Welcome!

"If you are neutral 0n the situations of injustice, You have choosen the side of oppressors." -Desmond tutu

Thursday, November 15, 2012

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፦ "በንብረት ጉዳይ ዳግም ፍርድ ቤት እንዳልቀርብ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ" አለ

ኢሳት ዜና:- “እኔም ሆንኩ ባለቤቴ በንብረት ውርስ ምክንያት መከራከር አንፈልግም፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ከዛሬ በኋላ እንዳልቀርብ ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ይሰጥልኝ፤” ሲል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፍርድ ቤትን ጠየቀ።

በፈጠራ የሽብርተኝነት ወንጀል ተከሶ የ18 ዓመት እና  ፅኑ እሥራትየተፈረደበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ዓቃቤ ሕግ እንዲወረስ ስለጠየቀበት ንብረት ቤተሰቡም ሆነ እሱ መከራከር እንደማይፈልጉ ለፍርድ ቤቱ  ያስታወቀው ትናንት ነው።

የ”ጉዞ ኃይለማሪያም” አንድምታ

“ቤተመንግስት ለመግባት፤መለስ ልብ መግባት”

ከጥበቡ ግርማ ሙላቱ
ጥቅምት 10 2005 ዓ.ም. ለንባብ የበቃው የሪፖርተር ጋዜጣ ልዩ ዕትም ለአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የኋላ ታሪክ ሰፊ ሽፋን ሰጥቶ ብቅ ማለቱ ይታወሳል፡፡ የዘገባውን ተኣማኒነት ለማጎልበት ጋዜጣው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የቀድሞ የሥራ ባልደረቦችንና ወዳጆች አግኝቶ ለማነጋገር ብዙ የደከመ ይመስላል፡፡ 

የእምዬን ወደ አብዬ ይብቃ ለዴሞክራሲ ያልበቃው ኢህአዴግ ነው!

Sibehat Nega
በቅርቡ የመወያያ አጀንዳ ሆነው ከሰነበቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ የሚጠቀሰው አንድ የህወሓት አንጋፋ ባለስልጣን “የኢትዮጵያ ህዝብ ለዴሞክራሲ ብቁ አይደለም” በማለት ህዝቡን መዝለፋቸውን የሚገልፀው መረጃ ነበር፡፡ እኚህ አንጋፋ ባለስልጣን በተለያዩ ጊዜያት የህወሓት/ኢህአዴግን እኩይ አላማና ፍላጎት ያለአንዳች እፍረት በይፋ በመናገር አነጋጋሪ መሆን ጀምረዋል፡፡

 ሰውየው ሆነብለውም ይሁን አምልጧቸው የሚናገሯቸው ሀሳቦች፣ የአምባገነናዊ ስርዓቱን እኩይ አስተሳሰብ ለአደባባይ እንዲውል የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን አይነት አስተሳሰብ ባላቸው አካላት እየተገዛ እንደሆነ እንዲገነዘብ የሚረዳ ነው፡፡

አምባሳደር ተወልደ ዓጋመ ከፓርቲው ለቀቁ (እየሩሳሌም አርአያ)

የሕወሐት ማ/ኰሚቴ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ ዓጋመ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው እንደለቀቁ ምንጮች አረጋገጡ። ባለፈው በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ከማ/ኰሚቴ አባልነት እራሳቸውን እንዳገለሉ አስታውቀዋል።

በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ 1993ዓ.ም በሑዋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል። በተጨማሪ ባለቤታቸው ሮማን ገ/ስላሴ በፓርቲው ሊ/መንበር « አይኖዋን ማየት አልፈልግም» ተብለው ከፓርቲው ርቀው እንደነበር ምንጮቹ አስታውሰዋል።

Tuesday, November 13, 2012

የሀይንሪኽ በል ድርጅት ከኢትዮጵያ የመውጣት ውሳኔ

መንግሥታዊ ያልሆነው የጀርመናውያኑ የሀይንሪኽ በል ድርጅት ኢትዮጵያን ለቆ እንደሚወጣ እና በአዲስ አበባ የሚገኘውን ጽሕፈት ቤቱንም እስከ ፊታችን ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚዘጋ አስታወቀ። 

በደራ ወረዳ አንዲት ሴት የባሉዋን ብልት በአደባባይ በገመድ እንድትጎትትና እንድትስም ተደረገ

Torturing
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ አድርገዋል።

የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ካስደረጉ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም ብልቱን እንድትስም አስደርገዋል። በእርግጫ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጅ አስወርዳለች። በድርጊቱ አልሳቃችሁም የተባሉትም ተደብድበዋል።

ኢትዮጵያ የተመድ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል ሆና መመረጡዋ ተተቸ

United Nations human right
ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ሰሞኑን ባካሄደው ምርጫ አስከፊ ሰብአዊ መብቶችን ጥሰት የሚፈጽሙ በርካታ አገሮችን መምረጡ በሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች ትችት ቀርቦበታል።

የሰብአዊ መብቶች አስከባሪ ድርጅቶች እንዳሉት ሰኞ እለት ከተመረጡት 18 አገሮች መካከል መስፈርቱን የሚያሟሉ አገሮች ሶስት ብቻ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ለአፍሪካ 5 መቀመጫዎችን የሰጠ ሲሆን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኢትዮጵያ፣ ጋቦን፣ ኬንያና ሴራሊዮን ለቦታው ተመርጠዋል። ጃፓን ፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ፓኪስታንና ዩናይትድ አርብ ኤምሬትስ ደግሞ የኤስያ ፓስፊክ አገሮችን መቀመጫዎች ወስደዋል። 

Thursday, November 8, 2012

ኢህአዴግ ስንት ቦታ ሊሰነጠቅ ይችላል?

 በተመስገን ደሳለኝ
ብርዱ የጥቅምት ነው፤ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚያንቀጠቅጥ ኃይለኛ ቅዝቃዜ፡፡ አዲስ አበባ ገና ከእንቅልፏ በመንቃት ላይ ነች፡፡ ለስራ የቸኮሉ መንገደኞች ትራንስፖርት ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይካለባሉ፡፡ ማክሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ብስራተ ገብርኤል አደባባይ ‹‹መገናኛ ራዲዮ›› በያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

 የትራፊክ ፖሊሶቹ ስራ የበዛባቸው ይመስላሉ፡፡ 12 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ሲል በሁለት የሞተር ብስክሌት በተፈናጠጡ የትራፊክ ፖሊሶች ፊት አውራሪነት አንዲት ሳይረን የተገጠመላት የፖሊስ ታርጋ የለጠፈች መኪና የ‹‹መንገድ ልቀቁልኝ›› ጩኸቷን እያንባረቀች አቋርጣ በማለፍ ወደ ሳር ቤት አቅጣጫ ከነፈች፡፡ ሶስት ‹‹ቪኤት›› መኪና ሰለሱ፡፡

Tuesday, November 6, 2012

የኦህዴድ ክፍፍል ወደ ዞን ባለስልጣናትም ወረደ

ኢሳት ዜና:-
OPDO
የኦህዴድ ክፍፍል ወደ ዞኖች ወርዷል፣ ይህን መንግስት ተቀብለን እንቀጥላለን ወይም አንቀጥልም የሚሉ ሁለት ቡድኖች መፈጠራቸውን አባላቱ ገለጡ ስማቸው እንዳይገለጥ ያስጠነቀቁ የኦህዴድ ባለስልጣናት ለኢሳት እንደገለጡት በኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮች የተፈጠረው መከፋፈል ወደ ዞኖች ወርዶ በድርጅቱ ውስጥ ሁለት ቡድኖች እንዲፈጠሩ አድርጓል።

ከፍተኛ ክፍፍል በሚታይበት በሀረሪ ክልል ፣  በአንድ በኩል ይህንን ስርአት ደግፈን መጓዝ አለብን የሚሉ  ኦህዴዶች ደጋፊዎችን ለማሰባሰብ ሙከራ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ” ብዙሀን እንዴት በአናሳ ቡድን ይገዛሉ? ” በማለት ስርአቱን አንቀበልም ያሉ ሀይሎች የራሳቸውን ደጋፊ በማሰባሰብ ቡድን እየፈጠሩ ነው።

በሲዳማ ዞን ቡና አምራች አርሶ አደሮች ተቃውሞ አስነሱ

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል፣ ሲዳማ ዞን፣ በንታ ወረዳ ቡና አምራች ገበሬዎች ተቃውሞውን ያነሱት የቡና መሸጫ ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ሆኖአል በማለት ነው።