጅቱ ቃል አቀባይ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባለሟል አቶ ተማም ባቲ፤ በአካል ተገኝተው፤ ንግግር በማድረግ ከተሰብሳቢው ጋር ተወያይተዋል።